• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ዳኛውማ “ደርግ” ነው

October 11, 2020 09:00 pm by Editor 2 Comments

የመጽሐፉ ርዕስ፡ “ዳኛው ማነው?” የብርሃነ መስቀል እና የታደለች ህይወት በኢሕአፓ የትግል ታሪክ 2012 ዓ.ም. እና የብርሃነመስቀል የእሥርቤት ቃል ምርመራ ሰኔ1971 ዓ.ም.

ሙሉውን የመጽሐፍ ግምገማ ለማንበብ

እዚህ ላይ ይጫኑ

“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣበ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Filed Under: Literature, Right Column Tagged With: birhanemeskel redda, dagnaw manew, derg, eprp, tadelech, ዳኛውማነው?

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    October 16, 2020 08:17 am at 8:17 am

    በኢትዮጵያ የፓለቲካ ታሪክ ውስጥ እንደ ኢህአፓ ያለ ሁለ አቀፍ ድርጅት ተፈጥሮ አያውቅም። በአላማ ጽናት፤ በጊዜው የርዬተ ዓለም ጥንካሬ ኢህአፓን የሚስተካከል ያኔም አልነበረም አሁንም አልተፈጠረም፡፡ ላመኑበት ሞትን በዝማሬ የተቀበሉ፤ ከሞቀ ቤታቸው ለሃገር በጎ ነገርን በማሰብ በረሃ ለበረሃ የተንከራተቱ እልፍ ናቸው፡፡ አይኔ ካየው ጥቂት ልበል፡፡ በአንድ ክፍል ተኝቼ እያለሁ የማያቋርጥ ተኩስ በከተማው ይሰማል፡፡ ውሾች ይጮሃሉ፤ ተኩሱም ጋብ ይልና እንደገና ይንጣጣል፡፡ በዚህ መካከል ድንገት በድምጽ ማጉያ “ይህ የኢህአሠ ሰራዊት ነው” የሚል ድምጽ ይሰማል። ወዲያውም ከተማውን ተቆጣጥረው እኔ ወደ አረፍኩበት ሆቴል በመግባት ፍተሻ አድርገው የሚገሉትንና የሚይዙትን ይዘው ወደ መጡበት ይመለሳሉ፡፡ ደርግ ከቀን በህዋላ በመድረስ ከጫማ ጠራጊ እስከ ገበሬ ሳይቀር ያገኘውን ሁሉ መግደልና ማሰሩ ትዝ ይለኛል፡፡ ሌላ ላክል ሁለት የኢህአፓ አባል ፍቅረኞች በደርግ ይያዙና ይታሰራሉ፡፡ ያው የስመ ምርመራው ካለቀ በህዋላ ከሌሎች ጋር አብረው እንዲገደሉ ይወሰናል፡፡ ጧት ቁርስ ልበላ ወደ ከተማ ስወጣ ተቃቅፈው የወደቁ የሁለት ሰዎች ሬሳ አየሁና ተጠግቼ ቆሞ የሚጠብቀውን የቀበሌ ዘበኛ እነማን ናቸው ስለው አይ አንተ ፍቅረኞች ናቸው፡፡ ገዳዪ ስፔሻል ፎርስ እንደነገረኝ አብረን ተቃቅፈን እንሙት ብለው በመጠየቃቸው ተፈቅዶላቸው በሆዳቸው ተቃቅፈው ተኝተው ይኸው ተገለው ወድቀዋል፡፡ እንደማስታወክ አረገኝና ልበላ ያሰብኩትን ቁርስ ረስቼ ወደ ቤት ተመለስኩ፡፡ የሚገርመው ሲተኮስባቸው ስጋቸውን አልፎ መሬቱ ሁሉ መቦዳደሱ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የግፈኞች ሃገር ናት፡፡ የሚያስብላትንና የሚያሳስቧትን ለይታ አታውቅም፡፡ የሞተላት ሳይሆን የገደሏት ነው የሚጠቀሙቧት፡፡ ታዲያ ያኔ እንዲህ ነበር አሁን እንደዛ ነው እያሉ ከሞት ተራፊዎች መካከል በሃሳብ መቧቀሱ አላስፈላጊ ነው፡፡ ተጠያቂው ማን ነው ለሚለው መልሱ ቀላል ነው፡፡ ሁላችንም ነን፡፡ የሃገሪቱን ብርቅዬ ልጆች አፈር የከተተው ያ የፓለቲካ ፍትጊያ ለሻቢያና ለወያኔ በር ከፍቶ ሃገሪቱ ዛሬ በኦሮሞ ጠባብ ብሄርተኞች እንድትናጥ ለማድረጉ ማነህ ባለሳምንት አስብሎ ሰንበቴ አያስደፋም፡፡ ጉዳዪ ግልጽ ነው። ሁሉም ሰው አጥፍቷል። ግማሹ ጠቋሚ፤ ሌላው ገዳይና አስገዳይ፤ ጭራሽ የለሁበትም የሚለው ሰው እንደበግ እየተጎተተ ሲታረድ ያኔም አይቷል አሁንም እያየ ነው፡፡ ስለዚህ እንደ ጲላጦስ እጅን ታጥቦ ከነገሩ የለሁበትም ማለት ግብዝነት እንጂ እውነትነት የለውም፡፡ ለሃገሪቱ መኮታኮት ከታህሳሱ ግርግር ጀመሮ አሁን እስካለንበት ጊዜ ድረሰ በጎሳና በቋንቋ አለያም በርዪተ ኣለም ጥሪ ተሰባስበው የተፋለሙና አሁንም በመፋለም ላይ ያሉ ሁሉ አስተዋጾ አድርገዋል፡፡ አንድ ነገር ግን አልገባኝም፡፡ የቀድሞዋ ታጋይ፤ የአሁኗ አምባሳደር እንዴት ነው ከወያኔ ጋር በሃሳብ ተጣጥመው አምባሳደር መሆን የበቁት? ለእኔ ኢህአፓና ወያኔ ማዶ ለማዶ የሚተያዪ ሜዳ ላይ የተፋለሙ ጭራሽ አስታራቂ ሃሳብ በመካከላቸው የጠፋ መሆኑን ብቻ ነው የማውቀው፡፡ ለዚህ ይሆን አበው “ለሞተ ይብላኝ” የሚሉት? እልፍ ቢከፈለኝ እኔ በወያኔ ስርአት አምባሳደር አልሆንም፡፡ መጽሃፉ መጻፉ ማለፊያ ነው። ግን ዳኛው ደርግ ብቻ ነበር ብሎ መቀበል ግን ተጨፈኑና ላሞኛችሁ እንደማለት ይቆጠራል፡፡ ቆንጭራም ሆነ ከዘራ፤ በጣትም ሆነ በወረቀት የጠቆሙ፤ በምላሳቸው ሰውን በውሸት የከሰሱ፤ ገራፊዎች፤ አፋኞች የቀይ ሽብርና የነጭ ሽብር ተሳታፊዎች፤ በየጎራው በካድሬ ስም ጠበንጃ አንግተው ህዝብን ያሰቃዪ፤ በመለዪ ለባሹ ውስጥ ወታደሩንና ሃገራቸውን ለወያኔና ለሻቢያ የሸጡ፤ በደርግ ጽ/ቤት ውስጥ ሚስጢር ሲያቀብሉ የኖሩ፤ ሰዎችን በሃሰት ከሰውና አስመስክረው ሚስቶቻቸውንና ሃብታቸውን የዘረፉ ዛሬ ቆመው እኛ አላጠፋንም እነዚያ ናቸው የሚሉ ሁሉ በድኖች ናቸው፡፡ የቁም ሙታኖች ሴራና ተንኮል ድምር ውጤት ነው ዛሬ ሃገሪቷ ፍርክርኳ እንዲወጣ ያደረጋት፡፡ የነገውንም በውል የሚያውቅ የለም፡፡ በቃኝ!

    Reply
  2. ዘረ-ያዕቖብ says

    October 22, 2020 09:46 am at 9:46 am

    Tesfa፣
    ያወሳሄው የቅርቡ ጊዜ ታሪካችን የሚየንገበግብና የሚያንሰፈስፍ ነው:: በመደምደምያህ ላይ ስለ ነገ ያወሳሄውን አስመልክቶ ግን፣ ዛሬ ነገን አርግዛ ትጓዛለች እንዲሉት ነውና፣ የዛሬ አስተሳሰባችንና ተግባራችን ነገን ይወስናል!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule