• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ከዕቅዱ የጨነገፈውና በሶማሊ ክልል ተሸርቦ የነበረው ሤራ

February 16, 2022 02:28 am by Editor Leave a Comment

“የፌደራል መንግስት ፈርሷል። የትህነግ ወራሪ ሃይል አዲስ አበባ ዙሪያ ከቧል። ራሳችሁን አድኑ። የውጭ ተቋማትና ዲፕሎማቶች አገር ለቃችሁ ውጡ። የመንግስት ባልስልጣናትም ቪዛ ተመቻችቶላችኋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም ወደ አረብ ኢምሬትስ ሊበሩ ነው …” አሜሪካ መራሹ የፕሮፓጋንዳ ሃይል በተከታታይ፣ በዕቅድ፣ በመናበብ፣ በመቀባበል ሲያውጁት የነበረው የሞት አዋጅ ነበር።

“ከማን ጋር ነው ድርድሩ? መንግስት ሞቷል” የሚለውና ከክህደት ቢላዋ ተርፎ አገሩን የታደገውን የአገር መከላከያ ዳግም በትኖ ለማኝ ለማድረግ” የብልጽግና ወታደሮች እጃችሁን ለትግራይ ነጻ አውጪ ስጡ። የሚያድናችሁ ምድራዊ ሃይል የለም። ጊዜ አታባክኑ። የትግራይ ነጻ አውጪ ሰራዊት እርምጃ ሳይወስድባችሁ …” ይህ ደግሞ ከዋና አሜሪካ መራሹ ፕሮፓጋንዳ ስር የሚርመጠመጠው የከሃጂዎች ስብስብ ጩኸት ነበር።

በክህደት የታረደው፣ የደርግ ተብሎ ለልመና የተዳረገው፣ አሁን ደግሞ ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ እንዲሉ “የብልጽግና የአብይ ሰራዊት” የሚል ታቤላ የተለጠፈለት የኢትዮጵያ መመኪያ የአገር መከላከያ ሰራዊት ራሱን ዳግም አደራጅቶ፣ በሃይል ገዝፎ፣ በትጥቅ ዘምኖ፣ ከፋኖ፣ ከሚሊሻ፣ ከልዩ ሃይልና ከአፋር አናብስት ጋር ተጋምዶ ከአየር ድጋፍ ተደርጎለት “መግባት እንደመውጣት አይቀልም” በሚል መርህ በሁለት ሳምንት ነገሮች ተገለበጡ።

ሃፍረትን ከቶ የማታውቀው አሜሪካ በወኪሏ አማካይነት “1991 ላይ የተቸነከሩ” ስትል የትህነግ መሪዎችን አገር በቀለ ስም አጸኑ። ሕዝብ የማይወዳቸውና የማይቀበላቸው እንደሆነ ቢነገራቸው የማይገባቸው እንደሆኑ በአደባባይ አስታውቀው ዘለፏቸው። ሱሉሱ ሲዞር እነሱም ዞሩ። ያቺ ፈርሳለች የተባለች አገር ዲያስፖራ ልጆቿ ጋለቡባት። የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ተካሄደባት። በአደባባይ በውሃ ዳንስ በግልጽ አዳራሽ፣ ዓለም በቀጥታ እያየ የዓለም “ታላላቅ” የሚባል እንግዶችና የአፍሪካ መሪዎች ተምነሸነሹባት። ይህ ዓይናቸውን ብቻ ሳይሆን ህሊናቸውን ያቆሰለባቸው ሃይሎች ግን አዲስ እቅዳቸውን ለማሳካት በሴራና በክፋት መርመጥመጣቸውን ቀጥለዋል።

ፊደራል መንግስት ላይ የተከፈተውና ኢትዮጵያ ላይ የተጠመደው የብተና ሟርት ሕዝብ አንድ ሆኖ ሲያከስመው ቀጣዩ ዕቅድ ክልሎችን ከተቻለ በሎቢ፣ ካልተቻለም ተቀጥያ በመፈለፈል ከማዕከላዊ መንግስቱ እንዲያፈነግጡ ማድረግ፣ ለዚሁም ከፍተኛ በጀት መመደቡን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።

