መከላከያ አላማጣን ጨምሮ 13 ስልታዊ ቦታዎችን ሙሉ በሙሉ ሲቆጣጠር ታጣቂው በሁሉም ግንባሮች እየተበተነ ነው አስገራሚ ወታደራዊ ስምምነቶችን በመፍጠርና ንጹሃንን ለጦርነት በመማገድ የሚታወቀው የትህነግ የጥፋት ቡድን፣ በራያ አላማጣ፣ በላሊበላና በተለያዩ የምሥራቅ ግንባሮች በከፈተው ትንኮሳ ታይቶ የማይታወቅ አይቀጡ ቅጣት እንደቀመሰና ፍጹም የመፍረስ አደጋ ላይ መውደቁን የጎልጉል የውስጥ ምንጮች አረጋገጡ። የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከተከላካይነት ወደ ማጥቃት በመሸጋገር ባደረገው መብረቃዊ ጉዞ የአላማጣ ከተማን፣ የአላማጣ ወረዳንና ዙሪያውን ጨምሮ 13 ስልታዊ ቀጠናዎችን ሙሉ በሙሉ ነጻ አውጥቷል። የጎልጉል ምንጮች ከግንባር እንዳረጋገጡት፣ በመከላከያ ኃይለኛ የተጠናከረ ክንድ ሙሉ በሙሉ ነፃ የወጡት 13ቱ አካባቢዎች፦ ዋጃ፣ ጥሙጋ፣ አየር ማረፊያ፣ ቢትሞ፣ ኩቢ ቀረንሳ፣ ኩቢ … [Read more...] about የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው
operation dismantle tplf
የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ
* ወደ ኋላ መመለሻ ድልድያቸው ተሰብሯል በትህነግ፣ በሻዕቢያ፣ በአገው ሸንጎ እና በፋኖ መካከል የተመሠረተው የጥፋት ኃይሎች ጥምረት በሰቆጣ እና በአብዓላ ግንባሮች በከፈተው መጠነ-ሰፊ ማጥቃት በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የገጠመውን ሽንፈት ተከትሎ፣ ሙሉ በሙሉ የመበታተንና የመደምሰስ አደጋ እንደተጋረጠበት ለጎልጉል የደረሱ የውስጥ ምንጮችና ወታደራዊ ተንታኞች ገለጹ። ከግንባር ለጎልጉል የደረሱ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ በጥምረቱ ስም በሚንቀሳቀሱት የትህነግ አርሚ 22 እና አርሚ 92 የጦር ክፍሎች እጅግ ከባድ የሰው ኃይልና የቁሳቁስ ኪሳራ ደርሷል። ትህነግ በድሮን ፍርሃቻ ጥንት በበረኻ እያለ ሲደርግ እንደለመደው በአህያ እና በግመል በብዙ መከራ ያጠራቀመው መሣሪያና ቁሳቁስ ነው በሰሞኑ ጥቃት እንዳለ የወደመበት። በዋግኸምራ ዞን የምትገኘውን ሰቆጣ ከተማን … [Read more...] about የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ
የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ
የአገር መከላከያ ሠራዊት በሁሉም ግንባሮች ድል እያደረገ መሆኑ ተነገረ በሴንትራል ኮማንድ ሥር ከሚገኙ የደህንነት እና የጸጥታ ምንጮች ለጎልጉል የደረሰው አዳዲስ ዜና እንደሚያመለክተው፣ በሁሉም የጦር ግንባሮች የተከፈተውን የጥፋት ዘመቻ በመመከት ላይ ያለው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በታጣቂዎቹ ላይ ከፍተኛ ውድመት እያደረሰ ይገኛል። የትህነግ (ህወሓት) ታጣቂ ኃይሎችና አጋሮቻቸው በየግንባሩ እየተገደሉ፣ የከባድ ጉዳት ሰለባ እየሆኑ እና የት እንዳሉ ጠፍተው በመበታተን ላይ ናቸው። ጦርነቱ በሁሉም ግንባሮች አሁንም በቀጠለበት በዚህ ሰዓት፣ ታጣቂዎቹ ሙሉ በሙሉ የመደምሰስ አደጋ ገጥሟቸዋል። 1. በደጉዓ ዛታ አቅጣጫ በዚህ አቅጣጫ በተካሄደው ከባድ ውጊያ ምክንያት የትህነግ "አርሚ 22" ሙሉ በሙሉ ተበታትኖ ወደ ሩባ ፅላረ ሸሽቶ ገብቷል። በዚህ ግንባር የተመዘገቡት … [Read more...] about የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ
የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ
* የቀጠናውን መረጋጋት በሚያናጉ አካላት ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ እንደሚጥል አስጠነቀቀ በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ኤርቪን ጄ. ማሲንጋ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ትህነግ) በአፋር ክልል እና በአቅራቢያ ባሉ አካባቢዎች ላይ አዲስ መጠነ ሰፊ የጦርነት ስምሪት መክፈቱን በጽኑ የሚኮንን እና እስካሁን ከተሰሙት ሁሉ እጅግ ጠንካራ የተባለ መግለጫ አውጥተዋል። “የማታሸንፉት ጦርነት ውስጥ” ነው የገባችሁት በማለት ትህነግንና ተባባሪዎቹን ተስፋ የሚያስቆርጥ መልዕክትም አስተላልፈዋል። ይህ የአሜሪካ መንግሥት ከፍተኛ ዲፕሎማት የመንግሥታቸውን አቋም ያንጸባረቁበት አስቸኳይ መግለጫ ይፋ የሆነው ሰባት የታጣቂ ቡድኖች በጋራ በመሆን አዲስ ወታደራዊ ኅብረት መመሥረታቸውን ባስታወቁ ማግስት ሲሆን፣ ዋሽንግተን በሁኔታው ላይ ያላትን ጥልቅ ስጋት እና ቁጣ በግልጽ ያሳየችበት … [Read more...] about የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ
በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ
* የትህነግና የፋኖ ጥምረት ዕዝ መበጠሱ፤ አርሚዎች መናበብ አለመቻላቸው ተገለጸ በትግራይ ደቡባዊ ዞን፣ በራያ አላማጣና በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በተመረጡ ወታደራዊ ይዞታዎች ላይ ከአስራ ሰባት ጊዜ በላይ እጅግ የበረታና ተከታታይ የድሮን ጥቃት መፈጸሙ ታወቀ። ከመስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ የተሰነዘረውና የፊት ለፊት የእግረኛ ውጊያ ሳይካሄድበት በቴክኖሎጂ ብቻ የተመራው ይህ ጥቃት፣ በታጣቂ ኃይሎች ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የጽምዶ ታጣቂዎች የተገደሉ፣ የቆሰሉና የሎጂስቲክ ክምችታቸውም ከፍተኛ ውድመት እንደደረሰበት ተነግሯል። የትህነግና የፋኖ ጽምዶ ዕዝ ሠንሠለቱ የተበጠሰና በርካታ አርሚዎች መናበብ በማይችሉበት ሁኔታ ላይ እንዳሉ ታውቋል። ጎልጉል ከተለያዩ ወታደራዊ ምንጮችና ከአካባቢው እማኞች ያሰባሰበው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በተካሄዱት ተከታታይ … [Read more...] about በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ
ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ
* ኤርትራ በዚህ ወሳኝ ስብሰባ አለመገኘቷ ከባሕር ወንበዴዎች ጋር በተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ተጠቆመ ከባሕር ላይ ዘረፋ እና ከስደተኞች ሕገ-ወጥ ዝውውር ጀምሮ እስከ ዓለም አቀፍ የመርከብ መስመሮች መስተጓጎል ድረስ፣ የዓለምን አንዱን እጅግ ስራ የበዛበት የውሃ አካል የሚያዋስኑ ሀገራት በፍጥነት እየተለዋወጡ ካሉ የባሕር ላይ ስጋቶች ቀድመው ለመገኘት የቅርብ ትብብር እያደረጉ ይገኛሉ። የባሕር ላይ ውጥረቶች በከፊል መካከለኛው ምስራቅ ላይ በግልጽ እየታዩ ባሉበት ባሁኑ ወቅት፣ የኢትዮጵያ፣ የየመን፣ የጅቡቲ እና የሶማሊያ የደህንነት ባለሥልጣናት ማንም ሀገር ለብቻው ሊወጣው ከማይችለው እያደገ ከመጣው ስጋት የቀይ ባሕርን እና የኤደን ባሕረ ሰላጤን እንዴት መጠበቅ እንደሚቻል የጋራ አሳሳቢ ጉዳይ ላይ ለመምከር በዚህ ሳምንት ናይሮቢ ውስጥ መሰብሰባቸውን የተባበሩት መንግሥታት … [Read more...] about ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ
ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ
የሰባተኛውን አጠቃላይ ምርጫ ተከትሎ፣ የቀድሞው የአብን ተመራጭና የአሁኑ የኢህአፓ/ትብብር እጩ ተወዳዳሪ የነበሩት ዶ/ር አበባው ደሳለው በሰጡት ቃለ መጠይቅ በምርጫው ማሸነፍ ባለመቻላቸው የተሰማቸውን ጥልቅ ብስጭትና ንዴት ገልጸዋል። እንደ እርሳቸው ተወዳድረው ከትብብሩ እና ከሌሎች ተፎካካሪ ፓርቲዎች በሕዝብ የተመረጡትንም በብልጽግና ችሮታና ድጋፍ የተመረጡ፣ በምርጫ ሳይሆን በቅርጫ ያሸነፉ በማለት ወርፈዋል። ወደ ፓርላማ አለመግባት ትክክለኛ ውሳኔ እንደሆነም ገልጸዋል። ከኢትዮጵያ ኢንሳይደር ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት የተከበሩ አቶ አበባው ብሔር ተኮር ከሆነው አብን ወጥተው ወደ ኢህአፓ የገቡበትን ምክንያት አስረድተዋል። “ኢህፓን የመረጥኩበት ምክንያት ደግሞ እንደሚታወቀው ጠንካራ ታጋዮች የወጡበት ፓርቲ ነው። ለተራ ጥቅም ብለው ለተራ ኢኮኖሚ ጉዳይ ብለው ህሊናቸውን የማይሸጡ … [Read more...] about ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ
“ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው”
በሀገር ውስጥ ለግማሽ ምዕተዓመት የሽብር ተግባራትን ሲፈጽም የነበረውና ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ትህነግ/ህወሃት) ተብሎ የሚጠራው ሕገወጥ የአሸባሪዎች ቡድን፤ በፍጥነት ዓለምአቀፍ አሸባሪ ወደመሆን እየተጓዘ እንደሆነ በቅርብ የሚወጡ ሪፖርቶች እየጠቆሙ ነው። በሰኔ ወር 2026 የወጣውን የሚሊተሪ ታይምስ (Military Times) ዘገባ መነሻ በማድረግ የተዘጋጀ የዜና እንዳለው ዩናይትድ ስቴትስ ጦሯን መቀነሷን ተከትሎ በአፍሪካ የአሸባሪዎች ስጋት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑ ያስረዳል። የአሜሪካ ጦር በአፍሪካ አህጉር ያለውን ውክልና እና የሠራዊት ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱን ተከትሎ፣ በሳህል እና በአፍሪካ ቀንድ አካባቢዎች የጂሃዲስት ቡድኖች ተጽዕኖ እና ጥቃት በአስደናቂ ሁኔታ እያደገ መሆኑን የስትራቴጂክ እና ዓለም አቀፍ ጥናቶች ማዕከል … [Read more...] about “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው”
አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ
በሰሜን ኢትዮጵያ በድጋሚ ግጭት ለመቀስቀስና ቀጣናዊ ሰላምን ለማደፍረስ ከሻዕቢያ ጋር ጽምዶ ፈጥሮ አደገኛ እንቅስቃሴ ላይ በሚገኘው ትህነግ (ህወሃት) አመራሮችና በቅርብ የቤተሰብ አባላቶቻቸው ላይ ያነጣጠረ የቪዛ እገዳ መጣሉን ተከትሎ የአሜሪካ መንግስት በይፋ አስታውቋል። ይህ ውሳኔ ይፋ የሆነው በኢትዮጵያ ውስጥ በሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ የመንቀሳቀስ ፍቃዱ የተሰረዘውና ሕገወጥ ተብሎ የተፈረጀው የትህነግ ታጣቂ ኃይል ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በቅርቡ በፈጠረው ቀጥተኛ የጦርነት ትንኮሳ ሳቢያ ነው። ትህነግ በተደጋጋሚ በቆሰቆሰው የሰሜኑ ጦርነት አንድ ሚሊዮን ያህል የንጹሃን ዜጎች ህይወት መጥፋቱ እንዲሁም በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወገኖች ለከፋ ረሃብና ለስደት መዳረጋቸው እየታወቀ ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር ብሎ የሚጠራው አሸባሪ አሁንም ለሰላም እያሳየ ያለው … [Read more...] about አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ
የታርጋ ጫጫታ
የተዛባ እና የተሳሳተ መረጃ በማሰራጨትና ከዚያ በማትረፍ ሕዝብን ማደናገርና ሀገርን መበጥበጥ የገፊና ጎታች ሤራ ዋነኛ አካሄድ ነው። የአርሲው ትንሽ ጋብ ሲል ሰሞኑን ደግሞ የታርጋ ጫጫታ አየሩን ሞልቶታል። በተለይ እንደ ኤሊያስ መሠረት ያሉ ከሙያም፣ ከስብዕና እጅግ በጣም የወረዱ ሰዎች ለሕዝብ ተቆርቋሪ መስለው የሚያሰራጩት መረጃ የብልጽግና ካድሬ እና የመንግሥት መዋቅሩ የተረዳው አይመስልም ወይም ሆን ብሎ እያገዛቸው ነው። ለታርጋ ሃምሳ ስድስት ሺህ ብር እንዲከፍል ሕዝቡ ተገደደ፣ የአይ ኤም ኤፍ ስልታዊ የግብር ስብሰባ ሕዝቡን እያደኸየው ነው፤ እንደ ኬኒያ ሀገሪቱ ልትናወጥ ነው፤ ሆ ብሎ መነሳት አሁን ነው፤ የግፍ አገዛዝ ገመዱን እያጠበቀው ነው፤ በየማኅበራዊ ሚዲያ የሚታየው ጭስ ይህ ነው። አይ ኤም ኤፍ እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ለኢትዮጵያ ብድር ለመፍቀድ እና በፊት … [Read more...] about የታርጋ ጫጫታ










