• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የጥቁር አንበሳ ዕጩ መኮንኖች (ካዴቶች) ተመረቁ

May 29, 2022 04:01 pm by Editor Leave a Comment

የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ ለ69ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን “የጥቁር አንበሳ” ዕጩ መኮንኖችን አስመረቀ። ተመራቂዎቹ “የጥቁር አንበሳ” መባላቸው በምዕራባዊያንና በውስጡ ነበሩ በተባሉ “ካሃዲዎች” የተበተነውን ታላቁን የኢትዮጵያ መከላከያ ያስታወሰ መሆኑ ልዩ ስሜት የሚሰጥ እንደሆነ ምርቃቱን ተከትሎ አስተያየት ተሰጥቷል።

“ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም በሚል ቁጭት ነው ኢትዮጵያን የሚመጥን የመከላከያ ኃይል ለመገንባት እየሠራን ያለነው” በማለት የጦር ኃይሎች ም/ጠ/ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ በተናገሩ ማግስት፣ አዳዲስ መኮኖች መመረቃቸው፣ ጀነራሉ በንግግራቸው የሚገነባው ኢትዮጵያን የሚመስልና የሚመጥን ሰራዊት ዘመናዊና ቴክኖሎጂን የተላበሰ፣ በምሁራን የተገነባ እንደሚሆን ካመላከቱት ጋር ተያያዥ ሆኗል። ተመራቂዎቹ የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ ያላቸው፣ በራሳቸው ተነሳሽነት ከሲቪል የስራ መስካቸው ወደ ውትድርና ያመሩ ተተኪ መኮንኖች መሆናቸው ታውቋል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት መኮንኖች ኢትዮጵያዊ ጀግንነት፣ ከሀገር ፍቅርና ከሕገመንግሥቱ የሚቀዳ ዓላማና ሁለገብ ዕውቀት ሊኖራቸው እንደሚገባ የጠቀሱት ደግሞ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አሕመድ ናቸው። ይህንንም ያሉት በምረቃው ሥነሥርዓት ላይ ነው።

በተከታታይ በወታደራዊ ሳይንስና ትምህርት የሰለጠኑ፣ በሜካናይዝድና ኢንተለጀንስ የተሠሩ አዳዲስና ወጣት ሙያተኞችን እያካተተ ያለው የመከላከያ ሠራዊት ውጊያን በትንሽ ኪሣራ፣ በአጭር ጊዜ ማጠናቀቅ እንዲችል ተደርጎ እየተሠራ መሆኑ በተደጋጋሚ ሲገልጽ እንደነበር ይታወሳል።

በ1983 የኢትዮጵያ መከላከያ “የደርግ ሠራዊት” ተብሎ እንደተበተነው ሁሉ በቅርቡ ትህነግ አማራና አፋር ክልልን ወሮ በነበረበት ወቅት “እጃችሁን ለትግራይ ኃይልን ስጡ” በሚል ጥሪ ሲቀርብለት የነበረና ወረራውን በአጭር ጊዜ ራሱን አደራጅቶ የቀለበሰና ልምድ ያካበተ እንደሆነ ከፍተኛ መኮንኖች ሲያስታውቁ ቆይተዋል። በወቅቱ የትህነግ አመራሮች ይህ በአዲስ እየተደራጀ ያለውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት “የዐቢይ ሠራዊት” በማለት ዳግም እንደሚያፈርሱት ሲዝቱ እንደነበር ይታወሳል።

የምረቃውን ሥነ ሥርዓት አስመልክቶ በታተሙ ምስሎች ለመረዳት እንደተቻለው የቀድሞ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አዛዥ የነበሩትና የኅብረተሰባዊት ኢትዮጵያ የጀግኖች ጀግና አንደኛ ደረጃ ኒሻን የተሸለሙት ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ኃብተማርያምና ሌሎች ዕውቅ የቀድሞ ባለኮከብ መኮንኖች በሥነሥርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።

ዛሬ የመንግሥት መገናኛዎች እንዳሉት የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ 69ኛ ዙር የጥቁር አንበሳ ኮርስ የሲቪል ወታደራዊ መኮንኖችን በምክትል መቶ አለቃ ማዕረግ ዛሬ አስመርቋል። በመርሀ ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አሕመድ፣ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ እና የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ተገኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተመራቂዎች ባስተላለፉት መልእክት የሀገር መከላከያ ሠራዊት መኮንኖች ኢትዮጵያዊ ጀግንነት፣ ከሀገር ፍቅርና ከሕገመንግሥቱ የሚቀዳ ዓላማና ሁለገብ ዕውቀት ሊኖራችሁ ይገባል ብለዋል።

የነገ የሀገር ኩራት ጄኔራሎችና ሀገር መሪዎች መሆናችሁን በቅጡ በመረዳት ለዓላማችሁ የምትታትሩ፣የምትተጉና ከቀድሞ የጦር መሪዎች ተምራችሁ የምትሠሩና የምታሠሩ መሆን ይጠበቅባችኋል ሲሉ አሳስበዋል።

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ብርሀኑ ጁላ፤ የዛሬ ተመራቂዎች የተሰጣቸውን ሥልጠና በብቃት በመወጣት የመከላከያ ሠራዊት አባል መሆን የቻሉ መኮንኖች መሆናቸውን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ችግር ውስጥ በገባችበት ወቅት ሀገራቸውን አስቀድመው በአስቸጋሪና ውስብስብ ስልጠና ተፈትነው ያለፉና ለምረቃ የበቁ መኮንኖች መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።

የ69ኛ ተመራቂ መኮንኖች አብዛኞቹ የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩበት ሥራቸውን አቁመው በራሳቸው ተነሳሽነት እናት ሀገር ጥሪን ተቀብለው ሠራዊቱን የተቀላቀሉ ናቸው። (ኢትዮ 12)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: News, Slider Tagged With: black lion army, endf, ethiopian military academy, operation dismantle tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule