ድልድይ በማፍረስ፤ መሠረተ ልማቶችን በማውደም ከየቦታው በተለቃቀሙ ወንበዴዎች መሪነት ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም በግፍ ሲገዛ የነበረው ህወሃት/ትህነግ ዛሬ ትክክለኛ ስሙን አገኘ።
ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት/ትህነግ) በማለት የሚጠራውና በኢትዮጵያ እጅግ አስከፊ የሚባልና ትውልድን ያወደመ ርዕዮት በመከተል አገር ያፈረሰው የወንበዴዎች ጥርቅም፤ እስካሁንም በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት በአሸባሪነት ተመዝግቦ የሚገኝ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል። አባላቱና ደጋፊዎችም በዚሁ ሁኔታ የሚታዩ መሆናቸውን ብዙዎች የሚስማሙበት ነው።
ከዚህ በታች የሚገኘው መረጃ በዓለምአቀፉ የአሸባሪዎች ቋት ተመዝግቦ የሚገኝ የህወሃት ወንጀል ዝርዝር ነው።
የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ “ህወሓት” እና “ሸኔ” በሽብርተኝነት ፈርጇል፡፡ ቡድኖቹን በሽብርተኝነት ለመፈረጅ የቀረበለትን የውሳኔ ሀሳብ ምክር ቤቱ በ1 ድምፀ ተዓቅቦ እና በ312 የድጋፍ ድምፅ አፅድቆታል፡፡
የተጠቀሱት ቡድኖች በንጹሃን ዜጎች ላይ ጭምር ሲፈፅመኑ የቆዩት አሁንም እየፈፀሙ ያሉት ድርጊት የሽብርተኝነት ወንጀል መሆኑን የውሳኔ ሀሳቡ ያስረዳል፡፡
ውሳኔው በምክር ቤቱ ከመፅደቁ በፊት ሽብርተኛ አይደለሁም ብሎ ማስረጃ ይዞ የሚቀርብ አካል ካለ በሚል ምክር ቤቱ ጥሪ ቢያደርግም በጊዜ ገደቡ ማስረጃ ይዞ የቀረበ አካል እንደሌለም የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ተናግረዋል፡፡
በምክር ቤቱ ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡ ጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡት የፌዴራል ዋና ዐቃቤ ሕግ ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቲዎስ ሽብርተኛ ተብለው የተፈረጁትን ቡድኖች በገንዘብ የረዱ፣ በሚዲያ የሚያግዙ፣ አመራርና አባል የሆኑ በህግ ይጠየቃሉ ብለዋል፡፡
ይህ ሲደረግ ግን እንደቀደመው ጊዜ የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዳይፈፀም በተሻለ መጠን ጥንቃቄ እንደሚደረግም አብራርተዋል፡፡
በሌላ በኩል ግን ያለመከሰስ መብታቸው ያልተነሳና ሕውሃትን ወክለው በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ወንበራቸው ተጠብቆላቸው ስራቸው የቀጠሉ አባላት እንዳሉ ይታወቃልና ሕውሃት እንደ ድርጅት በሽብርተኝነት ከተፈረጀ የእነዚህ አባላት እጣ ፋንታ ምን ይሆናል ለሚለው በውሳኔ ሀሳቡ ላይ አልሰፈረም፡፡
ሸገር ዐቃቤ ሕግን ጠይቆ እንደተረዳው በምክር ቤት የቀሩትም ሆኑ ሌሎች የሕውሓት የቀድሞ አባላት ሰላማዊ እስከሆኑ ድረስ ህጉ ወደ ኋላ ሂዶ አይሰራም የሚል ምላሽ አግኝቷል፡፡
በመሆኑም ተጠያቂ የሚያደርገው ከዚህ በኋላ ሲደግፉ መገኘት እንጂ የቀድሞ አባል መሆናቸው ተጠያቂ አያደርጋቸው ተብሏል፡፡
አሁን በምክር ቤት አባልነት ያሉም ቢሆንም ሕውሃት የሚለውን ቡድን ወክለው ሳይሆን የመረጣቸው ሕዝብ ወክለው የተገኙ በመሆናቸው የሕውሃት በሽብርተኝት መፈረጅ በእነሱ ላይ የሚያመጣው አሉታዊ ተፅዕኖ አይኖርም መባሉን ሰምተናል፡፡
መንግስት ቀደም ሲል “ኦነግ ሸኔ” ሲል ይጠራው የነበረውን ቡድን አሁን “ሸኔ” በሚል ስያሜ በሽብርተኝነት እንደፈረጀው ይታወቃል፡፡
ይህም ጥያቄ ሲያስነሳ ነበርና እኛም ዐቃቤ ሕግን ጠይቀናል፡፡
በህጋዊ በመንገድ ተመዝግቦ ኦነግ በሚል ስያሜ የሚንቀሳቀስ ስላለ ከእሱ ለመለየት ነው “ሸኔ” የሚል ስያሜ የተሰጠው የሚል ምላሽ አግኝተናል፡፡
የሁለቱ ቡድኖችን ሽብርተኝነት መፈረጅ ተከትሎት የምክር ቤቱ አባላት መንግስት “ህውሓት”ና “ሸኔ” በንጹሃን ዜጎች ላይ ጭምር የፈፀሙት ጭፍጨፋ በዝርዝር ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲያስረዳ በቡድኖቹ ላይም የፀጥታ ሀይሉ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እርምጃ እንዲወስድም ጠይቀዋል፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን ሸገር 102.1)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
ነፃ ሕዝብ says
የትግራዩ ፋሽስትና ነፍሰ_ገዳይ ቡድን የሆነው ህወሃት ካመሰራረቱ ጀምሮ አሸባሪና ሀገር አፍራሽ መሆኑ ይታወቃል ፥ ነገር ግን “ሸኔ” የሚለው ስያሜ የተሰጠው ለማን ነው ? ሸኔ ማለት ነፍሰ_ገዳዩና ተስፋፊው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) መሆኑን እናውቃለን ፥ ሌላኛው ሸኔ የሚባለው በምኒልክ ቤተ መንግሥት የመሸገው በነፍሰ_ገዳዩ አብይ አህመድ _ የግራኝ አሕመድ የጥፋት ዘር የሚመራውና በአማራ ሕዝብ መጨፍጨፍ ሁልጊዜም እየተደሰተና የተስፋፊነት ተግባሩን በሰፊው የተያያዘው ኦሮሙማው መሆኑ የአደባባይ ምሥጢር ነው ፥ ስለዚህ እናንተ አጉልታችሁ ለማሳየት የሞከራችሁት ፋሽስቱ ህወሃትን እንጂ ሸኔን አይደለም ፥ እንደዚህ ዓይነት የሴራ ድብብቆሽ የሚጫወተው ኢትዮጵያን ለማፍረስ ተግቶ እየሰራ ያለው የበሻሻው አውሬ አብይ አህመድና ተከታዮቹ ብቻ ናቸው ፥ በተለይ ዋና ዓላማቸው የአማራን ሕዝብ ከመሠረታቸው ከተሞችም ጭምር ማውደም ወይም ማጥፋትና የኦሮሚያ ሪፐብሊክን መመሥረት ነው ፡፡
GT says
TPLF, It is rebels who killed millions of Ethiopians, it is a collection of thief , corrupted & enemy of the country /Yenat tut nekash/
Tesfa says
ወያኔ ሃርነት ትግራይ ገና በረሃ እያለ ነው የአሸባሪነት ስራውን የጀመረው። ሽብሩ ነጻ እናወጣሃለን በሚሉትና አቶ መለስ ከወርቅ ህዝብ ተወለድኩ በማለት ያቅራሩለት እድሜ ልኩን በስሙ የሚነገድበት መከረኛው የትግራይ ህዝብ ነው። ስንቶቹ የትግራይ ወጣቶች ናቸው በወያኔ ሴራ አንጃ እየተባሉ አፈር የተመለሰባቸው? ስንቶች ናቸው በግዳጅ ላይ እያሉ ከህዋላቸው በገዛ ጓዶቻቸው የተገደሉት? ስንቶች ናቸው በመርዝ መቃብር የወረድት? ያ ሁሉ አልበቃ ብሎ 27 ዓመት የኢትዮጵያን ህዝብ ጭቁኖ በመያዝ ሴትንና ወንድን በምድፈር፤ ከሰው ባህሪ ውጭ የሆኑ አሰቃቂ ድርጊቶችን በእስረኞች ላይ በመፈጸም፤ በመኪና አደጋ በመግደል፤ ራሱን ገደለ/ች ብሎ አስከሬን በመጣል ያልተሰራ ሴራ በምድሪቱ አልነበረም። ያ አልበቃ ብሏቸው በሰሜን እዝ ላይ ጦርነት ከፍተው ዛሬም በትላንት እሳቤ የትግራይን ልጆችን ሲያስጨርሱ ማየት እንዴት ያማል?
