ሳይዋጋ የሚያሸንፍ ጠንካራ የመከላከያ ሰራዊት እየገነባን ነው የመከላከያ ሠራዊት ቀንን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ "የጥንካሪያችን ምንጭ ሕዝባችን ነው" በሚል መልዕክት የፓናል ውይይት ተካሄደ። በመርሃ ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር አብርሐም በላይ (ዶክተር)፣ አሁን በኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ግንባታ ከፍተኛ አቅም ተፈጥሯል፤ ከሩቁ የሚፈራ መከላከያ ሠራዊት ፈጥረናል ብለዋል። የኢትዮጵያ ጠላቶች ሳንቆም ሊጥሉን ሞክረዋል፤ አሁን ቆመን ማንም ሊነቀንቀን የማይችልበት ደረጃ ደርሰናል ያሉት ሚኒስትሩ፣ በአሁኑ ጊዜ ሳይዋጋ የሚያሸንፍ ሠራዊት መገንባት መቻሉን አንስተዋል። ኢትዮጵያ የግዛት አንድነቷ በማንም እንደማይሸረፍ በመስዋዕትነት የሚያረጋግጥ ጀግና ወታደር ያላት ሀገር እንደሆነች የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ይህን በተግባር እያረጋገጠ … [Read more...] about “ከሩቁ የሚፈራ የመከላከያ ሠራዊት ፈጥረናል”
Slider
ከ፴ ዓመት በኋላ በሰፈሩት ቁና መሰፈር እንደ ትህነግ
አደራውን ለባለ አደራው ሰጥተው የልማት ሥራዎችን እየተዘዋወሩ የሚመለክቱትና የአረንጓዴ ዘመቻ መመሪያ እየሰጡ ያሉ ዐቢይ አሕመድ ከአዲሱ ዓመት ጀምሮ የወትሮ ጭንቀትና ያለመመቸት ስሜት ፊታቸው ላይ አይታይም። በመንግሥት የዘመኑ ዕቅድ ላይም በተያዘው ዓመት አስተማማኝ ሰላም እንደሚሰፍን ተመልክቷል። ዐቢይ አህመድ ለበዓላት ባስተላለፉት መልዕክቶቻቸውና በፕሮጀክት ምረቃ ላይ “አትጠራጠሩ የሰሜኑ ጦርነት ያበቃል” ብለዋል። “አሁን” ሲሉ መረጃ የሰጡ ወገኖች “አሁን የሰኞው ንግግር ልክ እንደ 1991ዓም (እኤአ) ድርድር ዋጋ የለውም። ምክንያቱም የትህነግ አመራሮች ጊዜ የሚፈጁበት አንዳችም የድርድር ቀብድ የላቸውም”። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ቴድሮስ አድሃኖም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ደውሎ መማጸኑ ተሰምቷል። ምላሽም አግኝቷል። ከመቀሌ ውጪ ቀሪዋ ትልቅ ከተማ አዲግራትና አድዋ … [Read more...] about ከ፴ ዓመት በኋላ በሰፈሩት ቁና መሰፈር እንደ ትህነግ
“ትህነግን ለማጥፋት የሚደረግ ማንኛውም ነገር ቅዱስ ነው”
የትህነግ 10 በደሎች - በተለይ በአማራ ሕዝብ! "ትህነግ"... (ትግራይ/ተጋሩ አላልሁም) የተሸነፈው በ1967 ነው። ማንም ቡድን ወይም ርዕዮተ አለም ሕዝብን ጠላት አድርጎ ማሸነፍ አይችልም። ግለሰቦች፣ የፊውዳሉ ስርዓት ጠላት ሊሆን ይችላል። ሁሉም አማራ ግን ጠላት ሊሆን አይችልም። ትህነግ እንጂ የትግራይ ሕዝብ ጠላት እንዳልሆነው ሁሉ። የትህነግ መሠረታዊ ትርክት (ድርሰት) በገሃድ የተተወነው ባለፈው ዓመት ነው። ትህነግ በተለይ በአማራ ሕዝብ 10 ዐበይት በደሎች ፈፅሟል። በእኔ ሚዛንና ምልከታ። 1) መልክዓምድራዊ ለውጥ (Demographic Change): ድህረ 1983 ማንነትን ባላገናዘበ መልኩ ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ዋግና ራያ ላይ መሬቱን በመውረር ሰዎችን አፈናቅሎል፣ ጅምላ ግድያ ፈፅሟል። ሴቶችን በመድፈርና አስገድዶ በማግባት የዲሞግራፊ … [Read more...] about “ትህነግን ለማጥፋት የሚደረግ ማንኛውም ነገር ቅዱስ ነው”
“አበበ እንጂ መቼ ሞተ!”
በአሜሪካ ኦሪጎን ጠቅላይ ግዛት እየተካሄደ ባለው የሰሞኑ የአትሌቲክስ ኢትዮጵያ እንደገና ስሟ ከፍ ብሏል። በፖለቲካው የሚታየው መከፋፈልና ጥላቻ በስፖርቱ አከርካሪውን ተመትቷል። የዚህ ድል ምንጭ ምንድነው? ብለን ወደ ኋላ እንድናይ ያስገድደናል። ተወዳዳሪ የሌለው ወደፊትም የማይኖረው የጀግኖቹን ጀግና አበበ ቢቂላ ማስታወስ የግድ ይላል። አበበ ሮም ላይ በባዶ እግሩ ሲያሸንፍ የዓድዋ ድል ነው በድጋሚ የተበሰረው። ጣሊያኖቹም ይህንን አልካዱም። የክብር ዘበኛው ወታደር አበበ ሲያሸንፍ “ሮምን የወረረ ኢትዮጵያዊ” ብለው ዘግበውለታል። “ጣሊያን ኢትዮጵያን ለመውረር ግዙፍ ጦር አዝምቶ ነበር፤ ሮምን ለመውረር ግን አንድ ኢትዮጵያዊ ወታደር ብቻ በቂ ሆኗል” በማለትም አትተዋል። እነ ማሞ ወልዴና እነባሻዬ ፈለቀ “ኢትዮጵያ” የሚል ቱታ ለብሰው ሲያይ ለአገሩ ተሰልፎ ስሟን ማስጠራት … [Read more...] about “አበበ እንጂ መቼ ሞተ!”
ሸኔ አመራሮቹንና ጠንካራ ይዞታዎቹን እያጣ ነው
በተለይ ምዕራብ ወለጋን ምሽጉ አድርጎ ከትህነግ ጋር በመሆን ንጹሐንን እየጨፈጨፈ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚሞክረው ሸኔ ጠንካራ ይዞታዎቹን እያጣ መሆኑ ተነገረ። ሸኔን የማጽዳት ዘመቻው ወደ ፖለቲካውና መንግሥታዊ መዋቅሩም ውስጥ በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥል ተጠየቀ። ጎልጉል ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በአሁኑ ጊዜ በተጠናከረ ሁኔታ በሸኔ ላይ እየተካሄደ ባለው ዘመቻ ኦነግ ሸኔ ጠንካራ የሚላቸውን ይዞታዎቹን ሳይወድ በግዱ እንዲለቅ እየተደረገ ነው። በተለይ በቅርቡ በምዕራብ ወለጋ በንጹሐን ወገኖቻችን ላይ አሰቃቂና ለኅሊና የሚሰቀጥጥ ግድያ በፈጸመው ሸኔ ላይ አሁን ዝርዝሩን መናገር የማያስፈልግ ዘመቻ እየተካሄደበት ይገኛል። በቀጣይ ባሉት ቀናት መንግሥት በይፋ ዝርዝሩን የሚያሳውቅ ቢሆንም ዘመቻው በዋንኛነት ትኩረት ያደረገው የሸኔን ጠንካራ ምሽጎችን … [Read more...] about ሸኔ አመራሮቹንና ጠንካራ ይዞታዎቹን እያጣ ነው
“አድጌ እንደናንተ መሆን እፈልጋለሁ”
መከላከያ ሰራዊታችን በውጊያ ወቅት ሀገርና ህዝብ የሰጠውን ተልዕኮ በጀግንነትና በድል ለመወጣት ሀሩር እና ብርዱ ሳይበግረው በየተራራው በየጥሻው ድንጋይ ተንተርሶ ሙቀቱን በላቡ ዝናቡን በሰውነቱ ሙቀት እየተቋቋመ ግዳጁን በድል ይወጣል። አንፃራዊ ሰላም ባለበት ደግሞ በደረሰበት ቦታ ሁሉ ህዝባዊ ሰራዊትነቱን በተግባር ያሳያል። ካለው የዕለት ጉርሱ ቀንሶ ለተቸገሩ ወገኖች ያካፍላል። በጉልበቱም በገንዘቡም ይረዳል። በምዕራብ ዕዝ በሚገኝ ክ/ጦር ሁለተኛ አባይ ሬጅመንት የሆነው እንዲህ ነው። ህፃን አማኑኤል ሽፈራው ይባላል። የ11አመት ታዳጊ ሲሆን ተወልዶ ያደገው በሰሜን ጎንደር አድዓርቃይ ወረዳ አምበራ አካባቢ ልዩ ስሙ አዲስ አለም በሚባል ሰፈር ነው ። ህፃን አማኑኤል እንደሚለው እናቴ ትግራይ ለስራ እንደሄደች አልተመለሰችም። አባቴን አላውቀውም። ከአጎቴ ጋር ነበር … [Read more...] about “አድጌ እንደናንተ መሆን እፈልጋለሁ”
የጥቁር አንበሳ ዕጩ መኮንኖች (ካዴቶች) ተመረቁ
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ ለ69ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን “የጥቁር አንበሳ” ዕጩ መኮንኖችን አስመረቀ። ተመራቂዎቹ “የጥቁር አንበሳ” መባላቸው በምዕራባዊያንና በውስጡ ነበሩ በተባሉ “ካሃዲዎች” የተበተነውን ታላቁን የኢትዮጵያ መከላከያ ያስታወሰ መሆኑ ልዩ ስሜት የሚሰጥ እንደሆነ ምርቃቱን ተከትሎ አስተያየት ተሰጥቷል። “ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም በሚል ቁጭት ነው ኢትዮጵያን የሚመጥን የመከላከያ ኃይል ለመገንባት እየሠራን ያለነው” በማለት የጦር ኃይሎች ም/ጠ/ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ በተናገሩ ማግስት፣ አዳዲስ መኮኖች መመረቃቸው፣ ጀነራሉ በንግግራቸው የሚገነባው ኢትዮጵያን የሚመስልና የሚመጥን ሰራዊት ዘመናዊና ቴክኖሎጂን የተላበሰ፣ በምሁራን የተገነባ እንደሚሆን ካመላከቱት ጋር ተያያዥ ሆኗል። ተመራቂዎቹ የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ ያላቸው፣ በራሳቸው ተነሳሽነት ከሲቪል … [Read more...] about የጥቁር አንበሳ ዕጩ መኮንኖች (ካዴቶች) ተመረቁ
መከላከያ በተጨማሪ ድሮን፣ በሥልጠና፣ በዝግጅት ራሱን አብቅቷል
ከመካከለኛው ምስራቅ አካባቢ የሚሰሙ ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት ኢትዮጵያ ከትህነግ ጋር ወደ ዳግም ጦርነት ልትገባ እንደምትችል ጠቁመዋል። ትህግም ለውጊያ እየተዘጋጀሁ ነኝ ሲል ተሰምቷል። ኤርትራ ደግሞ በሩሲያ ሠራሽ ድሮኖች ራሷን አጠናክራለች። ከተለያዩ የዜና ምንጮች ለመገንዘብ እንደሚቻለው የኢትዮጵያ መካላከያ ሠራዊት አዲስ የማጥቃት ዘመቻ ሊጀምር ይችላል እየተባለ ነው። ለዚህም ይረዳ ዘንድ ኢትዮጵያ አዳዲስ ድሮኖችን ጨምሮ ተጨማሪ ተዋጊ ጀቶችን ወደ አገር ቤት በዚህ ማስገባቷ ተሰምቷል። ቱርክ ሰራሹ ባይራክ 32 ድሮን እና ተጨማሪ ጀቶች ወደ አዲስ አበባ ሳይገቡ አልቀረም። ከዚህ በፊት በተለያየ ዙር ሲሰለጥኑ የኖሩና በመጀመሪያው የክተት አዋጅ፣ የተመዘገቡ ወታደሮች እስካሁን ማስልጠኛ ካምፕ ውስጥ ቆይተው ሰሞኑን ወደ ወደ ተለያየ ክልል በተለይም ወደ አማራ ክልል ገብተዋል። … [Read more...] about መከላከያ በተጨማሪ ድሮን፣ በሥልጠና፣ በዝግጅት ራሱን አብቅቷል
ትህነግ ለሌላ ውጊያ እየተዘጋጀ ነው ተባለ
ትህነግ ለሌላ አውዳሚ ጦርነት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሀይል እየመለመለ መሆኑን አንድ ዓለም አቀፍ ጋዜጠኛ አጋለጠ። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጉዳዩን በሚገባ ተገንዝቦ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት መወጣት እንዳለበትም ገልጿል። በአሸባሪው ትህነግ ጠብ አጫሪነት በተቀሰቀሰው ጦርነት ከፍተኛ ጉዳት በደረሰባቸው የሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች ጉብኝት ያደረገው "የስኩፕ ኢንዲፔንደንት ዜና" ዋና ኤዲተር አላስቴየር ቶምሶን፤ የአሸባሪው ትህነግ ዋነኛ ፍላጎት ዳግም ጦርነት መቀስቀስ መሆኑን ከኢዜአ ጋር በነበረው ቆይታ ገልጿል። የሽብር ቡድኑ ከዚህ ቀደም በርካቶችን በጦርነት በመማገድ ለሞት መዳረጉን አስታውሶ፤ ቡድኑ አሁንም ተመሳሳይ ተግባር ለመድገም እየተዘጋጀ ስለመሆኑ ነው የተናገረው። ለዚህ ደግሞ በርካታ ቁጥር ያላቸውን ተዋጊዎች እየመለመለና እያሰለጠነ መሆኑን በአስረጂነት … [Read more...] about ትህነግ ለሌላ ውጊያ እየተዘጋጀ ነው ተባለ
ከሽፏል!
የአሜሪካ ኮንግረስ እና ሴኔት HR6600/S3199 ሕግ ሆኖ እንዲፀድቅ የቀረበው የውሳኔ ኃሳብ እንዲቋረጥ ወሰነ። HR6600 እና S3199 ረቂቅ ሕጎች ሕግ ሆነው ከመውጣት እንዲዘገዩ የአሜሪካ ኮንግረስ እና ሴኔት ውሳኔ ላይ መደረሱን የኢትዮጵያ አሜሪካ ሲቪክ ካውንስል በትዊተር ገጹ አስታውቋል። ረቂቅ ህጉ እንዲቋረጥ ለጊዜው ከስምምነት የተደረሰበት ውሳኔ በቀጣይም ህግ ሆነው እንዳይፀድቁ ኢትዮጵያውያን እያደረጉት ያለው የዲፕሎማሲ ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ካውንስሉ አሳስቧል። የኢትዮጵያ አሜሪካ ሲቪክ ካውንስል በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን ጣልቃ ገብነትና ጫና በመቃወምና ዳያስፖራ ማህበረሰቡን ጭምር በማስተባበር ከፍተኛ የህዝብ ዲፕሎማሲ ስራ በመስራት ላይ ያለ መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገ ተቋም ነው። (AMN) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ከሽፏል!