
ከመካከለኛው ምስራቅ አካባቢ የሚሰሙ ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት ኢትዮጵያ ከትህነግ ጋር ወደ ዳግም ጦርነት ልትገባ እንደምትችል ጠቁመዋል። ትህግም ለውጊያ እየተዘጋጀሁ ነኝ ሲል ተሰምቷል። ኤርትራ ደግሞ በሩሲያ ሠራሽ ድሮኖች ራሷን አጠናክራለች።
ከተለያዩ የዜና ምንጮች ለመገንዘብ እንደሚቻለው የኢትዮጵያ መካላከያ ሠራዊት አዲስ የማጥቃት ዘመቻ ሊጀምር ይችላል እየተባለ ነው። ለዚህም ይረዳ ዘንድ ኢትዮጵያ አዳዲስ ድሮኖችን ጨምሮ ተጨማሪ ተዋጊ ጀቶችን ወደ አገር ቤት በዚህ ማስገባቷ ተሰምቷል። ቱርክ ሰራሹ ባይራክ 32 ድሮን እና ተጨማሪ ጀቶች ወደ አዲስ አበባ ሳይገቡ አልቀረም።
ከዚህ በፊት በተለያየ ዙር ሲሰለጥኑ የኖሩና በመጀመሪያው የክተት አዋጅ፣ የተመዘገቡ ወታደሮች እስካሁን ማስልጠኛ ካምፕ ውስጥ ቆይተው ሰሞኑን ወደ ወደ ተለያየ ክልል በተለይም ወደ አማራ ክልል ገብተዋል። ቤኒሻንጉል ክልል ውስጥ ተጨማሪ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የገባ ሲሆን በሁመራ ግንባር ወደር የሌለው የኢትዮጵያ ወታደር ሰፎሮ እንደሚገኝ የሰሞኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት አመላካች ነው።
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አሕመድ ሰሞኑን በሰሜን ግንባር ያሉ ወታደሮችን እየዞሩ ሲጎበኙ ከርመዋል። በሌላ በኩል በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ ትህነግ ለዳግም ወረራ እየተጋዘጀ መሆኑን በትዊተር ገፃቸው መጻፋቸው ይታወሳል።
ከዚህ ሌላ በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች ፋኖዎች ወታደራዊ ሥልጠና እየወሰዱና እየተመረቁ እንደሚገኙ በየጊዜው የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply