በሰሜን ኢትዮጵያ በድጋሚ ግጭት ለመቀስቀስና ቀጣናዊ ሰላምን ለማደፍረስ ከሻዕቢያ ጋር ጽምዶ ፈጥሮ አደገኛ እንቅስቃሴ ላይ በሚገኘው ትህነግ (ህወሃት) አመራሮችና በቅርብ የቤተሰብ አባላቶቻቸው ላይ ያነጣጠረ የቪዛ እገዳ መጣሉን ተከትሎ የአሜሪካ መንግስት በይፋ አስታውቋል። ይህ ውሳኔ ይፋ የሆነው በኢትዮጵያ ውስጥ በሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ የመንቀሳቀስ ፍቃዱ የተሰረዘውና ሕገወጥ ተብሎ የተፈረጀው የትህነግ ታጣቂ ኃይል ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በቅርቡ በፈጠረው ቀጥተኛ የጦርነት ትንኮሳ ሳቢያ ነው። ትህነግ በተደጋጋሚ በቆሰቆሰው የሰሜኑ ጦርነት አንድ ሚሊዮን ያህል የንጹሃን ዜጎች ህይወት መጥፋቱ እንዲሁም በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወገኖች ለከፋ ረሃብና ለስደት መዳረጋቸው እየታወቀ ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር ብሎ የሚጠራው አሸባሪ አሁንም ለሰላም እያሳየ ያለው … [Read more...] about አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ

