• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አሸባሪው ህወሃት

June 25, 2018 10:03 pm by Editor Leave a Comment

“ዘረኛ ከሆንክ የዓለማችን ርካሽ ሰው አንተ ነህ” ሠኔ 16 ቀን (ዕለተ ትንሣኤ) 2010 ዓ/ም የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድንና የባልደረቦቹን የለውጥ እርምጃ ለማመስገንና ለመደገፍ በሚሊዮን የሚቆጠረው ህዝብ በመስቀል አደባባይ ይዞ ከወጣቸው መልዕክቶች መካከል አንዱ።

“…መግደል መሸነፍ ነው። መግደል መዋረድ ነው። በደስታ አንድ ሆኖ ሀገሬን የሚልን ህዝብ በራሱ ዜጋ ሠዎች አቅዶ አስቦ እንዲጨነግፍ መሥራት ትንሽነት ነው። ኢትዮጵያውያን ግን ትንሽ አይደለንም። ትልቅ ህዝቦች ነን። ከትንንሾች ጋር ወርደን ትንሽ አንሆንም። ይህንን ቀን ደስታችንን ለማጨለም፤ ፍቅራችንን ለማጨለም፤ አንድነታችንን ለማደፍረስ ያሰባችሁ ሃይሎች አልተሳካላችሁም።…ትላንት አልተሳካላችሁም። ዛሬ አልተሳካላችሁም። ነገም አይሳካላችሁም…”  ጠ/ሚር ዶ/ር አብይ አህመድ ሠኔ 16/2010 ዓ/ም በእርሱና በባልደረቦቹ የተጀመረውን ለውጥ በማመስገንና በመደገፍ በመስቀል አደባባይ ለተገኘው በሚሊዮን ለሚቆጠር ህዝብ ንግግር ካደረገ በሁዋላ በአሸባሪዎች ከተሰነዘረበት የቦንብ ጥቃት ተርፎ በዛው ዕለት ለኢትዮጵያ ህዝብ ካስተላለፈው መልዕክት የተወሰደ።

*****************************************************************************

እናንተ ህወሃቶች በሞት ጣዕር ላይ የምትገኙ አሸባሪዎች ናችሁ። እናንተ የመደመርና የአብሮነት ሳይሆን የመቀናነስና የመገነጣጠል ሣጥናዔላዊ ልብና ደም የተገጠመላችሁ ዘረኞች ናችሁ። ቅድመ ግንቦት 83ን እንኳን ብንተው ከድህረ ግንቦት 83 እስከ ሠኔ 16/2010 ዓ/ም ከተከዜ በታች እስከ ሞያሌ ከጋምቤላ ጥግ እስከ ሀረር ቀንድ ስንትና ስንት ኢትዮጵያውያንን ፈጃችሁ?

ስንትና ስንት እናቶችን ማቅ አስለበሳችሁ? ስንትና ስንት አባወራዎችን እንደወጡ አስቀራችሁ? ስንትና ስንት ህፃናትን ወላጅ አልባ አደረጋችሁ? ስንትና ስንት ወጣቶችን ገረፋችሁ? ጨለማ ቤት አኖራችሁ? አኮላሻችሁ? ደብዛቸውን አጠፋችሁ? የእናንተ የአሸባሪው ህወሃት ወንጀል እስከ ወዲያኛው ትውልድ ድረስ ገና ይፃፋል።

ሀገርንና ህዝብን በመንግሥትነት ተደራጅቶ የሚሰርቅና የሚገድል በዓለም መንግሥታት ዘፍጥረት ታሪክ ከናንተ ከህወሃት ሌላ አልነበረም፤ የለም፤ አይኖርምም። ህወሃት ማለት የበቀል የርኩሰት የክፋት የጥፋት የሴራ የምቀኝነት የሌብነትና የዘረኝነት – መገለጫና ትርጉም ማለት ነው።

እናንተ ህወሃት በተባለው የሽብር ‘ኢንኩቤተር’ የተቀፈቀፋችሁ ‘የጫጨ’ ህሊና ያላችሁ በሙሶሎኒ ፋሽስታዊ መንፈስ የምትኖሩ የክፍለ ዘመኑ ዘረኞችና ክፉ ሰዎች ናችሁ። በህወሃታዊው አብዮታዊ ዲሞክራሲ የተለከፉት ህወሃት ያልሆኑ ህወሃታውያን ደግሞ  የዘራፊዎችና የሌቦች የገዳዮችና የሽብርተኞች ቅጥረኞችና አገልጋዮች ናቸው። በደቡብ፤ በጋምቤላ፤ በቤንሻንጉል ጉምዝ፤ በኦሮምያ፤ በሶማሊ፤ በሐረሪ፤ በአፋር፤ በአማራ ህዝብ መኻል የተተከሉ የኢትዮጵያ አረሞች። አረሞቹን ስንመነግልና ከስራቸው ስንነቅል እናንተ – ህወሃት እንደ ስብስብ ትመክናላችሁ። የእናንተ የህወሃት መምከን ደግሞ ለኢትዮጵያ ሠላምንና ፍቅርን፤ አብሮነትንና መደመርን ያሰፍናል፤ ኢትዮጵያዊነትን ያነግሣል!!

እናንተ ለኢትዮጵያ ውጋት እንጂ ትንፋሽ አይደላችሁም። እናንተ ኢትዮጵያዊነት ሲዘመር ኢትዮጵያዊነት ከፍ ሲል ዛራችሁ ይነሳል። ታብዳላችሁ።  ደም ይናፍቃችዃል። ኢትዮጵያ ለእናንተ – ለህወሃት – ላሜ ቦራ እንጂ እናት ሀገር አይደለችም። ስታልቧትና ስታደርቋት እርካታንና ሣጥናዔላው ሀሴትን ታገኛላችሁና። ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ሲደሰቱና ሲደመሩ ደምስሮቻችሁ ይቆማሉ፤ ዓይኖቻችሁ ይቀላሉ፤ እጆቻችሁ ይገድላሉ።

ደደቢት ላይ በልባችሁ የተተከለው የርኩሰት ደዌ በዘመን ሂደት እየመዘመዘ እነሆ ከመቃብራችሁ አፋፍ ደርሳችሗል፤ በጣዕረ ሞት ተይዛችሗል። እርግጥ ነው መቃብራችሁ ከተቆፈረ ሰንብቷል። የተጠናቀቀው ሰኞ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ/ም የጆሮዎቻችሁን ታንቡሮች በታትኖ በትናንሽ ጭንቅላቶቻችሁ ውስጥ እንደ ነጎድጓድ ባስተጋባው የኢትዮጵያዊነት ደወል ነበር፤ እኛ ስንኖር ኢትዮጵያውያን ስንሞት ኢትዮጵያ እንሆናለን – በሚለው በአእላፍ ኢትዮጵያውያን መሥዋዕትነትና በአብይ ፆም ፀሎት ባገኘነው ሙሴያችን አብይ መሪያችን አንደበት በምክር ቤት አዳራሽ ሲያስተጋባ!!

ከዚህ ወቅት ጀምሮ ለየላችሁ። ትንሽነታችሁ ይበልጥ አነሰ። ድውይ አስተሳሰባችሁ ይበልጥ ድውይ ሆነ። ጡረተኛና አኩራፊ ደደቢቶች ከነምልምል ሎሌዎቻችሁ ተጠራርታችሁ መቀሌ ላይ ለሙሾና ለሴራ ተቀመጣችሁ።

ገዳዮች ሌቦችና ሀገር ሻጮች ሁላ አብይ መሲሃችንን አብይ መሪያችንን አብይ ሙሴያችንን ለመግደል ስትዶልቱ ከረማችሁ። የከንቱዎች ስብስብ ከንቱ ሴራ! አብይን ገድላችሁ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማንን ልትሾሙብን ነበር የዶለታችሁት? ያሰባችሁት ሆኖ ቢሆን ኖሮ ግን ማዕበሉ መቀሌ በምን ቅፅበት እንደደረሰ ሳታውቁት ይጠራርጋችሁ ነበር!!!

ሠኔ 16 ቀን 2010 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ አብያችንን ለመግደል የወረወራችሁት/ያስወረወራችሁት ቦንብ ስለምን እንደከሸፈ ታውቃላችሁ?  ዕለቱ ከመሲሁ አብያችን ጎን ቆመን ለኢትዮጵያ ትንሳዔ ቃል የገባንበትና የምህረትም ኪዳን ያደረግንበት ቀን በመሆኑ – ዕለተ ኪዳነ ምህረት! የኢትዮጵያ አምላክ በኢትዮጵያ ሠማይ ላይ የሠፈነበት ዕለት በመሆኑ። የርኩሳንን እና የክፉ ሰዎችን ጦር ማምከኛው ቀን በመሆኑ! ሕዝቤን ልቀቁት ያለው ሙሴያችን አብይ የዕለቱን ምስባክ ሲጀምርልን ‘ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ይባርክ’ በማለቱ። ይኸው ነው ምሥጢሩ፤ የፈጣሪ ተዓምሩ፤ የአብይ መዳን ትርጉሙ፤ የኢትዮጵያ ትንሳዔ ይፋ የመሆኑ!!

እንግዲህ የደደቢት ህወሃትና አሸርጋጆቹ ህወሃታውያን ሁሉ እነሆ ለመጨረሻ ጊዜ ይህንን እንነግራችሗለን። ከዚህ ወዲህ የመቃብር ስፍራ የማግኘታችሁን ነገር ተጨነቁበት እንጂ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን የመግዣና የመግደያ ጊዜያችሁ ማክተሙን እወቁ!!! የገዳዩና የዘራፊው የዘረኛውና የከፋፋዩ የሌባውና የሀገር ሻጩ የህወሃት የበላይነትና የአምባገነንነት ዘመን ከእንግዲህ አይመለስም!! በእናንተው ጣልያናዊ ቋንቋ…አዲዮስ!!!

እኛ ግን፤

ሠኔ 16 በሞታችንና በደማችን ሙሴያችንን አብይን ታድገናል።

ሠኔ 16 በሞታችንና በደማችን የኢትዮጵያን ትንሳኤ በአደባባይ አብስረናል።

ሠኔ 16 በሞታችንና በደማችን የእናንተን የህወሃትንና ህወሃታውያንን ትንሽነትን እኩይነትንና ሽንፈትን አሳይተናል። መጪው ዘመን የኢትዮጵያና የኢትዮጵያውያን የፍቅር የሠላም የመደመር የይቅርታና የትንሣኤ ዘመን መሆኑን እነሆ ከአብይ መሪያችን ጋር ሆነን አውጀናል።

አብያችን ሆይ! የኢትዮጵያ አምላክ እንኳንም ለሀገርህ ለኢትዮጵያ  ለህዝብህ ለኢትዮጵያውያን ለልጆችህ ለባለቤትህና ለወዳጅ ቤተሰቦችህ ሲል ከቀን ጅቦች መንጋጋ አተረፈህ!

እናንት በአብያችን ዙሪያ ወገባችሁን አጥብቃችሁ ነገን በመደመር አብያዊ ራዕይ ደፋ ቀና የምትሉ የለውጡ አጋሮችና አራማጆች ከእንግዲህ በንቃትና በብቃት ራሳችሁንም ሆነ አብያችንን ከሚታወቁም ሆነ ከተደበቁ የቀን ጅቦች ጠብቁልን! ከእናንተ አንዱስ ስንኳ ቢጎድል ኢትዮጵያን ትጎዳላችሁና። እናንት በተለይ ከአብያችን ጎን የቆማችሁ የኢትዮጵያ የቁርጥ ወቅት የለውጥ አራማጆች በአብይ መትረፍ እንኳን ደስ አላችሁ! ከእንግዲህ አትዘናጉ፤ ተጠንቀቁ፤ የቀን ጅቦቹንም መንጥሩ!!!

እናንት በደማችሁና በህይወታችሁ ለኛና ለኢትዮጵያ ትንሳዔ መሥዋዕትነት የከፈላችሁ የሠኔ 16 የመስቀል አደባባይ ሠማዕታት ከእንግዲህ በኢትዮጵያ ሠማይ ላይ እንደሚያበሩት ከዋክብት ትሆናላችሁ! በትውልድ ሁሉ ስትዘከሩም ትኖራላችሁ!

የተሰዉትን ፈጣሪ ነፍሳቸውን ከገነት ያኑርልን!
መፅናናት ለተጎዱትና ለመላው ቤተሰብ ሁሉ ይሁን!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ይባርክ!

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር
መስፍን ማሞ ተሰማ
ሠኔ 2010 ዓ/ም (ጁን 2018)
ሲድኒ አውስትራሊያ

mmtessema@gmail.com

ፎቶ፤ የህወሓት ነፍሰበላ የበረሃ ወንበዴ አዲስ አበባን በተቆጣጠረ ወቅት ሜክሲኮ አደባባይ ላይ አንድ ኢትዮጵዊን በጠራራ ፀሐይ ገድሎ


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “ዛሬ ‘ኃያል ነን’ የሚሉ ሀገራት ኢትዮጵያ ላይ በሚዲያ /በመረጃ/፣ በዲፕሎማሲ፣ በሳይበር እና በተልእኮ የተቀነባበረ ‘ግራጫ ጦርነት’ እያካሄዱባት ነው” ጠ/ሚ ዐቢይ July 7, 2022 10:03 am
  • የኦሮሞ ልሂቃንና ፖለቲከኞች በአማራ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለውን “የዘር ማጥፋት” ወንጀል እንዲያወግዙት አብን ጠየቀ July 6, 2022 01:38 pm
  • “አማራን ኦሮሚያ ውስጥ የመግደል እና የመጨፍጨፍ እቅድ የኦነግ ሳይሆን የኦሮሚያ ብልጽግና ነው” አቶ ሃንጋሳ July 6, 2022 01:53 am
  • “በኢትዮጵያዊያን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ሀገሪቱን ማተራመስ አለብን” አይማን አብድልአዚዝ ግብጻዊው ፖለቲከኛ July 5, 2022 12:57 pm
  • ባልደራስ የአገርን ደኅንነት አደጋ ላይ በመጣል ሊጠየቅ ይገባዋል ተባለ July 1, 2022 09:23 am
  • “ሚካኤል ችግኝ ነው። … ችግኝ ይተክላል” ቴዲ አፍሮ June 29, 2022 03:30 am
  • “የእኔን ልጆችና የልጅ ልጆች (22ቱንም) የቀበርኩት እኔ ነኝ” አቶ መሀመድ የሱፍ ከምዕራብ ወለጋ June 28, 2022 01:07 pm
  • የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ June 20, 2022 11:34 pm
  • “የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል June 12, 2022 07:09 pm
  • የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው June 12, 2022 06:21 pm
  • ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል June 12, 2022 05:40 pm
  • የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ June 12, 2022 05:35 pm
  • በኦነግ ሸኔ ፈርሶ የነበረውና ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ድልድይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ June 10, 2022 09:13 am
  • ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት June 8, 2022 12:59 pm
  • ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር June 8, 2022 11:53 am
  • እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ? June 8, 2022 05:59 am
  • ሕዝብ ድምፅ የነፈጋቸው “ፓርቲዎች” የሽግግር መንግሥት ይቋቋም አሉ June 7, 2022 01:11 am
  • “አድጌ እንደናንተ መሆን እፈልጋለሁ” June 5, 2022 06:58 pm
  • በሳምንት ለ100 ያህል ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጥ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ ጀመረ May 30, 2022 02:20 am
  • የጥቁር አንበሳ ዕጩ መኮንኖች (ካዴቶች) ተመረቁ May 29, 2022 04:01 pm
  • “ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም!!” በሚል ቁጭት ነው እየሠራን ያለነው May 29, 2022 01:04 pm
  • “ከሞፈርና ቀንበር ወደ ትራክተር” በሚል መርህ ለአማራ ገበሬዎች የግብርና ሜካናይዜሽን ተሰጠ May 29, 2022 02:02 am
  • ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል May 27, 2022 02:51 am
  • “እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው” የአማራ ወዳጃቸውን አደራ ቤት የመለሱ የቅማንት ተወላጅ May 27, 2022 01:40 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule