• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ከ፴ ዓመት በኋላ በሰፈሩት ቁና መሰፈር እንደ ትህነግ

October 24, 2022 10:37 am by Editor Leave a Comment

አደራውን ለባለ አደራው ሰጥተው የልማት ሥራዎችን እየተዘዋወሩ የሚመለክቱትና የአረንጓዴ ዘመቻ መመሪያ እየሰጡ ያሉ ዐቢይ አሕመድ ከአዲሱ ዓመት ጀምሮ የወትሮ ጭንቀትና ያለመመቸት ስሜት ፊታቸው ላይ አይታይም። በመንግሥት የዘመኑ ዕቅድ ላይም በተያዘው ዓመት አስተማማኝ ሰላም እንደሚሰፍን ተመልክቷል። ዐቢይ አህመድ ለበዓላት ባስተላለፉት መልዕክቶቻቸውና በፕሮጀክት ምረቃ ላይ “አትጠራጠሩ የሰሜኑ ጦርነት ያበቃል” ብለዋል።

“አሁን” ሲሉ መረጃ የሰጡ ወገኖች “አሁን የሰኞው ንግግር ልክ እንደ 1991ዓም (እኤአ) ድርድር ዋጋ የለውም። ምክንያቱም የትህነግ አመራሮች ጊዜ የሚፈጁበት አንዳችም የድርድር ቀብድ የላቸውም”። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ቴድሮስ አድሃኖም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ደውሎ መማጸኑ ተሰምቷል። ምላሽም አግኝቷል።

ከመቀሌ ውጪ ቀሪዋ ትልቅ ከተማ አዲግራትና አድዋ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የሚናገሩ ወገኖች ጦሩ በመቀሌ ቅርብ ርቀት ላይ እንደሚገኝ መረጃ ሰጥተዋል። ይህንኑ ተከትሎ በአዲስ አበባና በውጭ አገራት የሚገኙ የትህነግ ደጋፊዎች “ለዚህ ነው እንዴ ይህ ሁሉ ሰው ያለቀው” የሚል ጥያቄ የትህነግ አመራሮች ላይ እያነሱ እንደሆነም ተሰምቷል። ጥያቄው እየተነሳ ያለው ትህነግ ዋስትና ጠይቆ በሰላም ትጥቅ ለመፍታት እየተማጸነ መሆኑንን በውስጥ ለውስጥ ግንኙነታቸው መስማታቸውን ተከትሎ ነው።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተርና የትግራይ አክቲቪስት ቴድሮስ አድሃኖም “የዲፕሎማሲ ቃላት አልቀውብኛል። እኔ ተጋሩ ነኝ። ጄኖሳይድ በትግራይ ጠብቁ …” ሲል በተናገረና ቪዲዮው በተሰራጨ የቀናት ልዩነት ውስጥ ስልክ ደውሎ በሰላም ትጥቅ የሚፈቱበትን ሁኔታ እንዲመቻች መጠየቁ ትህነግ በአቋም ደረጃ ትጥቅ ለመፍታት መወሰኑንን ተከትሎ ነው። ጠቅላይ ሚንስትሩ ጥቂት አድምጠው ለወዲ አድሃኖም ምላሽ ሳይሰጡ እንዳሰናበቱት በስፍራው የነበሩ ለኢትዮ12 ነግረዋል።

የመንግሥት ኃይሎች በገቡባቸው ከተሞች ሕዝቡ ከተነገረውና ይሆናል ብሎ ከጠበቀው በተቃራኒ ስለተደረገለት፣ የተቋረጡ አገልግሎቶች ዳግም እንዲጀመሩ ርብርብ መጀመሩ፣ በየመጋዘኑ የተከማቸ እህል እንዲከፋፈል መደረጉ፣ በትግራይ ነገሮችን እንደቀየረና ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

“ከውጭም ሆነ ከውስጥ በትህነግ ተስፋ የቆረጡ ቁርጠኛ አቋማቸውን በገሃድ ባያስታውቁም፣ ነገሮች ሁሉ መገለባበጣቸውን እያመኑ ነው” ሲሉ የሚናገሩ፣ በዚህ ስሜት ላይ የመንግሥት ጦር አዲግራትን መቆጣጠሩ በደቡብ አፍሪካው ንግግር ትህነግን ከሚወክሉ አካላት ጋር ምን ዓይነት ስምምነት እንደሚደረግ ከወዲሁ መገመት አዳጋች እንዳልሆነ እየገለጹ ነው።

ትህነግ ዛሬ ላይ መሟገቻ፣ ማኩረፊያ ወይም መነጋገሪያ አጀንዳ ሊያቀርብ አለያም ሊመርጡ እንደማይችሉ በመረዳት ነገሩ እንዳበቃለት የሚገልጹ እ ኤ አ 1991 ለንዶን ላይ ከኢህአዴግ ጋር ድርድር ሲደረግ አሜሪካኖች በጓሮ የኢትዮጵያ ጦር ጠመንጃውን እንዲያወርድ አስደርገው ነበር። ድርድሩ ሲደረግ ከሰሜኑ አካባቢ ውጭ ያለው የአገሪቱ ክፍል ሰላም ነበር። ነገር ግን መንግሥት ራሱ ላይ ሽንፈት እንዲያውጅ ተደርጎ የትህነግ ወንበዴ ታጣቂዎች በቀላሉ ሰላምና መረጋጋት ኮሚቴ በማቋቋም ሥልጣናቸውን እንዳጠነከሩ በማስታወስ በርካቶች የነገሮችን መመሳሰል ከልዩነቱ ጋር አጣምረው እየገለጹ ነው።

ልዩነቱ መንግሥት የትግራይን ሰባ ከመቶ በላይ ተቆጣጥሮ ነጻ የማውጣት ሥራውን እየገፋበት ነው። አሁን ላይ ጥምር ጦሩ አዲግራትን ተቆጣጥሯል። ከትህነግ ወገን በይፋ መግለጫ ባይወጣም አክሱምና አድዋ አልተያዙም የሚል ማስተባበያ ቢያንስ በቢቢሲና በቪኦኤ ወይም በጀርመን ድምጽ አላሰማም።

ጦሩ አሁን ላይ ካለው ግስጋሴ አንጻር በደቡብ አፍሪካ በሚካሄደው ንግግር ትህነግን የሚወክሉ ኃይሎች ማስቀረት የሚችሉት ነገር ቢኖር ሞት እንዲቀንስ በይፋ ትጥቅ በማውረድ የትግራይ ህጻናት ወደ ሰላማዊ ኑሯቸው እንዲመለሱ ጥሪ ማድረግ ብቻ እንደሆነ በስፋት እየተሰማ ነው። ይህንንም ለማድረግ ምን አልባትም በውይይቱ ይሳተፋሉ የተባሉት የወንበዴው ቡድን አመራሮች እነ ብርሃነ ገብረክርስቶና የቲዲኤ ኃላፊ አክሊሉ ከዚህ አንጻር ለራሳቸው የሚሆን ታሪካዊ ውሳኔ ሊያስተላለፉ እንደሚችሉ ይጠበቃል።

የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር በሚል ስያሜ ሃያ ሰባት ዓመታት ሥልጣን ላይ የነበረው ትህነግ፣ ያለው ተዋጊ ኃይል ድምጥማጡ መጥፋቱን አሌክስ ዲዋል ማስታወቁ አይዘነጋም። ጌታቸው ረዳ ግን “አደገኛ ምት አሳርፈናል|” ሲል የትህነግ ወንበዴና ዘራፉ ኃይል በመልካም ቁመና ላይ እንደሚገኝም በመናገር ሲያሻቸው ቆቦን ዳግም፣ ወይም ደሴን መያዝ እንደሚችሉ ሲናገር እንደነበር የሚያስታወሱ “መቀለ ያሉ አመራሮች ለጊዜው መሸሸጊያ ወደሚሉት አካባቢ እየሸሹ እንደሆነ ሰምተናል” ብለዋል።

በመጨረሻም እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንደሚሉት ትህነግ ትጥቅ ለመፍታት መስማማቱ ነው። ትህነግ ከዚህ ውሳኔ የደረሰው ቀደም ሲል ተይዞ የነበረው የንግግር መርሃ ግብር ትህነግ መንግሥትን ከነሙሉ ህገ መንግስታዊ ባህሪው ጋር እንዲቀበል በአደራዳሪዎች የቀረበለትን ጥያቂ “አልቀበልም” ማለቱ ስለማያዋጣ “እኔም እንደመንግሥት በእኩል ደረጃ ልታይ” ሲል ያቀርበው ጥያቄ ውድቅ ከተደረገበት በኋላ ነው።

መጀመሪያ ለንግግር ተይዞ የነበረው ዕቅድ የተሰረዘው ትህነግ ከመንግሥት እኩል ደረጃ ተቆጥሮ ለንግግር እንዲሰየም ያቀርበውን ጥያቄ መንግሥት ህግ ጠቅሶና ምክንያት ሰጥቶ እንደማይቀበል፣ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት በትግራይ በህግ የተቋቋመ አስተዳደር አለመኖሩን፣ የነበረውም ጊዜው ያበቃና በአገሪቱ ህግ መሰረት ምርጫ ያላካሄድ ህገወጥ አካል በመሆኑ “የትግራይ አማጺ” ተብሎ እንደሚጠራ በይፋ ያስታወቀው ከዚሁ ከትህነግ ጥያቄ በመነሳት ነው።

“የትግራይ መንግሥት፣ የትግራይ የውጭ ግንኙነት …” የሚሉ ስያሜዎች ዳግም ስራ ላይ እንዳይውሉ፣ ይህን ማድረግ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት መጋፋት እንደሆነ ጠቅሶ ለዓለምና አህጉር አቀፍ ተቋማትና አገራት የስያሜ ማስተካከያ ደብዳቤም መበተኑ ይታወቃል። የመጀመሪያው ንግግር የተደናቀፈበትን ምክንያት የገለጹልን እንዳሉት የመንግስትን ምላሽ ተከትሎ በዳኝነት የተመደቡት አካላት የትህነግን “እኩል ልታይ” ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸውን አመልክተዋል።

በጦር ሜዳ ውሎ መከላከያ የሚመራውን የጥምር ጦር መቋቋም ያቃተው የትህነግ ሃይል እየተበተነ ባለበት በአሁኑ ወቅት የመቀሌ መያዝ ንግግሩ ላይ ብዙም የሚነሳ መከራከሪያ እንደማይኖር አመላካች ሆኗል።

የፌደራል መንግሥቱ በትግራይ የሚያደርገውን የአየር ማረፊያዎችንና የፌደራል ማዕከላት የመቆጣጠር ወታደራዊ ዘመቻውን እንደሚቀጥል በገለጸበት መግለጫው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በውይይት ለመፍታት አሁንም ቁርጠኛ ነኝ ሲል ግዛቱን እንደሚያሰፋ አመልክቷል።

የትግራይ አማጺ ኃይሎች ከፍተኛ አመራር ክንድያ በጽሁፍ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንዳስታወቀው በአፍሪካ ህብረት አነጋጋሪነት ሰኞ ጥቅምት 14 ቀን በደቡብ አፍሪካ ሊደረግ ቀጠሮ በተያዘለት የሰላም አማራጭ ንግግር መድረክ ላይ እንደሚገኙ አረጋግጧል። ይሁን እንጂ እነማን በንግግሩ ላይ እንደሚወከሉ ቀድሞ ከተነገረው ውጪ ያስታወቀው ነገር ስለመኖሩ ኤኤፍፒ በጽሁፍ ደረሰኝ ባለው መረጃ ላይ ስለመካተቱ ያለው ነገር የለም። ይህንኑ ዜና ተከትሎ ከትግራይ ለንግግር የሚወጡ አመራሮች እንደማይኖሩ እየተገለጸ ነው። በሌላ ቋንቋ ሰኞ ንግግሩ ላይ የትህነግ ሰዎች በውጭ አገር ክንፎቻቸው አማካይነት ካልሆነ በስተቀር የመወከላቸው ጉዳይ ያመነመነ ነው።

በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል እየተካሄደ ያለው ደም አፋሳሽ ጦርነት በሰላም ለመቋጨት ያስችላል የሚል ሰፊ ግምት በተሰጠው ንግግር መልካም ዜና ለመስማት ዜጎች በጉጉት ይጠብቃሉ። ትግራይም ዳግም ወደ ነበራት ሰላም ተመልሳ ከጎረቤት ክልሎች ጋር በመልካም መንፈስ እንድትቀጥል፣ አገሪቱም ወደ ልማት ፊቷን እንድታዞር መንግስት ከአሸናፊነት ስሜት ወጥቶ ለሰላም ያለውን ቁርጠኛነት እንዲያረጋግጥ የሚያሳስቡ “በምንም ይሁን በምን ጦርነት ይብቃን” እያሉ ነው። ትህነግን እዛም እዚህም በውክልና የሚያራምደውን ሽብር እንዲያቆም ቢያንስ እያስጨረሰው ላለው የትግራይ ሕዝብ ሲል እንዲያበቃ ሕዝብ ትናንትና ዛሬ አደባባይ ወጥቶ ጠይቋል።

አሜሪካ በአፍሪካ ህብረት የበላይነት የሚካሄደውን የሰላም ንግግር እንደምትደግፍ ስታስታውቅ “እልባት ይመጣል፣ ሰላም ይወርዳል” የሚል እምነት እንዳላት በማስታወስና ሙሉ ድጋፍ እንደምታደርግ በማረጋገጥ ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ የሆኑት አቶ ሬድዋን ኢትዮጵያ በንግግሩ ላይ እንደምትገኝ ሲያስታውቁ የአገር ሉዓላዊነት የማስጠበቁ ተግባር እንደሚቀጥል ጎን ለጎን መግለጻቸው ይታወሳል። እሳቸው ይህን ካሉ በኋላ አክሱምና አድዋን ጨምሮ ጥምር ጦሩ ይዞታውን እያሰፋና ወደ መቀሌ ማምራቱ ቀጥሏል።

አዲግራት እስካሁን ውጊያ ያልተደረገበት በመሆኑ የትህነግ ኃይሎች የመጨረሻ አቅማቸው እዛ ላይ እንዳለ አሰላለፉን የሚያውቁ ግልጸዋል። ይሁን እንጂ የመንግስት ሃይሎች አዲግራት ለመግባት ብዙም እንዳልተቸገሩ አመልክተዋል። አሁን ባለው ቀሪ የመቀሌ ኦፕሬሽን ላይ ምን አላባትም የንግግሩ ጠቀሜታ ፋይዳ ሊኖረው ይችላል። እየተገፋና ቀለበቱ እየጠበበት ተከማችቶ ከተማ ውስጥ ያለው ሃይል እጁን በሰላም እንዲሰጥ ማድረግ ትህነግን ወክለው ከሚገኙት ሃይሎች የሚጠበቅ መንግስትም የሚጠይቀው ጥያቄ ነው።

“ትግራይ ሰላም ካልሆነች ኢትዮጵያ ሰላም አትሆንም” ሲል ያስታወቀው ትህነግ ትጥቅ እንዲፈታ ከመንግስት በአገሪቱ ህግ መሰረት የቀረበለትን ጥያቄ መቀበሉን እንደሰሙ የሚገልጹ ወገኖች መልካም ዜና ይጠብቃሉ። የትግራይ እናቶችና ሕጻናትም የሰላም አየር ናፍቋቸዋል። አዛውንቶች እረፍት ናፍቋቸዋል። አፋርና አማራ ክልልም ነገ ከዛሬ ዳግም ወረራ ስጋት እየሆነባቸው መኖር መሯቸዋል። የውክልና ነውጥ የሚፈጥሩ አካላት በየአካባቢው ዘር እየለዩ የሚያደርሱት ጥቃት እንዲቆም ሕዝብ ጠይቋል። እናም ተነጋጋሪዎች ቢያንስ በህይወታቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ከስልጣን ጥማትና እብደት ነጻ ሆነው ለህዝብ ስቃይ መፍትሄ እንዲያበጁ የሁሉም ዜጎች ጥሪ ነው። ባከተመ ጨዋታ መንፈራገጥ አሁን ላይ ህይወት ከማጥፋት፣ ንብረት ከማውደምና ጣርን ከማስቀጠል የዘለለ ረብ አይስገኝም።

የሰላም አማራጭ ንግግሩ ሰፊ እድል ይዞ እንደሚመጣ ከወዲሁ የሚተነብዩ ኢትዮጵያ ሌቦችን ታድናለች። ተከፋዮች ወደ መደበኛ ህይወታቸው ይመለሳሉ። መንግስት ከሰላም ባሻገር ራሱን ያጸዳል። የጸረ ሌብነት ዘመቻው ሰይፉን ያነሳል። ይህ እንዳይሆን ሲያሴሩ የነበሩ ሁሉ ተስፋ ይቆርጣሉ። እዛም እዚህም ሽብርና ግድያ ላይ የተሰማሩ ያበቃላቸዋል።

