መከላከያ ሰራዊታችን በውጊያ ወቅት ሀገርና ህዝብ የሰጠውን ተልዕኮ በጀግንነትና በድል ለመወጣት ሀሩር እና ብርዱ ሳይበግረው በየተራራው በየጥሻው ድንጋይ ተንተርሶ ሙቀቱን በላቡ ዝናቡን በሰውነቱ ሙቀት እየተቋቋመ ግዳጁን በድል ይወጣል። አንፃራዊ ሰላም ባለበት ደግሞ በደረሰበት ቦታ ሁሉ ህዝባዊ ሰራዊትነቱን በተግባር ያሳያል። ካለው የዕለት ጉርሱ ቀንሶ ለተቸገሩ ወገኖች ያካፍላል። በጉልበቱም በገንዘቡም ይረዳል። በምዕራብ ዕዝ በሚገኝ ክ/ጦር ሁለተኛ አባይ ሬጅመንት የሆነው እንዲህ ነው። ህፃን አማኑኤል ሽፈራው ይባላል። የ11አመት ታዳጊ ሲሆን ተወልዶ ያደገው በሰሜን ጎንደር አድዓርቃይ ወረዳ አምበራ አካባቢ ልዩ ስሙ አዲስ አለም በሚባል ሰፈር ነው ። ህፃን አማኑኤል እንደሚለው እናቴ ትግራይ ለስራ እንደሄደች አልተመለሰችም። አባቴን አላውቀውም። ከአጎቴ ጋር ነበር … [Read more...] about “አድጌ እንደናንተ መሆን እፈልጋለሁ”