• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በትግራይ የ”ልጆቻችን የት ናቸው?” ጥያቄ እየተሰማ ነው

April 13, 2023 08:56 am by Editor Leave a Comment

ጦርነት ባሕላችን ነው፣ ተራራ ያንቀጠቀጠ ትውልድ፣ ወዘተ በሚሉ ባዶ ዲስኩሮችና ከንቱ ልፈፋዎች ትውልድን በስሁት ትርክት ሲነዳ የኖረው ትህነግ የሚፈራው ጥያቄ እየቀረበለት ነው። “ልጆቻችን የት ናቸው?” “ልጆቻችንን መልሰን ማግኘት እንፈልጋለን” ወዘተ የሚሉ የወላጆች ጥያቄ በትግራይ እየተሰማ ነው።

አቶ ገብረመስቀል አበበ የተባሉት ሌላኛው ነዋሪም የአንድ ወንድ ልጅ አባት ሲሆኑ “ከአንድ ቤት አንድ ሰው ወደ ጦርነት መግባት አለበት፣ ካልሆነ እርዳታ አይሰጠውሙ” በተባለ ጊዜ አንዱ ልጃቸው በግዳጅ ወደ ውጊያ ማምራቱን በሀዘን ድባብ ውስጥ ሆነው ነግረውናል። 

አሁን በተደረሰው ስምምነት መሰረት “ልጄ ከዛሬ ነገ ይመጣል እያልኩ በሀዘንና በተስፋ እገኛለሁ” የሚሉት አቶ ገብረመስቀል ልብ በሚሰብር ሁኔታ እያለቀሱ ልጄ ካለ መንግስት ምላሽ ይስጠኝ ሲሉ ይማፀናሉ።  

ወ/ሮ ለምለም ኃይሉ የመቀሌ ከተማ ነዋሪ ናቸው። ለሁለት ዓመታት በቆየው ጦርነት ሁለት ልጆቻቸው ወደበረሃ ወርደው ጦርነቱን እንደተቀላቀሉ ይገልፃሉ። ጦርነቱ በሰላም ስምምነት ተቋጭቶ ግልፅነት ይጎድለዋል የሚሉ አካላት ቢኖሩም አንፃራዊ ሰላም ሰፍኖ ክልሉም ጊዜያዊ አስተዳደር ተሹሞለታል። 

ይሁን እንጂ ወ/ሮ ለምለም ሁለት ልጆቻቸው እስካሁን ድረስ የት እንዳሉ እንደማያውቁ ገልፀው የልጆጃቸውን መገኛ በጉጉት እንደሚጠብቁ ነግረውናል። ከቤት በወጡበት ሰሞን ልጆቻቸው ደብዳቤ ይሉኩላቸው እንደነበር ለአዲስ ዘይቤ የተናገሩት አዛውንቷ፣ ለመጨረሻ ጊዜ የልጆቻቸውን ወሬ ከሰሙ 1 ዓመት ከ8 ወር ማለፉንም ገልፀዋል።

ወ/ሮ ለምለም ኃይሉ እንደሚናገሩት “ልጆቼን ለመፈለግ ያልደረሱስኩበት ቦታ የለም፣ መረጃ ላገኝ ግን አልቻልኩም” ብለው ወ/ሮ ለምለም ልብ በሚሰብርና ተስፋና ፍራቻ በተቀላቀለበት ሁኔታ ስለልጆቻቸው ይጠይቃሉ። 

በተመሳሳይ የመቀሌ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ሃረግ ተሰማ በተፈጠረው ጦርነት የአራት ልጆቿ አባት ወደ ጦርነት መቀላቀሉን ትገልፃለች። ባለቤቷ አቶ ግርማይ ፈቃዱ በመምህርነት እየሰራ ልጆቹንና ቤተሰቦቹን ያስተዳድር ነበር። 

ጦርነቱ ከጀመረ በኋላ በ2013 ዓ.ም. ከቤት እንደወጣ ወጣ እስካሁን ድረስ አድራሻው አይታወቅም። ወ/ሮ  ሃረግ አሁን ላይ የቀን ስራ እየሰራች ልጆቿን ለማስተዳደር ተገድዳለች። “ስራ ካልተገኘ ደግሞ ቤቴ ነው የምውለው፣ ልጆችን ማስተዳደር ከባድ ነው” የምትለው የመቀሌ ከተማ ነዋሪዋ ለመጨረሻ ጊዜ የቤት ኪራይ ከከፈለች 2 ዓመታት ከግማሽ ስለማለፉ እንባ እየተናነቃት ነግራናለች። የባለቤቷ የት እንዳለ አለመታወቅ ለራሷ እና ለልጆቿ ሃዘን እንደሆነባቸውም ለአዲስ ዘይቤ ተናግራለች።

ሌላኛዋ የመቀሌ ነዋሪ ወይዘሮ ክንደሓፍቲ ባለቤታቸው በ2013 ዓ.ም ልጃቸው ደግሞ በ2014 ዓ.ም ለጦርነቱ ከቤት እንደወጡ እስካሁን በህይወት ስለመኖራቸውም ሆነ ስለመሞታቸው ምንም ወሬ የለም ይላሉ። “ያልሄድኩበትና ያልጠየቅኩበት ቦታ የለም” የሚሉት ወ/ሮ ክንደሓፍቲ አሁን ላይ መንግስት የት እንዳሉ ምላሽ ቢሰጠን ሲሉ በሀዘን ተናግረዋል።

አዲስ ዘይቤ የክልሉን የአስተዳደርና ጸጥታ ተቋም አስተያየት ለማካተት ያደረገችው ሙከራ ባይሳካም በጉዳዩ ዙሪያ መረጃዎችን ለማገኘት ጥረታችን ቀጥሏል።

ይህ የወላጆች ጥያቄ ባለፈው ሰሞን መለስ “ቆሻሻ” ብሎ በሚጠራቸው የአካል ጉዳተኞች ከተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ጋር የሚመሳሰል ነው። ሰላም ከመጣና ሕዝብ መሠረታዊ ጥያቄዎቹ ከተሟሉ እነዚህ መሰል የሰብዓዊ መብቶች ጥያቄ እንደሚያነሳ ይጠበቃል። ትህነግ ውጊያና ጦርነትን የሙጥኝ ብሎ ይዞ የቀጠለው ይህንን መሰል ጥያቄዎች ላለመጋፈጥ ነበር። አሁን ነገሮች ዓይናቸውን አፍጥጠው መጥተዋል። ይህንን መሰል ጥያቄዎች መበራከት ትህነግ መቼም ቢሆን ማንሰራራት የማይችል ቡድን ሆኖ የሚያፈራርሰው ይሆናል ተብሎ ይገመታል። በትግራይ ለዘመናት የገነባውም ስሁት ትርክት፣ ዓላማውም፣ ፕሮግራሙም፣ ባንዲራውም፣ መዝሙሩም አብሮ የሚቀበር ይሆናል የሚሉ አስተያየቶች ይደመጣሉ።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: News, Politics, Slider, Social Tagged With: ethiopian terrorists, operation dismantle tplf, tplf terrorist

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule