የትህነግ 10 በደሎች – በተለይ በአማራ ሕዝብ!
“ትህነግ”… (ትግራይ/ተጋሩ አላልሁም) የተሸነፈው በ1967 ነው። ማንም ቡድን ወይም ርዕዮተ አለም ሕዝብን ጠላት አድርጎ ማሸነፍ አይችልም። ግለሰቦች፣ የፊውዳሉ ስርዓት ጠላት ሊሆን ይችላል። ሁሉም አማራ ግን ጠላት ሊሆን አይችልም። ትህነግ እንጂ የትግራይ ሕዝብ ጠላት እንዳልሆነው ሁሉ።
የትህነግ መሠረታዊ ትርክት (ድርሰት) በገሃድ የተተወነው ባለፈው ዓመት ነው። ትህነግ በተለይ በአማራ ሕዝብ 10 ዐበይት በደሎች ፈፅሟል። በእኔ ሚዛንና ምልከታ።
1) መልክዓምድራዊ ለውጥ (Demographic Change): ድህረ 1983 ማንነትን ባላገናዘበ መልኩ ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ዋግና ራያ ላይ መሬቱን በመውረር ሰዎችን አፈናቅሎል፣ ጅምላ ግድያ ፈፅሟል። ሴቶችን በመድፈርና አስገድዶ በማግባት የዲሞግራፊ ለውጥ እንዲመጣ አድርጓል (ይሄን ከ10 ዓመት በፊት ወልቃይት ላይ ያናገርኋቸውን ሴቶች ዋቢ አደርጋለሁ)
2) የሞራል_ስብራት: አማራ የተባለ ዘር ሁሉ በሄደበት ሁሉ እንደ ጠላት፣ እንደ ክፉ፣ እንደ ትምክህተኛና ጨቋኝ እንዲታይ በማድረግ እንዲገለል፣ እንዲሳደድ ማድረግ። በዚያው ሰርቶ እንዳይበላ፣ በሀገሩ እንዳይኮራ በማድረግ የሞራል ስብራት እንዲርስበት ማድረግ። ከዚህ ባለፈም “አማራ አድግ-አማራ አህያ” የሚሉ ክብረ ነክ ስድቦችን ከትግሉ ጀምሮ ይጠቀማል። ባለፈው ዓመትም አጣዬ ቴክኒክና ሙያ ተቋም ስገባ ያገኘሁት ይሄን ስድብ ነው። “አማራ ሰው ሆነህ ከምትፈጠር፣ ትግራይ ዕቃ ሆነህ ብትፈጠር ይሻላል” የሚለውም ኮምቦልቻ ቴክኒክ ተቋም ያገኘነው ነው።
3) የሕዝብ ዕድገቱን መቀነስ: እዚህ በማልጠቅሳቸው መጠነ ሰፊና ድብቅ በሆኑ መንገዶች የሕዝብ ምጣኔውን መቀነስ ዋነኛ መንገድ ነበር። ተሳክቶላቸዋል።
4) ጅምላ ግድያ (Genocide): ለ27 ዓመታት በወልቃይትና በሌሎች ቦታዎች ባለፈው ዓመት ደግሞ በገቡበት የአማራ ክልል ሁሉ ጅምላ ግድያ ፈፅመዋል። ቤተሰቡ በሙሉ ወደ አመድነት የተቀየረባቸውን የሐይቅና የዋድላ የተወሰኑ ቤቶችን አይቻለሁ። አመድ የሆነ የሰው አፅም በእጆቼ ዳብሻለሁ። የእንስሳትንም እንዲሁ። የገረመኝ ግን የጋይንት ሕዝብ አመድ ለሆኑ እንስሳት እንኳን ቀብር ፈፅሟል።
5) ሳይንሳዊ ጦርነት (Bioterrorism): ትህነግ ባለፈው ዓመት በየሆስፒታሎችና በደሴ መድሃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ የሚገኘውን የፖሊዮ ክትባት በባለሙያ በታገዘ መልኩ ወደ አፈርና የእርሻ ቦታዎች ደፍተውታል። ይሄን እኔው ራሴ በወሎ ሆስፒታልችና በአቅራቢ ኤጀንሲው በአካል አረጋግጫለሁ። በእነዚህ አካባቢዎች በቀጣይ 5-10 ዓመታት የፖሊዮ ወረርሽኝ ስጋት ሊኖር ይችላል። ከአሁኑ ማሰብ ያስፈልጋል። ትህነግ ዓመታትን አስቦ የሚሰራ ክፉ ድርጅት ነው።
6) ረሃብ: ትህነግ የአማራ ሕዝብ በድህነት እንዲማቅቅ ብዙ ስራ ሰርቷል። በማዳበሪያ ሰበብ መሬቱ ላይ ያደረሱትን “Natural Fertility Genocide” ባለሙያዎች ብዙ ያሉት ስለሆነ ልተወው። ባለፈው ዓመት በአማራ ክልል ለገበሬ ዘር የሚያቀርበውን የደሴ ቲሹ ካልቸር ማዕከል ያደረጉትን አይቻለሁ። 500,000 የዘር ማሳደጊያ ባልዲዎችን እንዴት እንዳደረጉ ምስሉን ተመልከቱ። ፅናታቸው። ትጋታቸው ይገርማል። የቆቦ ጊራና የገበሬው ፕሮጀክት ላይ የከርሰ ምድር ማውጫ የኤሌክትሪክ ስቴሽኖችን በመድፍ መተዋቸዋል። የንብ ማራቢያ ጣቢያዎችን በሳት አቃጥለዋቸዋል። ሲሪኒንቃ ለወሬ ነጋሪ አልቀረም። ለራሴ እንዴት ሰው በዚህ መጠን ይከፋል? እያለሁ እተክዝ ነበር። ጉዳዩ ግን የአማራን ሕዝብ በረሃብ የመጨረስ አንዱ መንገድ ነው። ምቀኝነት።
7) ትውልዱን ማምከን: በኢህአዴግ/ትህነግ ዘመን በአማራ ያሉ ት/ቤቶች፣ የህክምና ተቋማት ጉዳይ የሚታወቅ ነው። ምንም እንኳ አሁንም ከዚያው ፈቀቅ ባይልም። ባለፈው ዓመት ትህነግ በትምህርት ቤቶችና በጤና ተቋማት የጨከነው ጭካኔ፣ አንድም በበሽታ ሌላም ትውልዱን በትምህርት ተስፋ መቁረጥ የማምከን አንዱ መንገድ ነው።
8) ማኅበራዊ/ሃይማኖታዊ እሴትን መስበር፡ ወሎ አንድ ከተማ ውስጥ አባትን ከልጅህ ጋር ካልተኛህ ብለው በቤተሰብ መሃል ጥይት ደቅነውበት ነበር። ዝርዝሩ ያማል። በባል ፊት ነፍሰጡር ሚስቱን ለመድፈር ሲታገሉ፣ እባካችሁ ልጄ አለችላችሁ ብሎ የለመነውን አባት እንዴት እረሳዋለሁ? ጋይንት በተደፈሩ ማግስት ልጅ ወልደው ታቅፈው ያገኘኋቸውን እናቶች፣ ተዟዙሬ ያናገርኋቸውን 16 እንስቶች የአካልና የልብ ስብራት በምን እገልፀዋለሁ? የጋይንቱን የ8 ዓመት የአእምሮ ዘገምተኛ ልጅ (አንድ ጥይት በጭኑ አንድ ጥይት በጫንቃው ተመቶ) የተረፈውን እንዴት እረሳዋለሁ?
“እባካችሁ ልጄን ተውልኝ፣ ሌላ ሰው የለኝም” በማለቱ የገደሉትን የዋድላውን ዓይነስውር፣ ጫካ ወስደው ደፍረው ከሳምንት በኋላ የመለሷትን መሪውን ልጁን እንዴት መርሳት ይቻላል? ግብረሰዶም የተፈፀመበት የ9 ዓመቱ ልጅስ? የመነኮሳቱ ጉዳይስ? የቱን አንስቼ የቱን ልተወው?! ትህነግ ያላፈረሰው የሀይማኖት ህግ፣ ያላቆሸሸው ማህበራዊ ወግ የለም።
9) ዓለምአቀፍ ህግጋትን መጣስ፡ አይነኬ የሆኑ ሃይማኖታዊና የሕዝብ ተቋማትን አውድሟል፣ ደፍሯል። ዓለምአቀፋዊ ግብረሰናይ ድርጅቶችን ለጦርነት ተጠቅሟል። ለአብነት የዓለም ምግብ ፕሮግራም አልሚ ምግቦችንና ዱቄት ለጦርነት ተጠቅሟል። መኪኖችን ለውጊያ ተጠቅሟል።
10) ማኅበረሰባዊ መተማመንን (Social Capital) መሸርሸር: የአማራ ሕዝብ አብሮ ተዛምዶ፣ ተዋልዶና ተጎራብቶ ከኖራቸው የትግሪኛ ተናጋሪ ወገኖቹ ጋር በጥርጣሬና በጥላቻ እንዲተያይ አድርጓል። አስርጎ እያስገባም ብዙ ማኅበረሰባዊ መናጋቶች ፈጥሯል።
በአጠቃላይ ትህነግ ፈጣሪ ኢትዮጵያን ሊቀጣ አስቦ ወደ ጥልቁ ከተጣሉት ከሳጥናኤል ነገዶች መካከል መርጦ ያመጣው የጉግማንጉግ ስብስብ ነው። ትህነግን ለማጥፋት የሚደረግ ማንኛውም ነገር ቅዱስ ነው። ችግሩ ግን ከኑግ ጋር ያለች ሰሊጥ መሆኑ ነው። የትግራይን ወጣት በርዕዮተዓለምና በዕፅ በማደንዘዝ በእሳት አስጨረሰው። ደጋግ የትግራይ አዛውንቶችን የመከራ ማሳ አደረጋቸው።
ያም ሆነ ይህ ትህነግ ከምድረገፅ ካልተሰረዘ፣ በቀዳሚነት የአማራ ቀጥሎ የኢትዮጵያ ጉዳይ አደጋ ላይ ነው። የትግራይ ሕዝብ መከራም በባሰ መንገድ ይቀጥላል።
(ማሳሰቢያ: ባለፈው አመት በካሜራ ያስቀረኋቸው የአንድን ብሔር ስም ዝቅ የሚያደርጉ የስድብ ምስሎችን በመለጠፌ ከወዲሁ ይቅርታ እጠይቃለሁ)
(የጎልጉል ማሳሰቢያ፤ ጸሐፊው ህውሃት ብለው በጽሁፋቸው የተጠቀሙትን ቃል ትህነግ በሚለው ቀይረነዋል። ትህነግ በአማርኛ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር ማለት ነው። ሌላው ጸሐፊው ለጽሁፉ የሰጡት ርዕስ “የትህነግ 10 በደሎች፡ በተለይ በአማራ ሕዝብ” የሚል ነበር።)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Tesfa says
የሞተ አስተሳሰብ ቆሞ በራሱ አምሳል የሚሄድን ሰው ” አህያ” ብሎ የሚጠራ ነው። የወያኔ ክፋት በራሳቸው የቀድሞ ታጋዪች ሳይቀር የተነገረና የተጻፈ በመሆኑ እዚህ ላይ እንዲህ እና እንዲያ ማለቱ ሰውን ማሰልቸት ይሆናል። በቅርቡ እምኖርበት መኖሪያ ድረስ ወደ አራት የሚሆኑ በ Toyota RAv4 ሆነው ቤቴንና አካባቢውን ለመለየት አይናቸው ይቀላውጣል። ያላወቁት ነገር በከፍታና በማይታይ ስፍራ ላይ ያለው ካሜራ ሁሉን እንቅስቃሴአቸውን ይመዘግባል። አልፎ ተርፎም መኪናቸውን ወደ ቤቴ driveway አስጠግተው ሲመለሱ በመኪናው ውስጥ የሚሉትን ሁሉ ካሜራው ያስቀራል። ይህም ጉዳይ ለሚመለከተው የህግ አካል ይተላለፋል። እነዚህ የወያኔ ሽንኮች በምንም ሂሳብ ያለ እነርሱ እውቀትና ብልሃት ያለው፤ የታጠቀና ደፋር ሰው ያለ አይመስላቸውም። በደቦ ሰውን በሃገር ውጭና በሃገር ውስጥ የሚቀጠቅጡት እነዚህ ሙታኖች የራሳቸውን ቤት አቃጥለው መጠለያ የሰጧቸውንም ሃገሮች እያመሱ ይገኛሉ።
ከጦርነት የሚገኘው ሞትና ረሃብ የሰው ጉስቁልና መሆኑን እያወቁ በሃሳብና በገንዘብ ወያኔን የሚደግፉ ሁሉ ምን ያህል በሰው ህይወት እንደሚጫወቱ አይታያቸውም። ጀግንነት ሰውን ከመከራ መታደግ ነው። መከራን እንደ እህል ከሚዘራ ድርጅት ጋር እንዴት ጭንቅላት ያለው ሰው አብሮ ይሰለፋል? የስንቱ ሰው ህይወት፤ የስንቱ ቤት ከፈረሰ በህዋላ ነው ሰላምን ሰላም ነው የምንለው? የተካደው የሰሜን እዝ የተሰኘውን መጽሃፍ ላነበበ ሰው ጭራሽ ከሰው ተራ የወጡ አረመኔዎች መሆናቸውን አይን እማኞች አስረግጠው ያስረዳሉ። ጭካኔ፤ ዘረፋ፤ ሸርና ተንኮል የወያኔ የመኖሪያ ብልሃት መስፈርቶች ናቸው። ኢትዮጵያዊ መሆን አልፈልግም ካልክ ማን ያስገድድሃል? ትግራይን ሃገር አድርጋለሁ ካልክ ጠቅሎ መቀሌ መግባት ነው። ዋሽንግተንና ቦን ላይ ተቀምጦ ማቅራራት የድሃ ልጅ ለማስፈጀት ነው። የወያኔው የቁም አገልጋይ እስታሊን የሚለውን በረጋ መንፈስ ላዳመጠ የፈጠራ ወሬው ራሱን አዙሮ ሲጠልፈው የአረፍተ ነገሩ መጀመሪያና ማለቂያ ሲጣረሱበት ለሰማ ሰው ይህን ያህል ህሊናውን ይሸጣል ያሰኛል። እንዳጋጣሚ ሆኖ የራሺያው ጆሴስ ስታሊን ይጠቀምባቸው ከነበረው ዋና የፓለቲካ መሳሪያ “ወሬን ማወናበድ ወይም Misleading information ነበር። ወያኔም በዚህ የተካነ ነው። ክፍለ ጦር ደመሰስኩ፤ ያለፈ የወታደር ቪዲዪ እያሳየ ትላንት የተማረኩ ይላል። ያኔ ሰራዊቱ ዳግመኛ እያጠቃ መቀሌ ሲደርስ ጄ/ባጫን ገደልን በማለት ስንቶችን አሞኝቶና እልል እያሰኘና ጥይት ወደ ሰማይ እያስተኮሰ በጎን እነርሱ ወደ በረሃ ነበር የሸሹት። ይህ ድርጅት ነው ለትግራይ ህዝብ ቆሜአለሁ የሚለው። ወያኔ የአማራ ህዝብ ጥላቻው ሥፍራ የለቀቀ ነው። ይህ ደግሞ ራሱንና ህዝቡን ከጅምሩ ጀምሮ በሃሰት የፓለቲካ መርዝ ስለጋተው ጠጋ ብሎ እውነት የተነገረን እውን ነው ወይ ብሎ የሚጠይቅ የለም። ዝም ብሎ መትመም ነው። በስሜት፤ በፉከራ፤ በቀረርቶ፤ በሙዚቃ፤ በመሳሪያ ትጥቅ እየተነድ ወደ ሞት መጓዝና እየገደሉ መሞት። ይህ እውቀት ሳይሆን ድንቁርና ነው። ወያኔ ሌላው ቀርቶ በስደተኛ ካምፕ ውስጥ ያሉ ሰዎችን እንኳን አሰልጥኖ በማስታጠቅ ወደ እሳት የሚማግድ መሰሪ ድርጅት ነው። ብዙዎቹ የትግራይ ልጆች መርጠው አይደለም ውጊያ የሚገቡት። ምርጫ አጥተው እንጂ። ስለሆነም ወያኔን ከስሩ ለማጥፋት የትግራይ ልጆች ቀዳሚውና ዋናው ተፋላሚ መሆን አለባቸው። ከውጭ የሚደረጉ ግፊቶችን ሁሉ ወያኔ የትግራይ ህዝብ እንደተገፋ አድርጎ ስለሚጠቀምበት ፍሬ አያፈራም። የትግራይ ህዝብ ሆ ብሎ በመነሳት ራሱ ከታገላቸው ግን መደበቂያ አይኖራቸውም። ስንቱን ገድለው ይጨርሳሉና!
