• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኦብነግ፤ ከህወሓቶች ጋር መቀመጥ በሕዝብ ደም መቀለድ ነው!

December 3, 2019 07:12 pm by Editor Leave a Comment

በቀን 10/03/2012 ዓ.ም ተፅፎ በቁጥር 07642/2019 ወጪ የተደረገው አስገራሚ ደብዳቤ ይድረስ “ለህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ፣ መቀሌ” በማለት ይጀምራል። ጉዳዩ፡- “ስለተጠራንበት ስብሰባ ይመለከታል” በማለት ይቀጥላል። የዚህን ደብዳቤ ትርጉምና ፋይዳ በቅጡ ለመረዳት የተፃፈበትን አውድ በአጭሩ መዳሰስ ያስፈልጋል።

በደብዳቤው ላይ ፊርማቸውን አኑረው የላኩት የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ-አውጪ ግንባር (ኦብነግ) ዋና ሊቀመንበር አቶ አብዲርሃማን መሃመድ ናቸው። ከላይ እንደተገለፀው ዋና ጉዳዩ ሰሞኑን በመቀሌ ከተማ እየተካሄደ ባለው ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ከህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ለቀረበላቸው ጥሪ የተሰጠ ምላሽ ነው። ህወሓት በመቀሌው ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ጥሪ ያቀረበላቸው በሥልጣን ዘመኑ በአሸባሪነት የፈረጃቸው የኦብነግ አመራሮች ናቸው።

እንግዲህ በአካባቢው ያለውን የተፈጥሮ ነዳጅ አውጥቶ ለመሸጥ ሲል የኦጋዴንን ህዝብ ከምድረገፅ ለማጥፋት ሲሰራ የነበረው፤ ለዚሁ ዓላማ አልሸባብ የተባለ ቡድንን ያደራጀው፣ በሶማሌላንድ በኩል የጦር መሣሪያ እያቀበለ በእጅ አዙር ሀገሩን ያስወረረው፣ የኢትዮጵያን ወታደሮችን ለሞት እየገበረ በፀረ-ሽብር ትግል ስም ከአሜሪካን እና እንግሊዝ ዶላር ሲቀበል፣ በሰላም አስከባሪ ስም ደግሞ ከተባበሩት መንግሥታት ይቀፍል የነበረው ህወሓት…። ከቻይና የነዳጅ አፈላላጊ ድርጅት ጋር በመሆን የተፈጥሮ ነዳጅ ለማውጣት በኦጋዴ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ የፈፀመው፣ አብዲ ኢሌ የሚባል ንክ ከኤሌክትሪክ ፖል ላይ አውርዶ የሶማሌ ክልል ፕረዜዳንት አድርጎ የሾመው፣ የሶማሌ ህዝብን ለአስራ አምስት አመታት ያህል በመከላከያ ሠራዊት እና በሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል እንደ ጠላት እያደነ ሲያስገድል የነበረው፤ ንፁሃንን ማሰርና መግደል በውስጡ ያለውን ሰይጣናዊ መንፈስ ማርካት ተስኖት እስር ቤት ውስጥ ጅብና ነብር አስሮ ሲያሰቃይ የነበረው፣… ያለ ምንም ሃፍረት፣ ፀፀት፣ ይቅርታ፣ ተጠያቂነት፣… በጠራው ስብሰባ መገኘት የሶማሌን ህዝብ ማዋረድ ነው። የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ-አውጪ ግንባር ከህወሓት ለቀረበለት የስብሰባ ጥሪ የሰጠው ምላሽ ይህንን መራራ ሃቅ እንዲህ ሲል ገልፆታል፡- 

ኦብነግ ከህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ለቀረበለት የስብሰባ ጥሪ በሰጠው ምላሽ ሊሰመርባቸው የሚገቡ ሦስት መሠረታዊ ነጥቦች አሉ። የመጀመሪያው ህወሓት ላለፉት 27 ዓመታት በሥልጣን ላይ በነበረበት ወቅት በንፁሃን ዜጎች ላይ ለፈጸመው ግፍና በደል ተጠያቂ ሊሆን ይገባል። ሁለተኛ በማንኛውም አግባብ ቢሆን ከህወሓት ጋር ትብብርና ጥምረት መፍጠር ላለፉት 27 ዓመታት ግፍና በደል በተፈፀመባቸው ዜጎች ደምና እምባ ላይ እንደመቀለድ ይቆጠራል። ሦስተኛ ከህወሓት ጋር በመተባበር የፌደራሊስቶች ግንባር ለመመሥረት በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙት ግለሰቦች እና ቡድኖች ህወሓቶች ቀድሞ በፈፀሙት እና ወደፊት በሚፈፀሙት የወንጀል ተግባር ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተሳታፊ እንደመሆናቸው መጠን ከተጠያቂነት አያመልጡም። (ኢትዮ ዊኪ ሊክስ፤ https://t.me/ethiowikileaks1)

ደብዳቤው እንዲህ ይላል፤

ተጨማሪ፤ በተያያዘ ዜና ህወሓት የፌዴራሊስት ግምባር ለመመሥረት መቀሌ ደፋ ቀና እያለ ባለበት ወቅት ከጋበዛቸው ፓርቲዎችና ቡድኖች ግማሽ ያህሉ ብቻ የተገኙ ሲሆን አንጋፋዎቹና ተስፋ የተጣለባቸው ኦፌኮ፣ ኦነግ፣ … አልተገኙም፤ ኦብነግ አለመገኘት ብቻ ሳይሆን ከዚያ ይልቅ “የምንፈልጋት ኢትዮጵያ በ2032” በሚል ርዕስ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው ሀገር አቀፍ የውይይት መድረክ ላይ ተገኘቷል።  

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ህወሓት በኦጋዴን ወገኖቻችን ላይ የፈጸመውን ግፍ አስመልክቶ ከዚህ በፊት “ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት”፤ “አንዳችሁንም አናስተርፍም፤ እንጨርሳችኋልን” የህወሃት ነፍጠኞች – በሚል ርዕስ ዘገባ አውጥቶ ነበር። ነውር ጌጡ፤ ውርደት ቀለቡ የሆነው ህወሓት ይህንን ግፍ የት አስቀምጦ ይሆን “አሸባሪ” እያለ ሲጠራው የነበረውን ኦብነግ ለስብሰባ የጠራው? ሙሉ ዘገባውን እዚህ ላይ ማንበብ ይቻላል።

ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: News Tagged With: federalist meeting, Left Column, onlf, tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
Copyright © 2026 · Goolgule