በበርካታ ጉዳዮች መጨመላለቅ፣ ቧልት መጫወት፣ መደለል፣ በማህበራዊ ሚዲያ እንጭጭ አሳቢዎች አማካይነት ድራማ መስራት፣ ተቧድኖ ማሴር፣ እዛም እዚህም ሹመኛ ላይ እየተንጠላጠሉ፣ የተለያዩ ህጋዊ ተቋማት ውስጥ እየተወሸቁ ወዘተ እያስፈራሩም ጭምር ውንብድና መፈጸም እና የቴሌኮም ኔትዎርኮችና የዳታ መጋዘኖች ዙሪያ የሚደረግ ቁማር ተመሳሳይ እንደሆኑ አድርገን የምናስብ ካለን አልገባንም። ገብቶንም ዝምታን የመረጥን ካለን “ኢትዮጵያዊ” ልንባል አንችልም። ተቆጣጣሪ አካል ሆነን ቸል የምንል ካለን ጣጣው “በዘመቻ/ኦፐሬሽን” የሚታፈስ አይደለም። ይህን አስተያየት ለመጻፍ ያነሳሳኝ ከላይ በርዕሱ እንደጠቆምኩት፣ ጉዳዩ ከንትርክም፣ ከመካሰስም፣ ከቲፎዞ ጩኸትና ከችሎት ጀርባ ባለ ማመቻመች፣ እንዲሁም ሴራ የሚዘጋ አጀንዳ በመሆኑ ነው። እንደ መግቢያ የአንድ ሀገር የቴሌኮም መሠረተ ልማት፣ ዓለም … [Read more...] about የቴሌኮም ጌትዌይ፣ የዳታ ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ደህንነት – የዌብስፕሪክስ ጉዳይ ከባለቤትነት ክርክር በላይ ነው!
abraham minwuyelet
ሻርኮቹ ከውጭ እስከ ሀገር ውስጥ ያደሩት ድር፣ ዌብስፕሪክስን (WebSprix) የመጠቅለሉ ድራማና ብሔራዊ ስጋት
በሻርክ የሚሰየሙ አደገኛ ማፊያዎች ወይም በሳይበር ደህንነት ዓለም "Scattered Spider, Silence" ወይም በፋይናንሺያል እና ሳይበር ወንጀል ከሚታወቁ አደገኛ የጠላፊዎች/የወንጀለኞች ቡድኖች ጋር የሚመሳሰሉ—የአንድን ሀገር የቴሌኮም መሠረተ ልማት፣ የጌትዌይ (Gateway) መቆጣጠሪያዎች እና የዳታ ማዕከላት (Data Centers) ቢቆጣጠሩ የሚያስከትሉት አደጋ እጅግ ከፍተኛ እና ሀገራዊ ደህንነትን እስከማናጋት የሚደርስ ነው። ይህን የጠቀስኩት የፋይናንስ ተቋም ያላቸውን ከታች የምጠቁማቸውን ሰዎች በዚህ ማዕቀፍም እንድታዩዋቸው ነው። እንዲህ ያለው ቅዠት ቢሳካ ሻርኮቹ መጠነ ሰፊ ጉዳት የሚያደርሱ ቢሆንም ለዛሬ ጠላፊዎቹ ከባንክ ሲስተሞች ጋር የተገናኙ የቴሌኮም መተግበሪያዎችን በመጠቀም በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ወደ ውጭ ሀገራት ሕገ-ወጥ ዝውውር ሊያደርጉ እንደሚችሉና … [Read more...] about ሻርኮቹ ከውጭ እስከ ሀገር ውስጥ ያደሩት ድር፣ ዌብስፕሪክስን (WebSprix) የመጠቅለሉ ድራማና ብሔራዊ ስጋት