ግራም ነፈሰ ቀኝ እዚህም እዛም ወያኔ የጻፋቸውን (ግድግዳም ሆነ ሌላ ላይ)፤ ያወደመውን፤ የገደላቸውን፤ ያቆሰላቸውን፤ የሰረቀውንና ዘርፎ ያጓጓዘውን መዝግቦ መያዙ ለአሁ እና ለወደፊቱ ትውልድ ጠቃሚነት ይኖረዋል። ለምን፤ እንዴት፤ እና ሌሎችንም ጥያቄዎች መርምሮ ትምህርት ሊያገኝበት ይችላል። በቀረው የአሜሪካና የአውሮፓ የኢትዪጵያን መንግስት ማስፈራራት፤ የወያኔ ጀሌዎች በውጭና በውስጥ ሰውን እየለዪ ማስፈራራትና መደባደብ (አሁን እንደሰማሁት እንግሊዝ ሃገር ውስጥ ኤርትራዊያንን ለማጥቃት ሙከራ እንዳደረጉና በፓሊስ እየታደኑ እየተያዙ እንደሆነ ሰምተናል) አጉል የኋላቀርነት ምልክት እንጂ ሙግቱ መሆን የነበረበት በክብ ጠረጴዛ ላይ በሃሳብ ነበር። ግን እጃቸው በሰው ደም የጨቀየና በዘረፋ ሃብትና ንብረት ያካበቱ እና የወያኔ ዝንተ ዓለም ፍርፋሪ ለቃሚዎች አለቃቸው ወያኔ ያዘዛቸውን ከመፈጸም ወደ ኋላ አይሉም። ጠንቀቅ ነው። በቃኝ!
Tesfai Habte says
ወያኔ ለኣማራ ህዝቢ ብቻ ኣይደለም ጠላት። መጀመርያ ከህዝቡ የተጣላ ኣውሬ ቡድን ነው። ሌላው ክመላው የኢትዮጵያ ህዝብና ከኣፍሪካ ቀንድም የተጣላ ኣስመሳይና ተላለኪ ነው። ኣንድ ነገር ልነግርህ ኣንዲት የትግራይን ልጅ የቤት ሰራተኛ ነበረችን። ይህቺ ሴት ኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ከተጀመረ በቀይ መስቀል ወደ ሃገርዋ የሄደች ሴት ናት። ስትነግረኝ ” የኛ ሰው ቕመኛ እና የሌላ ሰው ሃብት ብዓይ ቆራኛ የሚመለከት መጥፎ ነው። የገዛ ቤተሰቡ እንኳን ንብረት ለመውሰድ ወድሙን ይገድላል። ለትዳር ሲወስን ሃብትን ከምንም ሰርቆ ወይም ሰው ገድሎ ሃብቱን ቀምቶ ልብቻው ለመኖር የሚፈልግ ሰው ምሁኑን ትናገር ነበርች። ይህ ጠሩነቱ ሲጀምር በማግስቱ ነው። መስረቅ፡ መገደል፡ መዋሸት፡ ማታለል፡ የወያኔውች ኣንድኛው ስራው ነው። ባህሉ ነው። ብግራኝ ዘመን ብዮዲት ጉዲት፡ የጣልያን ባንዳን፡ ብተጋዮች ኢሃፓ፡ —-የመሳሱሉና፡ ብየኢትዮጵያ ሰራዊት ለምን ስለምን ይህ ያህል ውዲት ኣደረገ ሲባል፡ ተፈጥራዊ ባህሪው ነው። ብ1975 ዓ.ም በኤርትርራ ብደርግ ዘመን ሰው ብግፍ ሲጨፈጨፍ ዋናው መሪና ተዋናይ የወያኔ ሰዎች ነበሩ። በጥልያን ለስራ የገቡ፡ የበለጸጉ ብሃላ ግን የኤርትራን ባህል ተላብሰው ሰውን የሚገድሉ የሚያስገድሉ እኒዚ ሰዎች ነበሩ። ተራ ሰራተኛ የነበረ ለሚያሰራው ሃብትም ሰው ብጥቅማ ጥቅም ያስገድላል። ለመግደል ያስተባብራል። በተፈጥሮ ሃይማኖት የሚባል ነገር የላቸውም። የኤርትራ ህዝቢ በነዚህ ሰውች በጣም ተቆሳቁለዋል።