የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከተከላካይነት ወደ ማጥቃት እርምጃ ከተሸጋገረ የትግራይ ክልል የመጨረሻው መዳረሻ እንደማይሆንና ዋናው ግብ ቀይ ባህር ላይ የኢትዮጵያን ባንዲራ መትከል መሆኑን በይፋ አስታወቁ። ጄኔራሉ በቅርቡ በሰጡት መግለጫ፣ በአሁኑ ወቅት ሠራዊቱ በትዕግስትና በጥበብ የመከላከል ሥራ ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ እየሠራ መሆኑን ጠቁመዋል። ይሁንና ወደ ማጥቃት በሚገባበት ወቅት ትኩረቱ ጥቃቅን አሸባሪዎችና ተላላኪዎች ላይ ሳይሆን፣ ቀጥታ ዕዝን መቀለ ላይ በማድረግ የቀይ ባህርን መውጫ መቆጣጠርና በአሰብ ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ማውለብለብ እንደሆነ በቁርጠኝነት ገልጸዋል። እንደ እርሳቸው ማብራሪያ፣ በአሁኑ ወቅት የትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ በመከላከያ ሠራዊቱ የካሜራ እይታና ቁጥጥር ሥር ያለ … [Read more...] about “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው

