የአገው ማኅበረሰብ ተወካይ አልላከም
የህወሓት መሪዎች ኢትዮጵያን እናድን በሚል ማምታቻ ቃል ኢትዮጵያን ለማፍረስ ፌደራሊስት ኃይሎች ያሏቸውንና ጫሚሶወችን ጋብዘዋል። ከእነኚህ ተጋባዥ ሰዎች አብዛኛዎቹ
1) የሚከፈላቸውን አበል እንጂ የህወሃት ያረጀና ያፈጀ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ሀሳብ ምን እንደሆነ አያውቁም
2) በኢትዮጵያ ፖሊቲካም ሆነ ኢኮኖሚ ተፅእኖ ፈጣሪዎች ያልነበሩ ናቸው
3) የህወሃት ስሪቶች እንደ መሆናቸው መጠን ወደፊትም ተጽእኖ መፍጠር ቀርቶ ቤተሰባቸውን ሊያሳምኑ አይችሉም
4) እስከካሁን ባለው መረጃ ኦብነግ፣ ኦነግ፣ ሲአንና በፕሮፌሰር መረራ የሚመራው ኦፌኮ ግብዣውን ተቀብለው አልሄዱም።
በአጠቃላይ ህወሃት እያደረገ ያለው አልሞትኩም፣ አልበሰበስኩም ትግል የትግራይን በጀት በአበል ስም መበተን፣ መስጠትና መቀበል ካልሆነ በቀር የሚያመጣው አንድ ውጤት የለም። የትግራይ ሕዝብ በፊት ለፊት ህወሃትን በቃኝ እያለ እየተናገረ ነው። መቼ እንደሆነ እርግጠኛ ባልሆንም የትግራይ ሕዝብ የህወሃት መሪወችንና የመንፈስና የስጋ ልጆቻቸውን ሁሉንም በቁጥጥር ስር አውሎ ለማዕከላዊ መንግስት አስሮ እንደሚያስረክባቸው አልጠራጠርም። (Brook Abegaz – P)
ይህ በእንዲህ እንዳለ ናትናኤል መኮንን ከዳዊት ከበደ የአውራምባ ታይምስ ባለቤት ፌስቡክ ገጽ ላይ በትግርኛ የተለጠፈውን የመቀሌውን ቅሌት ተርጉሞ በፌስቡክ ገጹ አትሞታል።
ዳዊት የጻፈው ትርጉም እንዲህ ይላል፤ “ኦነግን ወክየ ነው የመጣሁት ያለኝ ኣንድ ወጣት ፖለቲከኛን ቃለመጠይቅ ኣድርጌ ነበር፤ ሆኖም ግን ቪድዮውን ከማስተላለፌ በፊት የተላከው ወኪል በትክክል የኦነግ ወኪል መሆኑን ለማረጋገጥ ወደ ኦነግ ጽህፈትቤት ደውዬ ያገኘሁት መልስ በጣም የሚያሳዝን ሆኖ ኣገኘሁት። እንደዚህ የሚባል ስም በአመራር ደረጃም ይሁን በኣባል ደረጃ የለንም፣ በመሠረቱ ወደ መቀለ ስብሰባ አንዲሳተፍ የላክነው ወኪል የለንም ብለው ኣሳፈሩኝ፤ ህውከት፣ ድካም ብቻ ነው ያተረፍኩት። በሉ ኣበሉን ስጡትና ላኩት”።
በተጨማሪ ከደብረጽዮን በስተቀኝ አንድ ወንበር ቀጥሎ ተቀምጦ የሚታየው በፊትለፊቱ “የአገው ተወካይ” የሚል ቢሆንም ስብሰባው ከመጀመሩ በፊት የአገው ማኅበረሰብ ተሰብስቦ ተወካይ እንደማይልክ መግለጫ አውጥቶ ነበር።
ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply