
* “በወሎ ግንባር በነበረው ውጊያ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ኃይሎች ተሳትፈዋል”
* የ፷፪ ዓመት ሽማግሌ ከትግራይ ለትህነግ ዘምቷል
በወሎ ግንባር በነበረው ውጊያ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ኃይሎች ከአሸባሪው ቡድን ጋር መሳተፋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በጦርነቱ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ እና የኢትዮጵያውያ ዝርያ የሌላቸው ነጮች እና ጥቁሮች ከአሸባሪው ቡድን ጋር ተሳትፈው መስዋትነት መክፈላቸውን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያረጋገጡት።
“በወሎ ግምባር በነበረው ውጊያ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ኃይሎች ተሳትፈውበታል። የኢትዮጵያ ዝርያ የሌላቸው ሰዎች ተሳትፈው መስዋዕትነት ከፍለዋል። ኢትዮጵያዊ ያልሆነ ሰው ኢትዮጵያ መጥቶ በደሴ ግምባር ሲሞት ኢትዮጵያዊ የሆነ አካል ኢትዮጵያን ለማዳን ምን ያህል ዝግጁ ነው? የሚለው ለሁላችን የሚተው ነው” በማለት ዐቢይ ለባለሥልጣናቱ አስረድተዋል።
የሕወሀት የሽብር ቡድን የከፈተውን ጦርነት እና ጦርነቱን እየመራበት ያለው ህዝባዊ አካሄድ አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህዝብ ለመከላከያ ሠራዊቱ ያሳየው ድጋፍ የሚበረታታ እንደነበር አስታውሰዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በቅስቀሳ የመጣውን የህዝብ ኃይል ለማስተናገድ በመንግስት በኩል በቂ ዝግጅት እንዳልነበር በመግለፅ፤ በአሁኑ ሰአትም ከዛ ሁኔታ እርምት ተወስዶ ስትራቴጂካዊ በሆነ መልኩ እየተሰራበት እንደሆነ ጠቁመዋል።
አጠቃላይ ህዝቡ ለሠራዊቱ ያለው ድጋፍ አሁን ካለው በላይ ሊጠናከር ይገባል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የገጠመችው ጦርነት ከአንድ ወገን ጋር ብቻ እንዳልሆነ በመረዳት ህዝቡ ዋጋ በመክፈል ያለውን ፍቅር በተግባር ሊገልጽ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ጠ/ሚ/ሩ ሲናገሩ “ለምሳሌ ባለፉት ሦስት አራት ወር ገደማ ትግራይ ክልል ለቅቀን ከወጣን በኋላ በመቶዎች የሚቆጠሩ ውጊያዎችን አካሂደናል። ጦርነት አይደለም፤ ጦርነት ድምር ውጤቱ ነው፤ ውጊያ የሚቀደድ የሚሰፋ ነገር ነው፤ መቀሌን ስንይዝም ሲቀደድ ሲሰፋ ነበር፤ የሆነ ኃይል ይበተናል፣ የሆነ ኃይል ይማረካል፣ የሆነ ኃይል በጀግንነት ይዋጋል፣ መፍረስ መልሶ መደራጀት፣ አንዳንዴ ትጥቅን ጥሎ መሄድ፣ ትጥቅን ሽጦ መሄድ፣ አንዳንዴ ደግሞ ትጥቅ በሌለበት ሁኔታ እጅ በእጅ መዋጋት ሁሉም ባህርዮች ውጊያ አሉት” በማለት የጦርነቱንና የውጊያውን ሁኔታ አስረድተዋል።
ከዚህ ጋር በተያያዘም ከ፲ ቀን በፊት ትህነግ ፈንጂ ደርድሮ በሌላ መንገድ ነበር ሊያጠቃ ቢመጣም መከላከያው እንዳያልፍ የገደበውን ፈንጂ ፲፱ ራሳቸውን ለመስዋዕትነት ያዘጋጁ ወጣቶች እኛ በፈንጂ ላይ ተረማመደን ለመከላከያው መንገድ መጥረግ አለብን ብለው አድርገውታል፤ ራሱን መስዋዕት አድርጎ አገርን ለመታደግ የወሰነ ሕዝብ አለ በማለት አስረድተዋል።
ጦርነት የፖለቲካ እሳቤ ማስጠበቂያ የመጨረሻ መንገድ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚ/ሩ፤ ውጊያ በየትኛውም ሁኔታ ሊኖር እንደሚችል ገልፀው ጦርነቱን ግን ኢትዮጵያ እንደምታሸንፍ አትጠራጠሩ ብለዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሙሉ ንግግር ከዚህ በታች ይገኛል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
ልብ ያላቸው የድሮ ሰዎች ነገር ሲከብድባቸው “የምችለው ስጠኝ ይሉ ነበር”። ጠንቋዪ፤ ባለ ቃልቻው፤ ነብይና ነብይት ነይ ባዪቹ በሚዘላብድባት በዚህች የመከራ ምድር ላይ የሰው እንባና ሞት መቀለጃ ሆኗል። እኔ ጋ እስካልደረሰ የመከራው ወላፈን የላሰውን ቢልስ ደንታ የማይሰጣቸው በየቀኑ ከየስፍራው ከውጭ ሃገር ሰው ለፍቶ በሚልክላቸው ገንዘብ ጮቤ የሚረግጡ፤ አልፎ ተርፎም ከህዝብ ላይ ለ 27 ዓመት ዘርፈው ባጠራቀሙት የደም ሃብት በውስኪ የሚራጩና ከበሮ የሚመቱ በምድሪቱ እየተስተዋሉ ነው። ጀግና አባሮ ገዳይ፤ የሃገር መከታ የሚባለው ወታደርም ያለ ስልት አፈግፍጎ አሁን እንሆ ወያኔ በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል የመከራና የዘረፋ ዶፍ በማዝነብ ላይ ይገኛል። ገናም የመከራው ዝናብ ይቀጥላል። ያ ጎርፍ ማንን ጠርጎ ማንን አልፎ እንደሚሄድ ግን ማንም መገመት አይችልም።
ከወያኔ የተባረረው አሁን ተመልሶ የጦር መሪ ነኝ የሚለው ጻድቃን የተናገረውን ላዳመጠና የጠ/ሚሩን ዲስኩር ለሰማ የሁለቱ የአነጋገር ፈሊጥም ሆነ ድንፋታ ጭራሽ አይገናኝም። ግን ሁለቱም ለድላቸው መሳካት ያቀረቡትን ሃሳብ ለመዘነ የወያኔው ወታደር ጭብጥ መረጃ ያለው ይመስላል። ያው ሁሉም ወያኔ ከድርጅቱ ወጣ ገባ አንድ መሆናቸውን በዚህ ደም አፍሳሽ ወታደር ታያለህ። ዛሬም ስለ አንድ ብሄር የበላይነት፤ ስለ ሚኒሊክ ጨቋኝነት ሲያወራ ላዳመጠው እነዚህ ሰዎች ጨርቅ ያወለቁ እብዶች መሆናቸውን ታያለህ። ምንም አይነት ድርድር፤ ምንም አይነት የሰላም ጥሪ በእነዚህ ሰዎች ልብና ጭንቅላት አይደርስም። አፍርሶ መፍረስ ነው ምኞታቸው። ታዲያ ይህን ምኞታቸውን ማሳካት የሚቻለው በተጣመረ ጉልበት ሆኖ እያለ ሁሉም በየጎራው ማቅራራቱ ፍሬ የለውም። ወያኔ ወደፊት በገፋ ቁጥር ለእልቂት መጋለጡም አይቀሬ ነው። የኦሮሞ ሸኔዎች ከወያኔ ጋር አብሮ ሃተፍ ተፍ ማለት ደግሞ ወያኔ አኝኮ እስኪተፋቸው ነው። ያኔስ በለንደን በአሜሪካ መሪነት ከኦነግ ጋር አብረው አልነበረ የመከሩት። የተመከረው ሌላ አዲስ አበባ ከተገባ በህዋላ የተከወነው ሌላ። የዘር ፓለቲካ የሙታን ፓለቲካ ነው። እንደ ውሻ አናካሽ!
ጉዳዪ አሁን የሞትና የሽረት ነው። ዳግመኛ ወያኔን ተቀብሎ የሚያስተናግድ ምድር የተረገመ ይሁን። ጥፍራቸው የተነቀለ፤ ቆለጣቸው የፈረሰ፤ በሴትና በወንድ ብልት ያልሆነ ነገር የገባባቸው፤ የሴት መርማሪዎች የሸኑባቸው ኸረ ስንቱ ይባላል። ያ የመከራ ዘመን ይረሳል? ወያኔ በክህደት የተካነ የተናገረውን የሚረሳ ክፉ መናፍስት ነው። ጻድቃን ሲናገር እኛ የሰሜን ጦርን አላጠቃንም ሲል በፊት የተናገረውን ዘንግቶ ነው። አይ ውስልትና። ግን ከእብድ ጋር ግርግር አይመችም። መተው ነገሬን ከተተው ይላሉ አበው።
ዶ/ር አብይ አዲስ አበባ ላይ ሆኖ በካሜራ ፊት ከሚደሰኩር ነገሩን በዝግ ማድረግም በቻለ ነበር። ግን የዝግ ስብሰባ የሚያደርገው ምንም ሚስጢራዊ ነገር የለውም። ባይሆን እንኳን የተጨነቁትን ሰዎች ፊት አናይም ነበር። የድሮን አጠቃቀም ሰራዊቱ ታጥቋል፤ እንዲህም እንዲያም እናረጋለን እያሉ ሲለፉ የነበሩት ለምን የወያኔ አመራሮችን ለመግደል አልተቻለም። መንጋውን ለመበተን አመራርን መግደል ነው። ሌላው ሁሉ ከመንገድ ላይ እየተጫነ እቃ ለመዝረፍና ሃብታም ለመሆን የሚመጣ ጀሌና አንድ ተኩሶ የሚፈረጥጥ ነው። ግን ይህን የመሰለ ጥቃት ለማድረስ ደግሞ የስለላና የወታደራዊ ቅንጅት አስፈላጊ ነው። ይመስለኛል በስለላውም በወታደራዊ ቅንጅቱም ወያኔ የበላይነቱን ይዟል። የወያኔ ጄኔራሎች ልብ አብጦ በየምክንያቱ መጣንባችሁ ይህን እንይዛለን እቤታችሁ ታሸጉ ያሉትም ለዚሁ ነው።
በመጨረሻ ኢትዮጵያ የፈጣሪ ቃል ኪዳን አላት፤ የሰው ጸሎት አሳልፎ ለመከራ አይሰጠንም። የጾምና የጸሎት ጊዜ አውጅ የምትሉ ያለፈውን ታሪክ ከአሁኑ ታሪክ ጋር ብታመሳክሩ ፈጣሪ በእኛ ጉዳይ የገባበት አንድም ዘመንና ጊዜ የለም። የተደበቀው ማስታወሻ በዶ/ር ሀራልድ ናይስትሮም ተጽፎ በዶ/ር ገበየሁ ተፈሪና ደሳለኝ ዓለሙ የተተረጎመው (With St. George on the death ride) የሚነግረን ፈጣሪን ያመለክንና ያስቀደምን መስሎን ሰው ያስጨረስንበትን ታሪክ ነው። አሁንም አትዘላብድ። የእኛ ችግር ራሳችን የፈጠርነው፤ በራሳችን የሚፈታ እንጂ ፈጣሪ እሳት እንደሚያቃጥል አሳውቆን እጃችን እሳት ውስጥ ከተን ለምን ተበላን ወይም ና አውጣን ማለቱ በፈጣሪ ላይ ማሾፍ ነው። ግን የሞራል ድጋፍ ሊሆን ይችላል። የቃል ኪዳን ሃገር ናት እያሉ መመጻደቁ። ሶሪያ፤ ኢራቅ፤ የመን፤ አፍጋኒስታን፤ ዪጎዝላቪያ ወዘተ ፈጣሪ አይወዳቸውም እንዴ? የእኛ ሃገር ከማንም ከምንም አትለይም። በራስ አስቦ ለራስና ለሌሎች ሰዎች መብትና ደህንነት ቆሞ ማለፍ እሱ ነው ከፈጣሪ ጋር የሚያስማማ። ሌላው ሁሉ የመሰንበቻ ወይም የመኖሪያ ብልሃት ፍለጋ ነው። ይህ ፍልሚያ የሚያባራበትንና የት ቦታ ላይ እንደሚቆም አሁን ላይ ሆኖ ማሳየት የሚችል የለም። ድል ቀናን ያሉ ሲደመሰሱ፤ አለቀልን ብለው ዋይታ ሊያሰሙ ቀናት የቀራቸው ተነቃቅተው ጠላትን ሲያበራዪና ድል በድል ሲሆኑ በታሪክ አይተናል። ግን ወያኔ ለሃገራችን የጨለማ ዘመን የተመኘ፤ ሲኦል ድረስ ወርዶ ለማፈራረስ የተዘጋጀ በመሆኑ የወያኔ ሞት ለምድሪቱ ከሞላ ጎደል ሰላምን ሊያሰፍን ይችላል። ጠብቀን እንይ። በቃኝ!