በመሰረቱ በ 21 ኛው ክፍለ ዘመን ጠበንጃ አንግቦ ወገን ከወገኑ መፋለሙ እጅግ አሳፋሪና ኋላ ቀር አስተሳሰብ ነው። እውቁ የአሜሪካ ወታደር Eugene Sledge – With the old breed በተሰኘው መጽሃፉ ላይ በ Peleliu and Okinawa ላይ ከጃፓኖች ጋር የተደረገውን ግብግብ ጦርነቱ ካከተመ በህዋላ ሲናገር “ጦርነት የስልጣኔ ምልክት አይደለም። የእንስሳት ባህሪ ማሳያ እንጂ ይለናል” ይህ ሰው በሺህ የሚቆጠሩ ጓዶቹ ከፊቱ ላይ ሲታጨድ የተመለከተ አልፎ ተርፎም ራሱ በተደጋጋሚ የቆሰለ፤ የጃፓን ወታደርች ለንጉሳቸው በማለት እስከ ሞታቸው ድረስ ሲፋለሙ አይኑ አይቷል። ታዲያ በእኛ ሃገር በተለይም በወያኔ ጠበንጃ አንግቶ ሌላውን ማስጎብደድ ልክ እንደ ታላቅ ድል የሚቆጥሩበት ምክንያት ምንድን ነው ብሎ ለጠየቀ መልሱ ቀላል ነው። የሚሞቱት እነርሱ ሳይሆኑ ሌላው በመሆኑ ነው። ወያኔ የሃገር አስተዳዳሪ እያለ ወደ 2 ሚሊዪን የትግራይ ህዝብ ስንዴ እየተሰፈረለት ከእጅ ወደ አፍ እየኖረ እነርሱ ሰማይ ጠቀስ ፎቆች በሃገርና በውጭ ሃገር ገብተው የናጠጠ ኑሮ እንደሚኖሩ እማኝ መቁጠር አያስፈልግም። ወያኔ ማለት ድርቡሽ ማለት ነው። በሰው ሞት የሚጨፍሩ፤ ሰርቀው፤ ዘርፈው የከበሩ፤ ከጅምሩ በሰው ደምና በውሸት የተቃመሱ ናቸው። የሚያስገርመው የጌታቸው ረዳንና የደብረጽዪን ድምጽ ሰማን ብለው የሚጨፍሩ ድውያን ፓለቲከኞች ነው። እልፍ የትግራይ ልጆች በረሃ ላይ በወያኔ የሴራ ጦርነት የረገፉት በመርገፍ ላይ ያሉት ማን ይዘንላቸው? የሙታን ፓለቲካ ይዞ ይሞታል። የሚሆነውና እየሆነ ያለው ይህ ነው።
በወያኔ ስልት በዘርና በቋንቋቸው የሰከሩት የኦሮሞ ምሁራንና ጭፍሮቻቸው ዓለምን የሚያዪበት አይናቸው ሸውራራ ነው። የኦሮሚያ ሪፕብሊክን እንመሰርታለን በማለት የሚያቅራሩት እነዚህ ሙታኖች ያው እንደ ወያኔ ስማቸውንና ትጥቃቸውን እየቀያየሩ ሰው ከማሸበር አልፈው ለኦሮሞ ህዝብ እዚህ ግባ የሚባል አንድም ነገር አያረጉም በፊትም አላረጉም። ሴት ልጅ መጥለፍ/ሰው ማረድ/ቤት ማቃጠል/መኪና አስቁሞ ሰውን በዘሩ ለይቶ መረሸን ወዘተ… ጫትና ጋንጃ ያደነዘዘው ጭንቅላት እንጂ ሰው የሆነ ይህን አያረግም። የወያኔና የኦነግ ሸኔ በአሸባሪነት መመደባቸው የአደባባዪን በጓዳ እንዲሉ ካልሆነ ህዝባችን ጠንቅቆ ያውቃቸዋል። እነዚህ ድርጅቶች በአሸባሪነት ተፈረጅ አልተፈረጅ የሃበሻው ፓለቲካ እርስ በእርስ ከመላተም አይገታም። አሁን እንሆ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ከስልጣናቸው ወርደው በሌላ ሰው ተተኩ በተባለ ማግስት አረፉ መባሉ ምን ያህል ፓለቲካው የጥሎ ማለፍ እንደሆነ ያመላክታል። እንደ ውሻ የመነካከስ ፓለቲካ። መደማመጥና መቻቻል የነጠፈበት።
ግራም ነፈሰ ቀኝ አሳሪው ሲታሰር፤ የታሰረው ተፈታ ተብሎ ተመልሶ ሲታሰር፤ ነጻ ወጣ የተባለው ህዝብ መልሶ በከፋ መከራ ውስጥ ሲዘፈቅ አይናችን አይቷል እያየም ነው። በመስቀል አደባባይ የታሰበው ሙስሊሞች የኢፍጣር መርሀግብር የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መቋወሟን ሳነብ የእብደታችን ልክ እንደሌለው መታዘብ ችያለሁ። ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች በሃገራቸው የፈለጉትን ማድረግ የሚከለክላቸው ማን ነው? አልሞቱላትም እንዴ? ምን አይነት ጭንቅላት ነው ለአንድ ፍቅዶ ሌላውን የሚነፍግ?መቃወም የሚባለውስ ነገር ከየት የመነጨ ነው? የመከራችን ምንጭ እኛው ራሳችን ነን የምለው ለዚህ ነው። አፍሪቃዊው ህይወት ትርምስ የበዛበት ነው። በዚያ ላይ የቀን አለቆቻችን፤ በሃይማኖት ሳቢያ የሚመጡ ችግሮች፤ የነጭ የእጅ አዙር ሴራ፤ የአረብ ተንኮል ከራሳችን መከፋፈል ጋር ተጣምሮ ባሩድ እንዳሸተትን ስንኖር እልፍ ዘመን አልፏል። አሁን ሱዳን ውስጥ በየጊዜው የሚመላለሱት አሜሪካኖች የኤርትራውን መሪ ለአራት ሰአታት አናገሩት መባሉን ሳነብ ልቤ ፈራ። ሳዳምንና ሌሎችንም እንዲሁ ነበር ያደረጉት። በራሱ አስቦ ለራሱ የሚኖር መሪ ማየት አይፈልጉም። በፓርት ሱዳን ራሺያና ቱርክ የጦር ሰፈር ለመመስረት ደፋ ቀና ሲሉ አሁን እንሆ ሱዳን ሁለቱንም ሃገር ውጡልኝ ማለቷ ከአሜሪካ ጋር ሽርክና እንደገባች ያሳያል። ገና ብዙ ስር ግብ እናያለን። ሱዳን እንኳን ከኢትዮጵያ ጋር ጦር መማዘዝ ቀርቶ ይበልጡ ህዝቧ ጾሙን የሚያድርባት ሃገር ናት። ግን እንግሊዞች ያሰመሩትን ድንበር እንደ ፈጣሪ ቃል በመቁጥር በአሜሪካና በግብጽ ግፊት እንዲሁም በወያኔ እርዳታ ከኢትዮጵያዊያን ወንድምና እህቶቻቸው ጋር መጋደል መፈለጋቸው የቱን ያህል ጥቁሩ ዓለም የአረብና የነጭ ተላላኪ እንጂ በራሱ አስቦ ለራሱ የማይኖር እንደሆነ ያመላክታል። ሱዳን የወያኔ የእንጀራ አባት ናት። ዛሬም ወደፊትም ያስታጥቋቸዋል። ያስጠልሏቸዋል። አንድ አረብ ዘርህ ምንድን ነው ብሎ አንድ ሃበሻን ሲጠይቅ የቱን ያህል የወያኔ ሴራ በዓረቡ ምድር ስር እንደሰደደ ያሳያል። እስቲ እናንተ የእድሜ ልክ የዘር ፓለቲከኞች ንገሩ አሁን ኦነግና ወያኔ የሚያረጉት ግጭት ፍትሃዊ ነው? አይ መሞላቀቅ። ይመቻቹሁ። ከሥር ባለው ግጥም ልሰናበት። በቃኝ።
ሲያሸብር የኖረው በሌላ አሸባሪ ሽብረኛ ተብሎ
ይኸው እናያለን ጊዜ ተገልብጦ።
በፊትም ነበረ መገለባበጡ አንድ ትጥቅ ሲፈታ ሌላው መታጠቁ።
መቼ ነው ያ ጊዜ መቼ ነው ሰአቱ በሃበሻ ምድር እፎይታ ማግኘቱ?
መግደል መገዳደል ማሳደድ መሰደድ ያዝና ጥለፈው
አቃጥለው ደምሰው ማለታችን ቀርቶ
መች ይሆን እንደ ሰው ሰው ሆነን አስበን በቃችሁ የሚለን?
ጢቢራቸው ዙሮ በዘር ፓለቲካ አናክሰው ተናክሰው ለመኖር ለሚሹ
ቂሎች ቂላቂሎች የነፋስ አቅጣጫን በእጣት የሚያሳዪ
ከአዳራሹ ወተው ጎጆ ለቀለሱ ዋ ጊዜ ለኩሉ
እናንተም በተራ ፍርክርክ ብላችሁ
ታየኝ በተራችሁ ዘብጥያ ወርዳችሁ።