እኤአ በፌብሩዋሪ 2014 በ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ወደ ሥልጣን የመጣውንና ምርጫው “ደህንነትና ትብብር ድርጅት” (OSCE Organization for Security and Cooperation) በተሰኘው ዓለምአቀፋዊ ድርጅት የጸደቀው የዩክሬን መንግሥት በመፈንቅለ መንግሥት ተወገደ። ፕሬዚዳንቱ ቪክቶር ያኑኮቪች ሕይወታቸውን ለማዳን ከአገር ለቅቀው ወጡ። መፈንቅለ መንግሥቱ የተቀነባበረው በተለይ በአሜሪካ ባልሥልጣናት ነው። ትውልደ ዩክሬን የሆነችውና በወቅቱ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአውሮጳና ዩሬዢያ ረዳት ጸሐፊ የነበረችው ቪክቶሪያ ኑላንድ የሤራው ዋና አቀናባሪ ነበረች። አብሯት ሟቹ ሴናተር ጆን ማኬይን ሠርቷል። ፕሬዚዳንት ያኑኮቪችን ከሥልጣን ለማስወገድ ቪክቶሪያ ራሷ ከማስተባበር ባለፈ ሰላማዊ ሰልፍ የሚወጡትን ዩክሬናውያንን ከመደገፍ አልፋ ለሰልፈኞች ብስኩት ስታድል በወቅቱ … [Read more...] about “ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች” እየተባለ ስለሚነዛው ወሬ ጥቂት እውነታዎች
Slider
“ምኒልክ ዛሬም ንጉሥ ነው!”
የዓለም ህዝብ ሁሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ነጭን ድል ያደረገውን የጥቁር ጦር መሪ አጤ ምኒልክን ለማወቅ እጅግ ጓጓ፡፡ ምስላቸውን ለማየት ተቁነጠነጠ፡፡ ሙሉ ታሪካቸውን ለመስማት ተንሰፈሰፈ፡፡ ይህንኑ ተከትሎም፤ “እንኳንም ደስ አለዎት” ለማለት ከቁጥር የበዙ ደብዳቤዎች ይጎርፉላቸው ነበር፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ በፖስታ ቤት በኩል የኢትዮጵያ ቴምብር የተለጠፈበት መልስ እንዲላክላቸው ይጠይቁ ነበር፡፡ ለምን… ? ቴምብሩ ላይ ያለውን የምኒልክን መልክ ለማየት፡፡ ባለ ብዙ ዝናና ክብር ባለቤት የሆኑትን የምኒልክን ጥቁር ፊት ለማየት፡፡ የሰው ሀገር ሰው ሁሉ፤ “ዝናውን እንደሰማሁ መቼ ሄጄ ባየሁት”፣ “በጀግንነቱ እንደ ተማረኩ መች ተጉዤ ባገኘሁት”፣ “ካሁን ካሁን ፈቅዶልኝ ወታደር ሆኜ ባገለገልኩት” ያለላቸው አጤ ምኒልክ የኛ ናቸው፡፡ በዓለም ታሪክ … [Read more...] about “ምኒልክ ዛሬም ንጉሥ ነው!”
ትህነግንና ሸኔን በአፍሪካ ደረጃ አሸባሪ አድርጎ ለማስፈረጅ እየተሠራ ነው
ድልድይ በማፍረስ፤ መሠረተ ልማቶችን በማውደም ከየቦታው በተለቃቀሙ ወንበዴዎች መሪነት ኢትዮጵያን በ“ነጻ አውጪ” ስም በግፍ ሲገዛ የነበረው ትህነግ በአፍሪካ በትክክለኛ መጠሪያ ስሙ ሊጠራ ዝግጅት ላይ መሆኑ ተሰማ። ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት/ትህነግ) በማለት የሚጠራውና በኢትዮጵያ እጅግ አስከፊ የሚባልና ትውልድን ያወደመ ርዕዮት በመከተል አገር ያፈረሰው የወንበዴዎች ጥርቅም፤ እስካሁንም በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት በአሸባሪነት ተመዝግቦ የሚገኝ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል። አባላቱና ደጋፊዎችም በዚሁ ሁኔታ የሚታዩ መሆናቸውን ብዙዎች የሚስማሙበት ነው። ህወሓትና ተላላኪዎቹ በአሸባሪነት እንዲሰየሙ ተጠየቀ አሸባሪው ህወሓት በሕገወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር በሕግ መታገድ፤ መሪዎቹም በኃላፊነት መጠየቅ አለባቸው አሸባሪው … [Read more...] about ትህነግንና ሸኔን በአፍሪካ ደረጃ አሸባሪ አድርጎ ለማስፈረጅ እየተሠራ ነው
ለሶማሊ ክልል በስዬ አብርሃ የታሰበው “ፕሮጀክት X” ምሥጢር ሲገለጥ
የትግራይ ተወላጁ ሰለሞን ዘነበ በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ውስጥ ባለ ውድ ሆቴል ተንደላቆ የሚኖር የህወሃት ቁልፍ ሰው ነው። ቁልፍነቱ የሚመነጨው ደግሞ ጁንታው ስዬ አብርሃ በእናቱ ወገን አጎቱ በመሆኑ ሲሆን ይህ ሰው ለቀድሞዋ የህፃናት ሚኒስትር ፊልሰን እና የሲአይኤ ኬንያ ወኪል ነኝ ባዩ አህመድ ባጄን ጨምሮ ለህወሃት ደጋፊ ሶማሌዎች ገንዘብ በማስተላለፍ በሶማሌ ክልል ሊተገበር ለታቀደው የህወሃት የጥፋት ሴራ መንገድ ጠራጊ ነው። ባለፈው ሳምንት ሃርጌሳ ታይቶ የነበረው ሰለሞን በቆይታው በሶማሌ ክልል ውስጥ የከተማ ውስጥ ሁከት እና ረብሻ እንዲያስነሱ ለተቀጠሩ ወንጀለኞች ገንዘብ እንዳሰራጨ የታወቀ ሲሆን (የገንዘብ ዝውውር የሚያሳይ ሚስጥራዊ መረጃ የደረሰን ሲሆን አስፈላጊ በሆነ ግዜ ይፋ የሚደረግ ይሆናል) ነገር ግን ከተመደበልን ገንዘብ ቀንሶብናል ያሉና በገንዘብ ክፍያ … [Read more...] about ለሶማሊ ክልል በስዬ አብርሃ የታሰበው “ፕሮጀክት X” ምሥጢር ሲገለጥ
ከዕቅዱ የጨነገፈውና በሶማሊ ክልል ተሸርቦ የነበረው ሤራ
“የፌደራል መንግስት ፈርሷል። የትህነግ ወራሪ ሃይል አዲስ አበባ ዙሪያ ከቧል። ራሳችሁን አድኑ። የውጭ ተቋማትና ዲፕሎማቶች አገር ለቃችሁ ውጡ። የመንግስት ባልስልጣናትም ቪዛ ተመቻችቶላችኋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም ወደ አረብ ኢምሬትስ ሊበሩ ነው …” አሜሪካ መራሹ የፕሮፓጋንዳ ሃይል በተከታታይ፣ በዕቅድ፣ በመናበብ፣ በመቀባበል ሲያውጁት የነበረው የሞት አዋጅ ነበር። “ከማን ጋር ነው ድርድሩ? መንግስት ሞቷል” የሚለውና ከክህደት ቢላዋ ተርፎ አገሩን የታደገውን የአገር መከላከያ ዳግም በትኖ ለማኝ ለማድረግ” የብልጽግና ወታደሮች እጃችሁን ለትግራይ ነጻ አውጪ ስጡ። የሚያድናችሁ ምድራዊ ሃይል የለም። ጊዜ አታባክኑ። የትግራይ ነጻ አውጪ ሰራዊት እርምጃ ሳይወስድባችሁ …” ይህ ደግሞ ከዋና አሜሪካ መራሹ ፕሮፓጋንዳ ስር የሚርመጠመጠው የከሃጂዎች ስብስብ ጩኸት ነበር። በክህደት … [Read more...] about ከዕቅዱ የጨነገፈውና በሶማሊ ክልል ተሸርቦ የነበረው ሤራ
“የዛሬዋ ኢትዮጵያ አይደለም የትላንትናውን ትህነግ የዘመነውን ትህነግ ለመቀበል አትችልም” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ
* "በወሎ ግንባር በነበረው ውጊያ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ኃይሎች ተሳትፈዋል" * የ፷፪ ዓመት ሽማግሌ ከትግራይ ለትህነግ ዘምቷል በወሎ ግንባር በነበረው ውጊያ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ኃይሎች ከአሸባሪው ቡድን ጋር መሳተፋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በጦርነቱ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ እና የኢትዮጵያውያ ዝርያ የሌላቸው ነጮች እና ጥቁሮች ከአሸባሪው ቡድን ጋር ተሳትፈው መስዋትነት መክፈላቸውን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያረጋገጡት። “በወሎ ግምባር በነበረው ውጊያ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ኃይሎች ተሳትፈውበታል። የኢትዮጵያ ዝርያ የሌላቸው ሰዎች ተሳትፈው መስዋዕትነት ከፍለዋል። ኢትዮጵያዊ ያልሆነ ሰው ኢትዮጵያ መጥቶ በደሴ … [Read more...] about “የዛሬዋ ኢትዮጵያ አይደለም የትላንትናውን ትህነግ የዘመነውን ትህነግ ለመቀበል አትችልም” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ
ደሴ በወገን እጅ – መከላከያ እየገፋ ነው!
ደሴን ለመውረር አሰፍስፎ የነበረ አሸባሪው የህወሃት ወራሪ ኃይል አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቷልበወሎ ዩኒቨርሲቲ ፎቶ ለመነሳት ገብቶ የነበረ የጥፋት ቡድኑ ፎቶ ናፋቂም ባለበት አፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ እስከወዲያኛው ተሸኝቷልየደሴ ከተማና አካባቢዋን ተቆጣጥረናል በማለት ጮኸው የሚያስጮሁ የወራሪው ወሬ አራጋቢዎችም በስፍራው እየተፋለሙ የሚገኙትን የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ወኔና ጀግንነት አልተረዱም ልዩ መረጃ፤ ከጥቂት ደቂዎች በፊት ጎልጉል እንዳረጋገጠው ደሴን ያረጋጋው መከላከያ ሠራዊት፣ ልዩ ኃይል፣ ሕዝባዊ ሚሊሻና ፋኖ በርካታ አካባቢዎችን እየተቆጣጠረና በወገን እጅ ሥር እያደረጋቸው ይገኛል። በዚህም ጠላት በከፍተኛ ሁኔታ እየተደመሰሰና እየሸሸ እንደሆነ ለማረጋገጥ ችለናል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ መንግሥት የትግራይ ሕዝብ ላለቁት ልጆቹ ትህነግን ለመጠየቅ እንዲዘጋጅ … [Read more...] about ደሴ በወገን እጅ – መከላከያ እየገፋ ነው!
ስድስተኛው የአየር ጥቃት ተደርጓል፤ አየር ኃይሉ ብቃቱን አስመስክሯል
ዛሬ መቀሌ ኵሃ አካባቢ የሚገኘው የልዩ ኃይል ፖሊስ ማሠልጠኛ ተቋም በአየር ኃይል ተመቷል። ይህ ተቋም በአሁኑ ወቅት በርካታ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች እየሰለጠኑበት ያለ ተቋም መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል። በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ የተጠኑና ወራሪው ሽብርተኛው ህወሓት ወያኔ መሳሪያ በማከማቸት የጦር ስልጠና የሚሰጥበት ቦታ ላይ የኢትዮጵያ አየር ሀይል ለ6 ተኛ ዙር ዛሬ የአየር ጥቃት አድርሷል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ባደረጋቸው የአየር ጥቃቶች ኢላማውን አግኝቶ መምታቱና የጠላትን ወታደራዊ ይዞታዎችን ለይቶ ከጥቅም ውጪ ማድረጉ ስኬታማነቱንና በቂ ሥልጠና እንዳለው እንደሚያሳይ የቀድሞ ሠራዊት አባል ብርጋዴር ጀነራል መስፍን ኃይሌ ገለጹ። ብርጋዴር ጀነራል መስፍን በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ አየር … [Read more...] about ስድስተኛው የአየር ጥቃት ተደርጓል፤ አየር ኃይሉ ብቃቱን አስመስክሯል
CNN ትህነግን እንደ ማስረጃ ጠቅሶ የሠራው ዘገባና ያፈተለከው ቅሌት
ሲኤንኤን (CNN) “አሰቃቂው ዕይታ” የሚል ርዕስ የሰጠውን እና በሁመራ ተፈፅሟል ያለውን ግርፋት፣ ጅምላ እስር እና ግድያን በተመለከተ የምርመራ ዘገባ አቅርቧል። እነዚህ ግርፋት፣ ጅምላ እስር እና ግድያ የተፈፀሙት “በኢትዮጵያ ሠራዊት እና አጋሮቹ” ሲል በገለጻቸው ኃይሎች መሆኑንም ምስክሮቹን ጠቅሶ ደምድሟል። የዚህ የምርመራ ዘገባ መነሻ የሆነው በሱዳን ድንበር አካባቢ በሚገኝ ወንዝ ላይ የሚንሳፈፉ አስከሬኖች ዳግም መገኘታቸው እንደሆነ ሚዲያው ጠቅሷል። ኒማ ኤልባጊር ይሁን እንጂ የዘገባው አዘጋጅ የሆነችው ሱዳናዊቷ ጋዜጠኛ ኒማ ኤልባጊር ለምስክርነት የመረጠቻቸው ሰዎች ገለልተኛ አለመሆን እና የአሸባሪው ህወሓት ቡድን ደጋፊዎች መሆናቸው የዘገባውን ተዓማኒነት አጠያያቂ አድርጎታል። በተለይ ተፈፅመዋል የተባሉትን ግድያዎች በዝርዝር የሚናገረው እና የሞቱ ሰዎች … [Read more...] about CNN ትህነግን እንደ ማስረጃ ጠቅሶ የሠራው ዘገባና ያፈተለከው ቅሌት
“የማንነታችን መገለጫዎች ማሰሪያው ኢትዮጵያዊነት ነው”- ዶ/ር ዲማ ነገዎ
ዛሬ (ሰኞ) በሸራተን አዲስ እየተከበረ በሚገኘው የኢትዮጵያዊነት ቀን የመወያያ ጽሑፍ ያቀረቡት ዶ/ር ዲማ ነገዎ የማንነታችን መገለጫዎች ማሰሪያው ኢትዮጵያዊነት ነው ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያ የህዝቦች የተለያዩ የማንነት መገለጫዎች መኖራቸውን የገለጹት ዶ/ር ዲማ እነዚህን ሁሉ አጠቃሎ አንድ ዓይነት አገራዊ ማንነት የሚሰጠን ኢትዮጵያዊነታችን ማንነት ነው ብለዋል፡፡ አሁን ያለው ኢትዮጵያዊ ማንነት አንድነትን በብዝሀነት አጣምሮ ሁሉንም ህዝብ በእኩልነት የሚያስተናግድ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ አገሪቷ አሁን ያለችበትን ውስብስብ ፈተና እንድትሻር ለማስቻል በህግ ማስከበር እና በሌሎች በሚወሰዱ እርምጃዎች የአገርን አንድነት እና ኢትዮጵያዊነትን እንዳይሸረሽር ጥንቃቄ መደረግ አለበት ብለዋል፡፡ (ኢብኮ) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ማስታወሻ፤ የኦሮሞ መብት አቀንቃኝ ነን ለሚሉትና … [Read more...] about “የማንነታችን መገለጫዎች ማሰሪያው ኢትዮጵያዊነት ነው”- ዶ/ር ዲማ ነገዎ