
ደሴን ለመውረር አሰፍስፎ የነበረ አሸባሪው የህወሃት ወራሪ ኃይል አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቷል
በወሎ ዩኒቨርሲቲ ፎቶ ለመነሳት ገብቶ የነበረ የጥፋት ቡድኑ ፎቶ ናፋቂም ባለበት አፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ እስከወዲያኛው ተሸኝቷል
የደሴ ከተማና አካባቢዋን ተቆጣጥረናል በማለት ጮኸው የሚያስጮሁ የወራሪው ወሬ አራጋቢዎችም በስፍራው እየተፋለሙ የሚገኙትን የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ወኔና ጀግንነት አልተረዱም
ልዩ መረጃ፤ ከጥቂት ደቂዎች በፊት ጎልጉል እንዳረጋገጠው ደሴን ያረጋጋው መከላከያ ሠራዊት፣ ልዩ ኃይል፣ ሕዝባዊ ሚሊሻና ፋኖ
በርካታ አካባቢዎችን እየተቆጣጠረና በወገን እጅ ሥር እያደረጋቸው ይገኛል። በዚህም ጠላት በከፍተኛ ሁኔታ እየተደመሰሰና እየሸሸ እንደሆነ ለማረጋገጥ ችለናል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ መንግሥት የትግራይ ሕዝብ ላለቁት ልጆቹ ትህነግን ለመጠየቅ እንዲዘጋጅ አሳስቧል።
በጢጣ በኩል ሰብሮ በመግባት የደሴ ከተማን ለመቆጣጠር የሞከረው አሸባሪው የህወሃት ወራሪ ኃይል አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቷል።
የመጣውን ኃይልም ደሴ ከተማ ከመግባቱ በፊት ሙሉ በሙሉ ባለበት ማስቀረት መቻሉን በወሎ ግንባር ወራሪውን ኃይል እያጸዱ የሚገኙ የመከላከያና ደህንነት ምንጮች ለኢዜአ ጠቁመዋል።
የደሴ ከተማና አካባቢዋን ተቆጣጥረናል በማለት ጮኸው የሚያስጮሁ የወራሪው ወሬ አራጋቢዎችም በስፍራው እየተፋለመ የሚገኙትን የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ወኔና ጀግንነት ካለመረዳት የመነጨ እንደሆነ አስታውቀዋል።
በግንባሩ የተሰለፉ የሰራዊት አመራርና አባላትም ወራሪውን ኃይል ለአንዴና መጨረሻ ለማጥፋት አኩሪ ተጋድሎ እየፈጸሙ እንደሚገኝ አመላክተዋል።

በኩታበር በኩል አሰፍስፎ ደሴን ለመውረር የመጣው ወራሪ ኃይልም ምንም ማድረግ እንዳይችል ተደርጎ መደቆሱን ገልጸዋል።
በወሎ ዩኒቨርሲቲ ፎቶ ለመነሳት ገብተው የነበሩ የጥፋት ቡድኑ ፎቶ ናፋቂዎችም ባሉበት አፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ እስከወዲያኛው መሸኘታቸውን ምንጮቻችን አረጋግጠዋል።
ደሴና አካባቢዋን ለመውረር ከየአቅጣጫው ተሰባስቦ አሰፍስፎ የነበረውን ኃይልም አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት የደሴን ከተማ በወገን እጅ እንዳለች ማስቀጠል መቻሉን ገልጸዋል።

የደሴ ከተማ እና አካባቢው የሽብር ቡድኑን የአፈሳ ወሬ ባለመስማት አካባቢውን ጸንቶ እንዲጠብቅና ለግንባሩ ሰራዊት ሲያደርጉት የነበረውን ደጀንነት እንዲያስቀጥሉ ጠይቀዋል።
በግንባሩ ያሉ የሰራዊት አባላት የጥፋት ቡድኑን ማጽዳት ይቀጥላሉ ያሉት ምንጮቻችን በቅርብ ጊዜም ይህኑ የኢትዮጵያ ጠላት የሆነ ወራሪ ኃይልም እስከወዲያኛው የሚሸኙበት ቀን ሩቅ እንዳልሆነ አረጋግጠዋል። (ኢዜአ)
ማሳሰቢያ፤ እስካሁን በታሪካችን አስከሬን አትመን አናውቅም ነበር፤ ሆኖም ትህነግ በሕዝባችን ላይ እያደረሰው ካለው አንጻር ይህንን ፎቶ ማውጣታችን እንዲታወቅ እንፈልጋለን
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
በኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ታሪክ ውስጥ እንደ ወያኔ ያለ ጸላዬ ሰናይ የተጠናወተው ከናዚ ጀርመኖችና ከጣሊያን ወራሪ ሃይል የከፋ ራስ በቀል አረመኔ ገጥሟት አያውቅም። አብረው ቁጭ ብለው በልተው ምግብህና መጠጥህ ውስጥ መርዝ ጨምረው ገለው ሃዘን ላይ ቁጭ ብለው የሃዘን ንፍሮ የሚበሉ ዘግናኝ ፍጡሮች ናቸው። አሁን በደሴና ዙሪያዋ አስቀድመው አሰልጥነውና አስታጥቀው ባሰለፏቸው ሃገር ከሃዲ ሰዎች እየተጠቆሙ ነው ሆቴሎችን አልፎ ተርፎም የታወቁ ሰዎች ቤቶችን ለመደምሰስ የሞከሩት። እነዚህ ሰዎች ከራሳቸው ዘር ውጭ ሌላው ሰው መስሎ አይታያቸውም። ርህራሄ የሚባል ነገር አልተፈጠረባቸውም። ግን አንድ አንድ ሃበሻ አብሮ ከእነርሱ ጋር ሰክሯል። የእነርሱን የፕሮፓጋንዳ ወሬ ተቀብሎ ያናፍሳል። አብሮም ይነፍሳል። የጠ/ሚሩን መንግስት ቅርንጫፍ አልባ እንደ ቀረ ግንድ ይመለምላል። ይህ ሁሉ ግን ለወያኔና ለኦነግ ሸኔ ፈንጠዚያ ነው። የጠ/ሚሩ መንግስት ሴረኞችን አቅፏል፤ ለወያኔ ከውስጥ ሆነው ወሬ የሚያቀብሉትን ዝም ይላል ገለ መሌ መባሉን ከጊዜ ጋር በመረጃ የምንሟገተው ሲሆን አሁን ባለንበት የሞትና የሽረት ሰአት ግን ጠ/ሚሩንና አመራራቸውን የምንነቅፍበት ጊዜ አይመስለኝም። አሁን ሁሉም ነገር ወደ ወያኔ ቢያተኩርና የዚህ እልቂት መቋጫን መፈለጉ ለሃገሪቱና ለህዝቦቿ ደህንነት አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው። አሁን እንሆ እልፍ ገደልን እልፍ ማረክን እያሉ የሚያወሩና የሚያስወሩ ሙታን ቆጠራቸን በመተው ቆሞ ህዝባችን የሚገድለውንና የሚዘርፈውን መግደል አለባቸው። በዚህ ዙሪያ ላይ በየስፍራው ወደቀ የተባለው አስከሬን ተሰብስቦ ካልተቃጠለ ወይም ካልተቀበረ ሊያስከትል የሚችለው የበሽታ አይነት በጥይት የማንመክተው ይሆናል። አውቃለሁ ሙትን ማቃጠል በሃገራችን የተለመደ አይደለም። ለምሳሌ በጃፓን ከ 90 % በላይ ሙታናቸውን ያቃጥላሉ። ህንድና ከህንድ ተቆርሰው ሃገር የሆኑት እንደ ፓኪስታን ያሉ ሃገሮች ደግሞ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን አስከሬን ያጋያሉ። ሰልጥኛለሁ ከእኔ በላይ ላሳር ነው የሚሉት ምዕራባዊያን ሃገሮችም አሁን አሁን cremation የተለመደ ተግባር ሆኗል። ባጭሩ ሙታን መቀበር ወይም መቃጠል አለባቸው። ያለበለዚያ ቋሚን ወደ ላይኛው ዓለም የሚያሸጋግር በሽታ ያመጣሉ።
አሁን በደሴ (ወሎ) እየሆነ ያለውን ነገር በእርግጠኝነት የሚያውቅ የለም። የዜናው አውታር ሰበር ብሎ ከለጠፈው ሃሳብ ይልቅ ሌላ ሲያወራን፤ ካሳየን ተንቀሳቃሽም ሆነ የፎቶ ምስል ጋር ጭራሽ የማይገናኝ ሲቀባጥር መስማት የተለመደ ሆኗል። ይህ ሁሉ ግን ያው ሳንቲም ፍለጋ ለመሆኑ ልብ ማለት ያስፈልጋል። ጭንቅላት አለኝ የሚል ሰው የወያኔውን አፈ ቀላጤ ጌታቸው ረዳንም ሆነ የወያኔውን ቁንጮ ደብረጽዪንን ወሬ ተቀብሎ ማናፈስ አልነበረበትም። ወያኔ በእድሜው እውነት ተናግሮ አያውቅም። ገና ከጅምሩ የራሳቸውን የትግል ጓደኞች ለድርድር ጠርተው አብልተው አጠጥተው በተኙበት ነው ጭፍጭፈው የገደሏቸው። ሰው በተኛበት መግደል ልምድ ስላላቸው ነው የሰሜን እዝንም በተኙበት የጨፈጨፏቸው። ይህ አረመኔ ቡድን ከምድረገጽ መጥፋት አለበት።
በመጨረሻም ከወያኔ መድፍና የጥይት አረር በመሸሸት ማምለጥ አይቻልም። አንድም ሁለትም ይዞ በመሞት እንጂ። ተሩጦ የት ነው የሚደረሰው? ደግሞስ ወያኔ ምህረት ያረግልኛ ብሎ ማመን እንዴት ይታሰባል? ኢትዮጵያን እናፈርሳታለን የሚለው ወያኔ እንዴት ባለ ሂሳብ ነው ልብ ገዝቶ ለሰላምስ ድርድር ቁጭ የሚለው? አሜሪካ ወታደራዊው ግጭት ፍሬ አያመጣም የምትለው በጎን እሳት እያቀበለች ነው። ግን የኢትዮጵያ ልጆች አይለው ወያኔን ቢደመስሱት ከአሸናፊው ወገን ጋር ተገልብጣ መቆሟ አይቀሬ ነው። የውጭውንም የውስጡንም ግፊትና መከራ በመቋቋም መሆን ያለበትም ወያኔ ለአንድ ጊዜና ለመጨረሻ ጊዜ መቅበር ነው። በቃኝ!