ትህነግ 300 ሺህ የትግራይ ልጆች የት እንደደረሱ እንደማያውቅ በወጣት ሊጉ አማካይነት ሲያስታውቅ፣ ቀደም ሲል ከዛው ከትግራይ ተቃዋሚ መሆኑንን የሚናገር፣ ነገር ግን ከትህነግ ጋር የአጀንዳ ልዩነት የሌለው ድርጅት መሪ ሰባት መቶ ሺህ ወጣቶች መገደላቸውን በራሳቸው ኔትዎርክ በተደረገ ንግግር ማስታወቁ አይዘነጋም።

የዚሁ ክልሎች ላይ እሳት የመለኮሱ ተግባር በኦሮሚያ በስፋት እንዲከናወን ሰፊ በጀት መለቀቁን ከነበጀት ዝውውሩ የስለላ መዋቅሩ አግኝቶት በታሰበው ደረጃ ሳይሰፋ መቆጣጠር የተቻለ መሆኑንን በውስጥ የሚሰሙ መረጃዎች ያመልክታሉ። በተመሳሳይ የሶማሌ ክልልን በማተራመስ፣ የአፋር ነጻ አውጪ በሚል ትህነግ ያደራጀው ሃይል ጦርነት እንዲከፍትና የአብዲ ኢሌ መዋቅር በሶማሌ ክልል ባለስልጣናትን በመጀንጀንና መዋቅር በመስበር ከቻለ መንግስት እንዲገለብጥ፣ ካልቻለም የተወሰኑ አካባቢዎችን እንዲቆጣጠር ዕቅድ መኖሩም ታውቆ ነበር።

ከአካባቢው የተገኙ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በሶማሌ ክልል መሪዎች ላይ መፈንቅለ አመጽ ለማካሄድ ገንዘብ የወሰዱ፣ አብረው የመከሩ፣ ያሴሩና የተባበሩት ቀድሞ ይታወቁ ነበር። ለዚህም ይመስላል ሁከት ለመፍጠር ያሰቡት ክፍሎች በተከፈላቸው መጠን ሂሳብ ሊያወራርዱ ሲዘጋጁ ጅግጅጋና አካባቢው የፌደራል ልዩ ሃይል፣ ቀይ ለባሽ ተወርዋሪዎች፣ እንዲሁም መከላከያ እንደሁኔታው እርምጃ ለመውሰድ ጣቱን በቃታ አድርጎ መመሪያ ይጠብቅ ነበር።

ቅርብ የሆኑ እንዳስታወቁን ሁሉም ነገር በጥንቃቄ ያለቀው ልክ በአንድ በታጠረ ግቢ ውስጥ በዝግ እንደተደረገ ግጥሚያ ነው። ዋናዎቹ አተራማሾች በመረጃ ተበልጠው ለትርምሱ እንዲጠቅም ተደርጎ በተሰራ መረብ ውስጥ እንዲገቡ ተደርጎ ሸምቆቆው ጠብቆባቸዋል። ቀሪው ውሪም ተለቅሟል። በዚህ መልኩ ያለቀውን ጉዳይ አዲስ ስታንዳርድ “መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተደረገ” ሲል አጉኖታል።

ሁሉም ካለቀ በኋላ ነው የሶማሌ ክልል ሰላምን ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን እንደማይታገስ ያስታወቀው። በሶማሌ መንግስት ስራው ለሰኮንድ እንዳልተስተጓጎለ። የሚገልጹ እንዳሉት ዓላማው ከአፋር ጀምሮ እስከ ሶማሌ ክልል ያለውን ኮሪዶር የማተራመስ ዕቅድ የኖረ የትህነግ ሁለተኛ ደረጃ አሳብ እንደሆነ አመልክተዋል። ለውጡ ይፋ እንደሆነ ቅድሚያ ሶማሌ ክልል ላይ የተሳካ ኦፕሬሽን የተካሄደውም በዚሁ መነሻ እንደሆነ አስታውሰዋል።

አጸደ የምትመራው አዲስ ስታንዳርድ ያሰራጨችውን ዜና ተከትሎ ትላንት አመሻሹን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ጅግጅጋ ከተማ ውስጥ ረብሻ፣ አለመረረጋጋትና መንግስታዊ የኃላፊነት ቦታዎችን በኃይል ለመያዝ የተደረገ ሙከራ እንዳለ ተደርጎ ተናፍሷል። ይህን መረጃ ክልሉ “ፍፁም ሀሰትና ከእውነት ራቀ” ሲል አንኳሶታል። በአሁኑ ወቅት ጅግጅጋ ከተማን ጨምሮ መላው የሶማሌ ክልል እንደ ወትሮው ሁሉ በሰላምና መረጋጋት እንቅስቃሴዎች እየተከናወነ መሆኑም ገልጿል።

ክልሉን የማተራመስ ሙከራ እንደነበር ያላስተባበለው ክልሉ ፀረ ለውጥ የሆኑ፣ በሙስና እንዲሁም በውጭ ሀገራት ከሚገኙ ለውጥ አደናቃፊ አካላት ጋር በድብቅ ግንኙነት ሲያደርጉ ተደርሶባቸው ከመንግስት መዋቅር የወጡ ሀይሎች ሰላም ለማደፍረስ ያደረጉት ሙከራ ከሰላም ወዳዱ የክልሉ ህዝብ ጋር በመተባበር መክሸፉን አመልክቷል። ክልሉ ከውጭ አካላት ጋር ግንኙነት ያላቸውን አካላት ባያብራራም ከቀድሞ መሪ አብዲ ኢሌ መዋቅር ተጎሮ የቀረው፣ ከፍተኛ ሃብት ይዞ ኮብልሎ ቱርክና ኬንያ የተቀመጠውና ትህነግ ዳግም ያደራጀው ሃይል እንደሆነ ይታወቃል።

የሶማሌ ክልል መንግሥት ከሰላም ወዳዱ ህዝብ ጋር በመሆን የክልሉን ሰላምን ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን እንደማይታገስና አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ማስታወቁን የሶማሌ ክልል ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ሲያስታውቅ ምን ያህል በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ይፋ አላደረገም። ሸገር ታይም የጠቀሳቸው የሶማሌ ክልል የልዩ ሃይል አዛዥ ኮሚሽነር መሀመድ አህመድ መረጃ ሰጥተዋል።

ከቀናት በፊት ርእሰ መስተዳድሩ የሌላ ብሄር ውግንና አለው፣ አሃዳዊ ነው እንዲሁም ካቢኔያቸው ለድርቁ በቂ ምላሽ እየሰጠ አይደለም በሚል ሽፋን ክልሉን ለመበጥበጥ እና በዋናነትም ጅግጅጋ ከተማ ላይ ረብሻ ለማስነሳት የታቀደ ቢሆንም በዚህ ቅስቀሳ የተሰማሩ እና ለአላማቸውም ማሳኪያ ገንዘብ በሚስጥር ሲያከፋፍሉ የነበሩ 10 የሚሆኑ የቀድሞ አመራሮች ከፍርድ ቤት የማሰሪያ ትዕዛዝ እንደወጣባቸው በይፋ አመልክተዋል። የሚፈለጉት ጥቂቶቹ እየታደኑ ሲሆን አብዛኞቹ ከላይ በተገለጸው መሰረት ፍለጋ ድረስ እንኳን አላስቸገሩም።

ከቀናት በፊት የክልሉ መንግስት እንዲህ ያለው ተግባርና እንቅስቃሴ እንዳለ መረጃ እንዳለው በማስታወቅ ቅድመ ማሳሰቢያ ሰጥቶ ነበር፣ ከማሳሰቢያው በኋላ ኮሚሽነሩ አሁን ላይ ግን ክልሉ አፈንጋጮችን የሚታገስበትም ሆነ ማንንም የሚያባብልበት አቅምና ትእግስት እንደሌለው አመልክተዋል። የክልሉ መንግስት ይህ ከመሆኑ በፊት ለመጨረሻ ግዜ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ተከትሎ ጀሌው ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ኮሚሽነሩ ይፋ አድርገዋል። ከሴራው ጋር በተያያዘ እጃቸው ያለበትን ማናቸውንም አካላት በህግ ለመጠየቅም እንቅስቃሴ መጀምሩንና በቁጥጥር ስር የዋሉ አካላት መኖራቸውን አስታውቀዋል።

“ሁከት እና ውዥንብር ለመፍጠር የሚያልሙ አካለት አንቅስቃሴያቸውም ሆነ እኩይ ተግባራቸው ከክልሉ መንግስት እና የፀጥታ መዋቅር በላይ አይደለም” ያሉት ኮሚሽነሩ ተገቢውን እርምጃ እና ህግ የማስከበር ስራ በማያዳግም መልኩ እንደሚተገበር አመልክተዋል።

ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ የክልሉ ሹም እንደነገሩን የልዩ ሃይል፣ የቀይ ላባሽ ኮማንዶዎች ፍጥነትና መከላከያ በቅጽበት ተናበው ያሳዩት ዝግጅት ለሌሎችም ትምህርት የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል። አንዳቸውም ወደ እርምጃ እንዳልገቡ ነገር ግን ሲፈለግ በአጭር ጊዜ ውስጥ ምን ማድረግ እንደሚችሉ ለመገመት ቀልል እንደሆነ አመልክተዋል።

ከክልሉ ያኮረፉና ቀደም ሲል የአብዲ ኢሌ መረብ ስር የነበሩ ኬንያ ሚዲያ ከፍተው እንቅስቃሴ መጀመራቸው የሚታወስ ነው። አሁን ላይ ቻይና በጀመረችው የምስራቅ አፍሪቃን የሰላም ቀጠና የማድረግ እንቅስቃሴ፣ ለዚህም ለቀጠናው ከመደበችው ልዩ ልዑክ ጋር በተያያዘ ይፋ እንዳደረገችው የቀጠናው አገራት አንዱ በሌላው ላይ አፍራሽ ድርጊቶችን እንዳያከናውኑ፣ ድጋፍ እንዳይሰጡ፣ ይልቁኑም ተጋግዘው እንዲመክቷቸው ትሰራለች። የዚህ አካል የሆነው የቅድመ ስምምነት ስብሰባ በኬንያ መካሄዱን ተከትሎና ቀደም ሲሉ ሁለቱ አገራት ባላቸው ስምምነት መሰረት ኬንያ ምድሯ ላይ ሆነው ኢትዮጵያን ለማወክ የሚንቀሳቀሱ አካላትን ጀርባ እንደምትሰጥ ይፋ ማድረጓ ይታወሳል። (ኢትዮ 12)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Middle Column, Politics, Slider Tagged With: operation dismantle tplf, somali region

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ባልደራስ የአገርን ደኅንነት አደጋ ላይ በመጣል ሊጠየቅ ይገባዋል ተባለ July 1, 2022 09:23 am
  • “ሚካኤል ችግኝ ነው። … ችግኝ ይተክላል” ቴዲ አፍሮ June 29, 2022 03:30 am
  • “የእኔን ልጆችና የልጅ ልጆች (22ቱንም) የቀበርኩት እኔ ነኝ” አቶ መሀመድ የሱፍ ከምዕራብ ወለጋ June 28, 2022 01:07 pm
  • የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ June 20, 2022 11:34 pm
  • “የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል June 12, 2022 07:09 pm
  • የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው June 12, 2022 06:21 pm
  • ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል June 12, 2022 05:40 pm
  • የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ June 12, 2022 05:35 pm
  • በኦነግ ሸኔ ፈርሶ የነበረውና ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ድልድይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ June 10, 2022 09:13 am
  • ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት June 8, 2022 12:59 pm
  • ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር June 8, 2022 11:53 am
  • እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ? June 8, 2022 05:59 am
  • ሕዝብ ድምፅ የነፈጋቸው “ፓርቲዎች” የሽግግር መንግሥት ይቋቋም አሉ June 7, 2022 01:11 am
  • “አድጌ እንደናንተ መሆን እፈልጋለሁ” June 5, 2022 06:58 pm
  • በሳምንት ለ100 ያህል ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጥ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ ጀመረ May 30, 2022 02:20 am
  • የጥቁር አንበሳ ዕጩ መኮንኖች (ካዴቶች) ተመረቁ May 29, 2022 04:01 pm
  • “ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም!!” በሚል ቁጭት ነው እየሠራን ያለነው May 29, 2022 01:04 pm
  • “ከሞፈርና ቀንበር ወደ ትራክተር” በሚል መርህ ለአማራ ገበሬዎች የግብርና ሜካናይዜሽን ተሰጠ May 29, 2022 02:02 am
  • ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል May 27, 2022 02:51 am
  • “እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው” የአማራ ወዳጃቸውን አደራ ቤት የመለሱ የቅማንት ተወላጅ May 27, 2022 01:40 am
  • ትግራይን አገር እናደርጋለን፤ “በውይይት እና በጦርነት” ሁሉንም ጉዳይ እንቋጫለን – የወንበዴው መሪ ደብረጽዮን May 26, 2022 09:18 am
  • “ሁለቱ የምዕራብ ዕዝ ተዋጊ ዶክተሮች” May 26, 2022 08:19 am
  • ወደ ትህነግ ሊተላለፍ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ተያዘ May 25, 2022 01:57 am
  • የጦርነቱ ስትራቴጂያዊ እውነታዎች May 19, 2022 09:37 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule