የትግራይ ተወላጁ ሰለሞን ዘነበ በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ውስጥ ባለ ውድ ሆቴል ተንደላቆ የሚኖር የህወሃት ቁልፍ ሰው ነው።
ቁልፍነቱ የሚመነጨው ደግሞ ጁንታው ስዬ አብርሃ በእናቱ ወገን አጎቱ በመሆኑ ሲሆን ይህ ሰው ለቀድሞዋ የህፃናት ሚኒስትር ፊልሰን እና የሲአይኤ ኬንያ ወኪል ነኝ ባዩ አህመድ ባጄን ጨምሮ ለህወሃት ደጋፊ ሶማሌዎች ገንዘብ በማስተላለፍ በሶማሌ ክልል ሊተገበር ለታቀደው የህወሃት የጥፋት ሴራ መንገድ ጠራጊ ነው።
ባለፈው ሳምንት ሃርጌሳ ታይቶ የነበረው ሰለሞን በቆይታው በሶማሌ ክልል ውስጥ የከተማ ውስጥ ሁከት እና ረብሻ እንዲያስነሱ ለተቀጠሩ ወንጀለኞች ገንዘብ እንዳሰራጨ የታወቀ ሲሆን (የገንዘብ ዝውውር የሚያሳይ ሚስጥራዊ መረጃ የደረሰን ሲሆን አስፈላጊ በሆነ ግዜ ይፋ የሚደረግ ይሆናል) ነገር ግን ከተመደበልን ገንዘብ ቀንሶብናል ያሉና በገንዘብ ክፍያ ያልተስማሙ ቅሬታ ያላቸው አካላትን መረጃ ተመርኩዞ የኬንያ የደህንነት ምንጮች የገንዘብ ዝውውሩን አላማ ሲያነፈንፉ ስለ አንድ “ፕሮጀክት X” የተሰኘ እቅድ እጃቸው ላይ አንድ መረጃ ገብቷል።
ምሥጢራዊው “ፕሮጀክት X” ምንድነው?
ታማኝ የኬንያ የመረጃ ምንጮቻችን ትላንት ማምሻውን እንዳሳወቁን በህወሃት ቁልፍ ሰዎች መሪነት የተቆመረው እና ኬንያ ላይ ተብላልቶ በስዬ አብርሃ ዘመድ ሰለሞን ታረቀ ፋይናንስ አቅራቢነት በፊልሰን አብዱላሂ፣ መሀመድ ሀሰን (ባጄ) ወደ እንቅስቃሴ የገባው project X (ፕሮጀክት ኤክስ) የተሰኘው እቅድ ተጋልጧል።
ዕቅዱ በተለያዩ ክፍሎች የተቀመጠ ነው ያሉት ኬንያ የደህንነት የመረጃ ምንጮቻችን ከነዚህም መካከል በዋናነት
- በፕሮፓጋንዳ ዘርፍ
- ፓርቲው ውስጥ መከፋፈል መፍጠር ወይም ተፈጥሯል በሚል ውዥንብር መፍጠር፣
- መፈንቅለ መንግሥት በሚል አለመረጋጋት እንዲኖር ማድረግ፣
- የኢኮኖሚ ሻጥር በመሥራት ህዝብ እንዲማረር ማድረግ
- የክልሉን መንግሥት ቅቡልነት (legitimacy) ማሳጣት፣
- ለድርቁ በቂ ትኩረት አልተሰጠም በሚል ተቃውሞ ማስነሳት
- የክልሉን ተወላጆች በክልሉ በሚኖሩ የሌላ ብሄር ተወላጆች ላይ እንዲነሱ ማድረግ የሚሉት ይገኙበታል።
2. በተግባር
- ነዳጅ ከሀገር እንዲወጣ እና እጥረት እንዲፈጠር ማድረግ (ኢኮኖሚ ሻጥር)
- መሰረታዊ የፍጆታ ፍላጎት ላይ አርቴፊሻል እጥረት መፍጠር፣
- ሕዝብ ተማርሮ መንግሥት ላይ እንዲነሳ ማድረግና የከተማ ሁከትእና ረብሻ ማስነሳት የመሳሰሉ እና ዝርዝር መረጃዎችን ያካተተ ነው ብለዋል።
3. ግቡም
ኦብነግ እና ሸኔን በመሳሰሉ ሃይሎች አጋዥነት በክልሉ የሃምሌ 28 ዓይነቱን ጭፍጨፋ በማካሄድ ኦሮሚያና ሶማሌ ክልልን የጦርነት አውድማ በማድረግ በሰሜን የሚገኘውን የሀገር መላከያ ሰራዊት ፊቱን ወደ ምስራቅ እንዲያዞር እና በሰሜን የሚገኘው ግንባር እንዲሳሳና ለጥቃት ተጋላጭ እንዲሆን የተቆመረ የወያኔ ሤራ አካል ነው።
4. የመረጃ ምንጮች መረጃ ሲገመግም
- በከተማዋ እና በክልሉ የተለያዩ አከባቢዎች ብጥብጥና ሁከት ለመታቀዱ ማሳያ የሚሆነው ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር በዋሉ አካላት ቤት የክልሉ ልዩ ሃይል ልብስ በተለያየ ደረጃ ተደብቆ መያዙ እንዲሁም ወደ ከተማዋ በድንበር በኩል አልፈው ሊገቡ የነበሩ የጦር መሳሪያዎች በቀጥታ ለዚሁ አላማ ሊውሉ ዝግጅት እየተደረገ እንደነበር ጠቋሚ ሆነው የተገኙ ሲሆን የታሰበው የክፋት እና ሁከት ሴራ ምን ያህል የተደራጀ እንደሆነ ነው።
- እያንዳንዷ እንቅስቃሴ ከክልሉ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ክትትል እየተደረገበት እንደሆነ እና ለዚህ ጉዳይ ያሰማሯቸው አካላትም በፀጥታ አካላት እጅ ሲወድቁ በኬንያ የሚገኙ የቡድኑ አንቀሳቃሾች በተለይም የቀድሞዋ የህፃናት እና ሚኒስትሯ ፊልሰን አብዱላሂ በግልፅ ለክልሉ መንግሥት ህዝቡ እንዳይታዘዝ፣ ግብር እንዳይከፍል ምንም ዓይነት ትብብር እንዳያደርግም በይፋዊ የፌስቡክ ገፅዋ ጥሪ ማቅረቧ ነገሮችን አመላካች ናቸው።
5. መሬት ላይ ያለ እውነታ
- የሶማሌ ክልል መንግስት እና የፀጥታ አካሉ እያንዳንዷን ነገር በጥንቃቄ እና በተረጋጋ ሁኔታ እየተከታተለ ሲሆን በኢኮኖሚ ሻጥር በተለይም ነዳጅ ከሀገር በህገወጥ መንገድ እንዲወጣ በማድረግ ህዝብ ላይ ያልተገባ ጫና በፈጠሩ እና ተሳታፊ በሆኑ አካላት ላይ ንብረት እስከመውረስ የደረሰ እርምጃ የወሰደ ሲሆን ሁከት እና ረብሻ ለማስነሳት ቅስቀሳ ያደረጉ ሌሎች ተጠርጣሪዎችን እያደነ መሆኑ መግለፁ ይታወሳል።
- በመሆኑም ህዝቡ በሬ ወለደ ለሚያናፍሱ አካላት ጆሮ ባለመስጠት የወያኔ ተላላኪዎችን እና ተከፋዮቻቸውን በማጥራቱ እርምጃ ላይ የትኛውንም መረጃ ሳይንቅ ለፀጥታ ሃይሉ በማሳወቅ የወያኔን እና የተላላኪዎቿን ሴራ ማክሸፍ፣ ሀገርን በጋራ መጠበቅ፣ ሰላማችንን ከማስጠበቅ ጎን ለጎን በተፈጥሮ አደጋ ለተጎዳው ወገናችን የምናደርገውን ድጋፍ ማጠናከር አለብን መልእክታችን ነው።
በሌላ በኩል እዚህ ምስል ላይ ያሉት ወጣቶች በጠቅላላ የኦብነግ አባል ሲሆኑ ትላንት በደገሃቡር ከተማ ተሰብስቦ በግራ መጋባት ስሜት ውስጥ ሆኖ የብልጽግና አባልን ነን እያሉ መግለጫ ሲስጡ ነበር።
ለአብነት ያክል ማአሊም ቢሊግ ከኦብነግ ጀግኖች አንዱ እና የነጻነት ሰራዊት ውስጥ መንግሥትን በትጥቅ ሲታገሉ ከነበሩት ተጋይ ወታደሮች ታዋቂ ከሆኑ ሰዎች አንዱ ነበር።
መአሊም ቢሊግ በጦርነት ሲዋጉ ተይዘው ጨለማ ክፍል ውስጥ እና እስር ቤት ውስጥ ለረጅም ጊዜ ማሳለፈቸው ከመያዛቸው በፊት በጣም ከታጠቁ ወታደሮች አንዱ እንደሆነም መረጃዎቹ ይገልጻሉ።
ታጋይ ማአሊም ቢሊግ አሁን የብልጽግና የእሪምት ክንፍ ነን በሚሉ የኦብነግ ወጣቶች መካከል ታይቷል።
ይህ ጉዳይ በኬኒያ የመሸገው የሶማሌ ጉዳዮች ኮንግረስ፣ በአብድራህማን ማህዲ የሚመራው ኦብነግ አንጃ፣ በብቃት ማነስ እና በሙስና የተባረሩና ከብልጽግና አባልነት የተሰናበቱ የቀድሞ የክልሉ ባለሥልጣናት ጥምርት የፈጠረው ውዥንብር ሲሆን ዋና አላማው የሶማሌን ክልል የሁከት እና የብጥብጥ ቀጠና የማድረግ ሴራ አንድ አካል መሆነን በቂ ማስረጃ ነው።
በፎቶ ላይ የሚታዩት ወጣቶች ስለ ድርጅታቸው ኦብነግ የት እንደ ወጣና የት እንደገባም አልተናገሩም በምትኩ ብልጽግና ውስጥ ችግር እንደተፈጠር ለማስመስል በክልሉ ሁከት እና ትርምስ ለመፍጠር ራሳቸውን የብልጽግና የእርምት ክንፍ ብሎ ውዥንብር ሲፈጥሩ ታይተዋል።
(Somali Fast Info. ሶማሌ ፈጣን መረጃ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
gi haile says
የሕወኣት ሃይል ከሕዝባችን የተዘረውና በብድር ለአገራችን ተሰጥቶ በተዘዋዋሪ ሕወኣት እጅ የገባው ከ30 ቪሊዮን ዶላር የደረሰው የት ከተባለ ፓርቲው ለወኪሎቹ አከፋፍሎ በሌላ ክልሎች ለሽብር፣ለወንጀል ፣ለመከፋፈል ፣ለዘረፋ፣ለማፊያና አሸባሪ ካድሬዎች ምልመላ የተመደበላቸው በውጭ የፀጥታ ተቋም ሰልጥነው በኢትዮጵያ ፌዴራል ሲሰሩ የነበሩ የጌታቸው አሰፋ ምልምል ድብቅ ሰላዮች ገና ከአገሪቱ ተለቅመው ኣላለቁም ማንነታቸውም አይታወቅም። መረጃውን ሁሉ ጌታቸው አሰፋ ስላጠፋ የኣሁኑ መንግስት በስውር የሚሰሩትን የወያኔ ካድሬና ሰላዮች ለማግኘት ከባድ ጥረት ማድረግ ኣለበት። እነዚህ ካድሬዎች የሁሉም ክልል አባላት ሲሆኑ ድብቅ ማሰልጠኛ ተቋሙን ወደ ኋላ ሄዶ መመርመር ነው።