ዛሬ ሬውተርስ በዘገበው መሠረት የአሜሪካ የጦር አውሮፕላን የተገንጣይ ቡድኑን አባላትና የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ኃላፊ ማይክ ሐመር ይዞ ደቡብ አፍሪካ ማረፉን ተናግሯል። ሁኔታውና ድባቡ የዛሬ ፴ ዓመት አካባቢ ሎንዶን ላይ ኸርማን ኮህን ኢትዮጵያን አደራድራለሁ ብሎ ለወንበዴው ቡድን አሳልፎ የሰጠበትን ሁኔታ የሚያስታውስ ሆኗል። የዚያን ጊዜው ተደራዳሪዎች አገር አለን ብለው ከአዳራሹ ሲወጡ ነበር ወንበዴው ቡድን አገር እንዲረከብ በተነገረው መሠረት ወደ አዲስ አበባ የገባው። መቀሌ በየአቅጣጫው ተከብባ ባለችበት ባሁኑ ወቅት የደቡብ አፍሪካው ሁኔታ ሁሉ የሎንዶኑን ድርድር የሚያስታውስ ሆኗል።

የፖለቲካ ተንታኙ ስዩም ተሾመ እሁድ ዕለት በማህበራዊ ት ሥሥር ገጹ እንዳለው ወደ ደቡብ አፍሪካ የሄዱት የወንበዴው መሪዎች ወደ ካናዳ ሄደው የስደት ኑሯቸውን ይቀጥላሉ የሚል ፍንጭ ሰጥቶ ነበር። ይህንን ተከትሎ የደቡብ አፍሪካው ጉዳይ እየተካሄደ ባለበት ሁኔታ ዛሬ ረፋዱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከካናዳው ጠቅላይ ጋር በስልክ ውይይት አድርገዋል።

ከደቡብ አፍሪካው ንግግር በኋላ ወንበዴው ትህነግ የዛሬ ፴ ዓመት የኢትዮጵያን ሠራዊት እንደበተነው እሱም “የትግራይ መከላከያ” እያለ የሚጠራው ታጣቂ የወንበዴ ስብስቡ ይበተናል። ተደራዳሪዎቹ አገር አልባ ሆነ ለስደት እንደተዳረጉት አሁን ደቡብ አፍሪካ የሄዱት የወንበዴው ተወካዮች መድረሻቢስ ሆነው በየምዕራቡ አገር በስደት ኑሯቸውን ይቀጥላሉ። “በሎም” እያሉ ያስፈጁት ሕዝብ ደም ቀን ተሌት ዕረፍት እየነሳቸውና አፋቸውን ደም ደም እያላቸው ተቅበዝባዥ ሆነው በዳያስፖራ በሚኖረውና ባታለሉት የትግራይ ተወላጅ ተጠልተው ኢትዮጵያን ለመበታተን እንደሞከሩት እነርሱም እንዲሁ ተበታትነው ቀሪ የመከራ ዘመናቸውን ይቀጥላሉ። የትግራይም ዕጣ ፈንታ በዚሁ የሚታይ ይሆናል። በሠፈሩት ቁና መሠፈር ማለት ይኸው ነው።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Politics, Slider Tagged With: ethiopian terrorists, mike hammar, operation dismantle tplf, tplf, tplf terrorist

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm
  • አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን March 15, 2023 08:52 am
  • ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ March 15, 2023 08:48 am
  • በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ March 15, 2023 01:43 am
  • ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ March 15, 2023 12:52 am
  • አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች  March 10, 2023 10:45 pm
  • ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ March 2, 2023 09:56 am
  • በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ? March 2, 2023 09:43 am
  • አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት February 24, 2023 10:44 am
  • በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል February 24, 2023 08:39 am
  • የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ! February 24, 2023 08:19 am
  • “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ February 21, 2023 10:09 am
  • አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ February 21, 2023 10:01 am
  • በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት February 17, 2023 06:39 pm
  • ኦነግ ሸኔ አሸባሪነቱ ሳይነሳለት በሽመልስ የሰላምና የእርቅ ጥሪ “በክብር” ቀረበለት February 17, 2023 12:35 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule