ድልድይ በማፍረስ፤ መሠረተ ልማቶችን በማውደም ከየቦታው በተለቃቀሙ ወንበዴዎች መሪነት ኢትዮጵያን በ“ነጻ አውጪ” ስም በግፍ ሲገዛ የነበረው ትህነግ በአፍሪካ በትክክለኛ መጠሪያ ስሙ ሊጠራ ዝግጅት ላይ መሆኑ ተሰማ።
ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት/ትህነግ) በማለት የሚጠራውና በኢትዮጵያ እጅግ አስከፊ የሚባልና ትውልድን ያወደመ ርዕዮት በመከተል አገር ያፈረሰው የወንበዴዎች ጥርቅም፤ እስካሁንም በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት በአሸባሪነት ተመዝግቦ የሚገኝ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል። አባላቱና ደጋፊዎችም በዚሁ ሁኔታ የሚታዩ መሆናቸውን ብዙዎች የሚስማሙበት ነው።
ህወሓትና ተላላኪዎቹ በአሸባሪነት እንዲሰየሙ ተጠየቀ
አሸባሪው ህወሓት በሕገወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር በሕግ መታገድ፤ መሪዎቹም በኃላፊነት መጠየቅ አለባቸው
አሸባሪው ህወሃት
“ህወሃት በሚያኮርፍባቸው የሶማሊያ ‹አሸባሪ› ድርጅቶች ይጠረጠራል”
ዓለምአቀፉ አሸባሪ ትክክለኛ ስሙን አገኘ
ከዚህ በታች የሚገኘው መረጃ በዓለምአቀፉ የአሸባሪዎች ቋት ተመዝግቦ የሚገኝ የህወሃት ወንጀል ዝርዝር ነው።
ይህንን ታሳቢ በማድረግ በዓለምአቀፍ ደረጃ እስካሁን ድረስ በአሸባሪነት ስሙ ተተክሎ የሚገኘው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር / ትህነግ በኢጋድ ቀጥሎም በአፍሪካ ኅብረት በአሸባሪነት ሊፈረጅ እንደሆነ ተሰምቷል ሲል ኢትዮ 12 ዘግቧል። አፍሪካ ኅብረት ለምስራቅ አፍሪቃ መልዕክተኛ አድርጎ የሾማቸው የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ሪፖርት ማቅረባቸውም ተሰምቷል።
ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ለአዲስ አበባ ዘገባቢያችን እንዳስታወቁት ትህነግ ወደ ሰላም መድረክ እንዲመጣ የቀረበለትን “የትጥቅ ፍታ” ጥያቄ እንደማይቀበል ባስታወቀ ማግስት የአፋር ክልልን ዳግም መውረሩ ነገሮች እንዲከሩበት አድርጓል። ከዚህ በተጨማሪ የአሸባሪው ትግሬ ቡድን መሪ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል “የትግራይ ሠራዊት ጉዳይ ለድርድር የማይቀርብ ጉዳይ” ነው ማለቱን አፈቀላጤዎቹ ዛሬ ባሰራጩት መረጃ አሳውቀዋል።
ትህነግን “አሸባሪ” የማስባሉ መረጃ ምንጭ እንዳሉት ቀደም ሲል በአማራ ክልል ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ሳይቀሩ በመሰከሩበት ደረጃ በሽብርተኛነት ሊያስፈርጁ የሚችሉ ተግባራትን መፈጸሙ በማስረጃ ተያዟል። ከዚያም በተጨማሪ ሸኔ በይፋ ከትህነግ ጋር መሥራቱ ካወጀበትና ከዚያም በፊት ሰላማዊ ዜጎችን በማሸበር፣ በመግደል፣ በሰላም እንዳይኖሩ በማፈናቀል፣ በመዝረፍ፣ በማፈንና በመሰወር ሁለቱ ተናብበው እንደሚሠሩ መረጃ ቀርቧል። ምስክሮችም ቃላቸውን ሰጥተዋል።
ቀደም ሲል ጀምሮ ትህነግ ለምስራቅ አፍሪቃ ስጋት እንደሆነ ሲጠቆም ይሰሙ የነበሩ አገራት አሁን ላይ በኢጋድ ደረጃ ትህነግ በአሸባሪነት እንዲፈረጅ ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። የዜናው ባለቤቶች እንዳሉት የሚጠበቀው የኦባሳንጆ ሪፖርት ግምገማ ብቻ ነው። ትህነግና አጋሩ ሸኔ በኢጋድ አሸባሪ ተብለው ከተፈረጁ በኋላ የአፍሪካ ኅብረት በቀጣይ ውሳኔውን ከፍ አድርጎ በአፍሪካ ደረጃ ያጸድቀዋል የሚል እምነት አለ።
ትህነግ ሻዕቢያን በመጀመሪያ በኢጋድ፣ ቀጥሎ በአፍሪካ ኅብረት አሸባሪ አድርጎ ማስፈረጁና በተባበሩት መንግሥታት ማዕቀብ እንዲጣልበት፣ ከዓለም ተገልሎ እንዲቀር ማድረጉ ይታወሳል። ከረዥም ጊዜ በኋላ ሻዕቢያ አሸባሪ ስለመሆኑና ከአሸባሪ ጋር ግንኙነት ያለው ድርጅት ስለመሆኑ ማስረጃ እንደሌለ ተተቅሶ ቅፍደዳው እንደተነሳለት ይታወሳል።
ጅቡቲ አሁን ባለው የትህነግ እንቅስቃሴ ሥጋት ላይ የወደቀችና ኃይሏን በተጠንቀቅ ያቆመች አገር መሆኗን የሚያነሱ፣ ኬንያ ሸኔንና በድንበር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ አሸባሪ ድርጅቶችን ለመዋጋት ከኢትዮጵያ ጋር መስማማቷ ክዚሁ እንቅስቃሴ ጋር በማያያዝ ይጠቅሳሉ። የመከላከያ ኤታማዦር ሹም ሱዳን በዝግ መክረው መመለሳቸውና ከሱዳን የላዕላይ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢና የፈጥኖ ደራሽ ኃይል አዛዥ ጋር የተደርገው ምሥጢራዊ ስምምነት በትህነግ ላይ ያጠነጠነ ጉዳይ ስለመኖሩ ማረጋገጫ መሆኑን በርካቶች በደፈናው አስተያየት ሲሰጡበት ነበር።
የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ “ህወሓት” እና “ሸኔ” በሽብርተኝነት ፈርጇል። ቡድኖቹን በሽብርተኝነት ለመፈረጅ የቀረበለትን የውሳኔ ሀሳብ ምክር ቤቱ በ1 ድምፀ ተዓቅቦ እና በ312 የድጋፍ ድምፅ ማጽደቁ አይዘነጋም።
ምክር ቤቱ የተጠቀሱት ቡድኖች በንጹሃን ዜጎች ላይ ጭምር ሲፈፅመኑ የቆዩት አሁንም እየፈፀሙ ያሉት ድርጊት የሽብርተኝነት ወንጀል መሆኑን የውሳኔ ሀሳቡ ያስረዳል። ውሳኔው በምክር ቤቱ ከመፅደቁ በፊት ሽብርተኛ አይደለሁም ብሎ ማስረጃ ይዞ የሚቀርብ አካል ካለ በሚል ምክር ቤቱ ጥሪ ቢያደርግም በጊዜ ገደቡ ማስረጃ ይዞ የቀረበ አካል እንደሌለም የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በወቅቱ ማስገንዘባቸው፣ በምክር ቤቱ ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡ ጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡት በወቅቱ የፌዴራል ዋና ዐቃቤ ሕግ የነበሩት ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቲዎስ ሽብርተኛ ተብለው የተፈረጁትን ቡድኖች በገንዘብ የረዱ፣ በሚዲያ የሚያግዙ፣ አመራርና አባል የሆኑ በህግ ይጠየቃሉ ማለታቸው ይታወሳል።
የዜናው ሰዎች እንዳሉት ውሳኔው ከጸናና በአውሮፓ ኅብረት ተቀባይነት ካገኘ፣ ለትህነግና ለሸኔ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ መዋጮ ሲከፍሉ እና ሲያዋጡ የነበሩ አባሎቻቸው በጎፈንድሚ እና መሰል የገንዘብ መዋጮ መሰብሰቢያ እንዳይጠቀሙ ማድረግ ብቻ ሳይሆን በፊት ካዋጡባቸው መሰል ተቋማት ዳታ ቤዝ ስም ዝርዝራቸው ተለቅሞ ለሚኖሩበት አገር ይተላለፋል ብለዋል። ከዚያ በኋላ ጉዳዩ ምን እንደሚሆን የሚታይ እንደሆነም አመልክተዋል።
በኢትዮጵያ ከፖለቲካ ጥያቄም ሆን አጀንዳ ጋር ግንኙነት የሌላቸውን ሰላማዊ ዜጎች ማወክ፣ ማፈን፣ መግደል፣ ማፈናቀል፣ መዝረፍ፣ ይህንኑ እንደ ድል በማኅበራዊ ሚዲያ ማሰራጨት፣ ለዚሁ ሥራ በቅስቀሳና በአካል ተዋናይ የሆኑትን ድርጅቶች በገሃድ በገንዘብ መደገፍ ላለፉት አራት ዓመታት እጅግ የተለመደና በርካቶችን ያሳዘነ ጉዳይ ሆኗል።
ይህ የኢጋድ ውሳኔ ፍጻሜ ሲያገኝ ወራሪው የትግሬ ቡድን የሚጠቀምበት ባንዲራም ሆነ ማንኛውም ድርጅቱን የሚስታውስ መለያ (አልባሳትንም ጨምሮ) እንዲሁም ሸኔ ለፊት ለፊት እያነገበ የሚያወጣው ባንዲራ በማንኛውም የመገናኛ (ማኅበራዊ ሚዲያንም ጨምሮ) መስመር በበሸባሪነት የሚስጠይቅና በሕግ የሚስቀጣ እንደሚሆን የመረጃው አቀባዮች ትንበያ ሰጥተዋል። እንደማጣቀሻም አልቃይዳን እና መሰል ድርጅቶችን መደገፍም ሆነ ምልክቶቻቸውን መጠቀም በሕግ የሚያስጠይቅ እንደሆነ ለዋቢነት ጠቅሰዋል።
በዚህ የማያፈናፍን አጣብቂኝና ቅርቃር ውስጥ የገባ ትህነግ ሁኔታው በአሜሪካ ከሚገኙት የግፍ ተካፋይ ወዳጆቹ በመረጃነት የደረሰው በመሆኑ ሰሞኑን ኤችአር 6600 የሚል ሕግ በአሜሪካ እንዲጸድቅለት እየተጋ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ብራስልስ ማቅናታቸው በታላቅ ተስፋ ከሚጠበቀው የኦባሳንጆ ሪፖርት ጋር ተዳምሮ፣ የተባበሩት መንግሥታት ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና መሐመድ አማራ፣ አፋርና ሱማሌ ክልልን መጎብኘታቸውና ኒውዮርክ ላይ “ባየሁት ግፍ እንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም” በማለት የሰጡት መግለጫ እንዲሁም አምነስቲ ኢንተርናሽናል በትላንት ሪፖርቱ ትህነግን በጦርነቱ ለተፈጸሙ ወንጀሎች ቀጥተኛ ተጠያቂ ማድረጉ ለተጀመረው ጉዳይ ከፍተኛ ግብዓት ከመሆን ባሻገር ውሳኔው ዕውን እንደሚሆን ጠቋሚዎች ናቸው ተብሏል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Tesfa says
ስማቸው ሳይጠራ፤ በመድረክ ሳይዘከሩ፤ አልፎ ተርፎም መታሰቢያ ሳይቆምላቸው ዘርና ጎሳን፤ ሃይማኖትና ቋንቋን ወይም የዛሬውን የወያኔ ሽንፍላ የፓለቲካ አፓርታይድ የክልል ሰፈራን ተገን ሳያረጉ ለሃገራቸው የወደቁ እልፎች ናቸው። የሚያሳዝነው ዮፍታሄ ንጉሴ እንዳለው ” አንቺ እናት ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ፤ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ”ሆነና ዛሬ በምድሪቱ በኦሮሞና በትግራይ ህዝብ ስም የሰው አንገት ቆራጮች በቅለዋል። ግን ይህም ያልፋል። ገዳዪን ገዳይ ይተካዋል። 300 ሺህ ህዝብ አለቀብኝ ብሎ የሚያላዝነው ወያኔ ለሰው ልጆች መብትና ነጻነት አንድም ቀን ሰርቶ አያውቅም። እንዴት የሰው ቁጥር እንደ ትቢያ ይናቃል? እንዴት እንኳን የ 300 ሺህ ወገን ሞት ቀርቶ የአንድ ሰው አላግባብ መሞት እንዴት ልብን ሰብሮ መንገድን አያስቀይርም? ግን ወያኔ ዓይነ ሰውር ድርጅት መሆኑ በራሱ የመንግስት ጊዜና ስርዓት የገነባውን የሰሜን እዝ መጨፍጨፉ ነው። እናውቃለን ከህዋላ ሆነው እኛ እርስ በእርሳችን ስንተላለቅ የሚሳለቁና እሳት የሚያቀብሉ አልፎ ተርፎም አብረው የሚሰለፉ የውጭ ሃይሎች እንዳሉ። ግን በምንም ሂሳብ ቢሆን ለትግራይ ህዝብ ወይም ለኦሮሞ ህዝብ ገዷቸው ይህን አያረጉም። ለራሳቸው ጥቅም እንጂ። ዛሬ በየሚዲያው ረሃብ፤ መገዳደል፤ መታሰርና ሌሎችንም ነገሮች የቀን ወሬአቸው አርገው የሚነግድ የውጭና የሃገር ውስጥ ሚዲያዎች ሁሉ እይታቸው ጠንጋራ ነው። እሳትን እፍ እያሉ ማንደድ እንጂ እናብርደው የሚል በጠፋበት የበደል ክምር ሰማይ ቢደርስ ጉድ አያስብልም።
እውቁ ጸሃፊ አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ በጦቢያ ላይ እንዲህ ብለውን ነበር። “ከእነዚህም ከእነዚያም ወገን ከቶ እርቅ የሚፈልግ አንድም ሰው አልነበረም፤ ብቻ በየጊዜውና በየወሩ በያመቱ ሲዋጉ፤ ሲፋተኑ፤ ሲተራረድ፤ ሲተላለቁ ይኖሩ ነበር እንጂ”። ይህ ደራሲው ያለፈውን ታሪካችን ለመጥቀስ ያሉት ነበር። ግን የዛሬውን ይመስላል? ለውጥ፤ ለውጥ እንላለን እንጂ ትላንት ያለቀሱ አይኖች ዛሬም ያነባሉ። ትላንት ዘብጥያ የወረድ ሰዎች ዛሬም እስር ላይ ናቸው። ትሻልን ትቼ ትብስን እንዲሉ ሁሉም ነገር ሁሉ አማራ ላይ በማነጣጠሩ እንደ ጫካ አውሬ እየታደነ የሚገደለው አማራው ነው። ሰው የትግራይ ወይም የአማራ ወይም የኦሮሞ ተወላጅ የሆነው ማመልከቻ አስገብቶ አይደለም። ግን ለጠባብ ብሄርተኞች ዓለማቸው ብሄራቸው ነው። የሚታገሉት የጭቁን ህዝቦችን ድምጽ ሰምተው ሳይሆን በዘርና በቋንቋቸው ተጠልለው የመኖሪያ ብልሃት ለመፈለግ ነው። ፓለቲከኞች ሲጀመር ወስልትና በስልቻ ይዘው ነው የሚዞሩት። ለመሰላቸው ያካፍሉታል። ያም እንደ እንቁራሪት አንድ ሲጮህ አብሮ ይንጫጫል። ሳያስበው የደም ሰው ይሆናል። እጅ በንጽሃን ደም ይጨቀያል። ያ ሰው ተመልሶ ጤናማ ኑሮ ለመምራት ጭራሽ አይችልም። የሃገርና የዘመድ ሸክም መሆን እንጂ። የሰው ደምን ለዚያውም በከንቱ አፍሶ በጤና ቆሞ መሄድ የለም። ለዛ ነው ደ/ጽዪንና መሰሎቹ ህጻናት የማያስቡትን ሃሳብ እያሰቡ የትግራይን ህዝብ ከሌላው ወገናችን ጋር የሚያላትሙት። ተለምነው እንቢኝ ያሉት፤ ተመክረው ያልሰሙት የእልፍ ሰው ደም በእጃቸው ላይ ስላለ ነው። ልቧቸው ድንጋይ ሆኗል። ትግራይ መገንጠል ከፈለገች ማንም ሃይል መከልከል አይችልም። ግን ተገንጥሎ ምን ለማደረግ ነው? ከደቡብ ሱዳን፤ ከኤርትራና ከሌሎችች ሃገራት የመገንጠል ታሪክ መማር እንዴት ይከብዳል? ግን ያበደ ጭንቅላት ዶክተር፤ ጄኔራል ገለ መሌ ብትለው የሰከነ ባለመሆኑ ሚዛናዊ አይደለም። አሁን እንሆ የወያኔ ተለጣፊ ድርጅቶች በተለይም የኦነግ ሸኔና የጉምዝ ታጣቂዎች የሚፈጽሙት ደባና ሴራ ሰው ያቀባብራል? እንዴት ባለ ሂሳብ ነው የሰው ልጅ እንደ ከብት እየታረደ ሌላው ቆሞ ዝም የሚለው። አዲስ አበባ ላይ ለኦሮሞ ነጻነት ሲታገሉ የነበሩ፤ ወያኔ አፍቃሪ ሃይሎች፤ የሃይማኖት አባቶችና ቤ/ክርስቲያናትና መስጊዶች ለምንድነው ከህዝቡ ጋር በጋራ አደባባይ ወጥተው መንግስትን ፈጣን እርምጃ ባለመውሰድ፤ ወያኔና መሰሎቹን እብደታቸውን እንዲያቆሙ በድፍረት ድምጻቸውን የማያሰሙት? ግን ሁሉም ደንዝዟል። በሩ ድረስ ችግሩ እስኪመጣ ይጠብቃል። ሊደርስ ይችላልና ያኔ ምን ይውጣችሁ?
ነገርን በሃሳብ ተማግቶ በዚያው ዙሪያ መረጃን አመላክቶ ይህ ነው ያ ነው ተባብሎ መኖር ቀርቶ አሁን ሁሉም በሬ እየሸጠ ክላሽን ከገዛ እናንተ ሆዳሞች ሁሌ የሰንጋ ሥጋ የምትበሉ ሰንጋ ሲያልቅ ምን ልትበሉ ይሆን? አንዴ በረሃቡ፤ ሌላ ጊዜ በበሽታ የሚያልቀውን እንስሳ ከግምት ታስገባላችሁ? የሞት መድሃኒት ሥጋ ነው የተባለ ይመስል ሁሌ ሥጋ የምትበሉ ሰዎች ለጤናም በጎ እንዳልሆነ አይገባችሁም ወይስ የዛሬን ኑሬ ልሞት ነው? ሰይፉ መታፈሪያ ፍሬው ” የተጉዋጎጠ ልብ” በሚለው ግጥሙ ላይ ብዙ ካስነበበን በህዋላ እንዲህ ይለናል።
መጻፍ መጻፍ አለኝ ማቅለም ወረቀት
ብዕሬን ማስቆጣት ቀይ ደም ማስተፋት።
የኢትዮጵያ ችግር የሚፈታው በጽሁፍ፤ በሙዚቃ፤ በግጥም፤ ሃሳብን በሃሳብ በመሞገትና አንድ የአንድን አምኖና ተቀብሎ በመኖር እንጂ በውጭ በተሸመተ የጦር መሳሪያ አይሆንም። መስሎን እንጂ የሚያስታጥቁን ሃይሎች ሁለታችንም ነው በተዘዋዋሪና በቀጥታ እሳት የሚያቀብሉት፡ እስራኤል ሃገር ከመሆኗ ከ 1948 በፊት እንግሊዞች ፍልስጤማዊያንና ጽዪናዊያንን እያስታጠቁ ሲገዳደሉ ቆመው ያዪ ነበር። በህንድ በሂንድና በእስልምና ተከታዪች መካከል ቅራኔ እንዲነሳ ከደረጉ በህዋላ ሲገዳደሉ እንግሊዞች ቆመው ይሳለቁ እንደነበር የታሪክ መጽሃፍት ይናገራሉ። ወያኔም ሸኔም ሌላው እንዘጥ እንዘጥ ባይ በጊዜው ይከስማሉ። ለአሁኑ ግን ጥለውት የሚያልፉት የክፋት ጠባሳ የልጅ ልጅ አይረሳውም። ኦነግም ሆነ ሸኔ በሽብርተኝነት ተፈረጀ አልተፈረጀ ብዙም ፋይዳ የለውም። ዋናው ጥያቄ ማን እየሞተ ማን ይኖራል ነው። የዚህ መልስም ቢሆን ግልጽ ነው። ገዳይ ማችን ተጫምቶ ብዙ አይቆይም። ጊዜ ይገለበጣል። ለአሁን ሜዳውም ፈረሱም ከቀን ጋራ የእናንተ ነውና አስለቅሱን፤ ግደሉን፤ ዝረፉን፤ ተሳለቁብን። ግን የፓለቲካና የግድያ አዟሪቱ እንደ ጠበል ነው። ለሁሉም ይደርሳል። እሳትን በእሳት ብሎ ሰው ሲከፋው ይነሳል? ያኔ አትራፊም ሸማችም አይገኝም። ተያይዞ እየየ ነው። አሁን ከምናየውና ከምንሰማውም የከፋ ይሆናል። በቃኝ!