በበርካታ ጉዳዮች መጨመላለቅ፣ ቧልት መጫወት፣ መደለል፣ በማህበራዊ ሚዲያ እንጭጭ አሳቢዎች አማካይነት ድራማ መስራት፣ ተቧድኖ ማሴር፣ እዛም እዚህም ሹመኛ ላይ እየተንጠላጠሉ፣ የተለያዩ ህጋዊ ተቋማት ውስጥ እየተወሸቁ ወዘተ እያስፈራሩም ጭምር ውንብድና መፈጸም እና የቴሌኮም ኔትዎርኮችና የዳታ መጋዘኖች ዙሪያ የሚደረግ ቁማር ተመሳሳይ እንደሆኑ አድርገን የምናስብ ካለን አልገባንም። ገብቶንም ዝምታን የመረጥን ካለን “ኢትዮጵያዊ” ልንባል አንችልም። ተቆጣጣሪ አካል ሆነን ቸል የምንል ካለን ጣጣው “በዘመቻ/ኦፐሬሽን” የሚታፈስ አይደለም። ይህን አስተያየት ለመጻፍ ያነሳሳኝ ከላይ በርዕሱ እንደጠቆምኩት፣ ጉዳዩ ከንትርክም፣ ከመካሰስም፣ ከቲፎዞ ጩኸትና ከችሎት ጀርባ ባለ ማመቻመች፣ እንዲሁም ሴራ የሚዘጋ አጀንዳ በመሆኑ ነው። እንደ መግቢያ የአንድ ሀገር የቴሌኮም መሠረተ ልማት፣ ዓለም … [Read more...] about የቴሌኮም ጌትዌይ፣ የዳታ ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ደህንነት – የዌብስፕሪክስ ጉዳይ ከባለቤትነት ክርክር በላይ ነው!

