• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው

January 25, 2026 04:23 am by Editor Leave a Comment

“ጫካ ስንገባ ምክንያታዊ ነበርን አሁንም የሰላምን አማራጭ ተቀብለን ስንመጣ በምክንያት ነው” – ኮሎኔል ፈንታው ሙሀባ

“በሰላማዊ መንገድ የአማራን ህዝብ ጥያቄ እናስመልሳለን” – ረ/ፕ እያሱ አባተ

ከዚህ ቀደም በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) መካከል የዘላቂ ሰላም ስምምነት መፈረሙ ይታወሳል።

ሐሙስ ዕለት ደግሞ ስምምነቱን ውጤታማ ለማድረግ የማስፈፀሚያ ስምምነት ተፈርሟል።

ስምምነቱን የአማራ ክልል የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ እሸቱ የሱፍ (ዶ/ር) እና የአፋሕድ ወታደራዊ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ኢያሱ አባተ ነው የተፈራረሙት።

በስምምነት ፊርማ ስነስርዓቱ ላይ የሰላም ሚኒስትር አቶ መሐመድ ኢድሪስን ጨምሮ ፣ የመከላከያ አመራሮች፣ የአማራ ክልል አመራሮች የሰላም ጥሪ ተቀብለው የገቡ አካላት ተገኝተው ነበር።

በቅርብ ወደ ሰላም አማራጭ የገቡት የአፋሕድ ከፍተኛ አመራር ኮለኔል ፈንታው ሙሀባ እንዲሁም ረ/ፕ እያሱ አባተ ተገኝተው ነበር።

ምን ተባለ?

የሰላም ሚኒስትር አቶ መሐመድ ኢድሪስ፦

“ይህ ዘመን ያለንን አቅም በጋራ አዳምረን አንዱ ለአንዱ ድጋፍ ሆኖ ሰርቶ ከድህነት ለመውጣት የምንተጋበትና የምንሰራበት እንጂ ኋላቀር በሆነ መንገድ አንዱ ሌላኛውን ገድሎ የሚፎክርበት ዘመን አይደለም።

“በመግደል እና በመሞት የሚሟላ ወይም የሚሳካ የፖለቲካ ፍላጎት የለም። አሸናፊ መሆን ከፈለግን ዓለም ስልጡኖች በደረሱበት ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ውስጥ መግባት ህዝባችንን ማልማት ለህዝባችን ለትውልዳችን የሚበጀውን መስራት እንጂ ለቀጣዩ ትውልድ መማሪያ የሆኑትን አቅም የሚሆኑትን መሰረተ ልማት ማጥፋት፣ እድሎችን ማጨናገፍ አይገባም።

“ህብረታችን ፣ መደመራችን ለልማት መሆን መቻል አለበት። አንዳንዴ የኢትዮጵያን እድገት በማይፈልጉ አካላት ፣ ማደጋችን አብሮነታችን፣ ጥንካሬያችን ስጋት ለሆኑባቸው አካላት እራሳቸው እንኳን ኃይላቸውን ሰብስበው ምንም ማድረግ ከማይችሉ ትናንሽ አካላት አጀንዳ ተቀብሎ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ፣ ህዝቦቿን ለመጉዳት መንቀሳቀስ በታሪክም በትውልድም ተጠያቂ ያደርገናል።

“ይህ የሰላም መንገድ ሌሎችም በጫካ ውስጥ ያሉ ወገኖች ሊከተሉት የሚገባው አትራፊ መንገድ ነው።”

አቶ መሐመድ ፤ አሁን ላይ ሀሳብን ወደ መድረክ ይዞ መጥቶ መነጋገር እና በሀሳብ ማሸነፍ እየተሻለ ኋላቀር በሆነ መንገድ መሳሪያ አንግቦ የህዝብን እንቅስቃሴ መግታ፣ ህዝብ በየዕለቱ ከኑሮው ጋር የሚያደርገውን ትግል እየገቱ መፈተን የሞራልም በህግም ፣ በታሪክም ያስጠይቃል ሲሉ አሳስበዋል።

ረዳት ፕሮፌሰር እያሱ አባተ፦

“እኛ ወደጫካ ስንወጣ የተቆጠሩ ጥያቄዎች ይዘን፣ ህይወታችንን ለመስጠት ፣ ለህዝባችን ዋጋ ለመክፈል ነው የወጣነው። ከዚያ በላይ ዋጋ ከፍለን ከመንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት ፈጽመናል።

“በብዙ መንገድ እንደ ሀገር ፣ እንደ ህዝብ የተነሱ ጥያቄዎችን መንግሥት ማዳመጥ ካልቻለ ነፍጥ አንስተን መዋጋት አለብን ብለን ስንወጣ ጥያቄዎቻችንን ቆጥረን ይዘን መንግሥት ደግሞ ጥያቄያችሁ ምንድነው ? እንከሚልበት ጊዜ ድረስ ነው ውጊያ የሚያስፈልገው። ይሄን ጉዞ ለሶስት አመት ያህል ሄደናል።

“አሁንም የቀጠናውን ሁኔታ ፣ የዓለምን ሁኔታ ተንትነን ሚሻለው መንገድ የትኛው ነው የሚለውን ረጅም ጊዜ ተወያይተን እኛም በፋኖ በኩል፣ መንግሥትም እንደ መንግሥት የገመገመው ያየው ነገር ኖሮ ነው ይሄን የሰላም ስምምነት ለመፈራረም የማስፈጸሚያ ሰነዱንም ለመፈራረም የበቃነው” ብለዋል።

ረ/ፕ እያሱ ፥ ጥያቄዎቻችን ቆጥረን አስቀምጠናል አፈጻጸሙን በተመለከተ መንግሥትም ካለፈው ሂደት ተምሮ ሁሉንም ነገር ይፈጽማል ብለን እናምናለን ለዛም ነው የፈረምነው ሲሉ ገልጸዋል።

ቆጥረን ካስገባነው ውጭ ሌላ ጥያቄ የለም ስለዚህ ሌሎችም ወደዚሁ የሰላም መስመር ቢመጡ የተሻለ ነው ሲሉ አክለዋል።

እነሱ (መንግሥትን የሚታገሉ) “ከሰይጣንም ጋር ቢሆን አብረን እንሰራለን” ይላሉ እኛ የአማራን ርስት ለማስጠበቅ፣ ብሔራዊ ጥቅማችንን ለማስከበር ፣ የአማራን ህዝብ ጥያቄ ለማስመለስ ከመንግሥት ጋር በሰላም እንሰራለን ማለታችን ከባድ ውሳኔ ነበር ግን ወስነነዋል ሲሉ ገልጸዋል።

“እኛ አሁንም ከትግል አልወጣንም። የትግል ጥያቄዎቻችን የሚያርፉበት ምዕራፍና ቀጣይ ምንሄድበት መንገድ ምንድነው? የሚለውን ነው ያስቀመጥነው። በሰላማዊ መንገድ የአማራን ህዝብ ጥያቄዎች ሁሉ እናስመልሳለን። ልንሞት ነው የወጣነው ከእግዚአብሔር ውጭ ማንም ዋስትና አልነበረንም። እስከፍጻሜያችን ድረስ በአማራ ህዝብ ጥቅም ጥያቄ ላይ አንደራደርም። በሀገራችን ሉዓላዊነትና ጥቅምም ላይ አንደራደርም” ብለዋል።

ኮሎኔል ፈንታው ሙሀባ ምን አሉ ?

“ለሶስት ዓመት ያህል በጫካ ቆይተናል። ወደ ትግል/ጫካ ስንገባ ምክንያታዊ ነበርን አሁንም የሰላምን አማራጭ ተቀብለን ስንመጣ በምክንያት ነው።

“ይሄ ውይይት ዛሬ የተጀመረ አይደለም። የሰላማዊ መንገዱ የተፈለገበት ምክንያት አለ የሰላም ውይይቱ ለአንድ አመት ያህል የተካሄደ ነው።

“የዛሬ አመት ጥር ወር ላይ ዳውንት ላይ የአፍሪካ ህብረት፣ ኢጋድም መጥተው እኔም ባለሁበት ጠቅላላ ውይይት አድርገናል። በዛ ውይይት በጥሩ መንፈስ በጥሩ መግባባት ነው የተለያየነው። በግብታዊነት የተደረገ ነገር የለም።

“ውይይቱ አንድ አመት የተደረገ፣ ምክንያታዊ፣ ህጋዊነትን የተከተለ እንጂ ሰዎች እንደሚሉ በክህደት ወይም እጅ በመስጠት አይደለም” ብለዋል።

ኮለኔል ፈንታው በአማራ ክልል ያለው ትግል “ተጠልፏል” ያሉ ሲሆን ጠላፊዎቹ ህወሓት፣ ሻዕቢያ፣ ግብፅ ናቸው ሲሉ ገልጸዋል።

“ከነዚህ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል ? እንደ ሀገር የኢትዮጵያን እና ህዝቧን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል ? ካልን በምንም ተአምር አይቻልም ” ብለዋል።

” ይህች ሀገር ዛሬ የምትተራመሰው ህዝባችንም መረጋጋት ያቃተው ህወሓት እና ሻዕቢያ ባፀደቁት ህገመንግስት ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።

” ኢትዮጵያን እያተራመሱ ያሉት አሁንም ህወሓት ፣ ሻዕቢያ እና ግብፅ ናቸው ” ሲሉ ከሰዋል። ” ብር ይመድባሉ፣ መሳሪያ ይሰጣሉ ፣ ተተኳሽ ይሰጣሉ፣ አሁንም ሀገሪቱ እንዳትረጋጋ እንዲያውም ጦርነቱ አማራ ክልል እንዲካሄድና ትርምሱ እዛው እንዲቆም ይፈልጋሉ ፤ ትንኮሳው ወደነሱ እንዳይመጣ በሩቅ ጦርነቱ ትርምሱ አማራ ክልል እንዲሆን ይፈልጋሉ ፤ እኛ አንቀበልም ” ብለዋል።

የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር) በበኩላቸው ፤ “ሌሎች በትግል ውስጥ ያሉ ኃይሎች የክልላቸውን እና ሀገራቸውን ቁመናና ወርድ ተገንዝበው ለክብራቸው ሲሉ ወደ ሰላም አማራጭ እንዲመጡ በድጋሚ የሰላም ጥሪ አቅርበናል ” ብለዋል። (@tikvahethiopia)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Middle Column, News Tagged With: ethiopian terrorists, Fano, operation dismantle tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm
  • “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል October 26, 2025 10:15 pm
  • አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው October 25, 2025 11:09 pm
  • በዓባይ ግድብ ምረቃ፡ የሕዝብ ደስታ፣ የቴድሮስ ካሳሁን ዝምታ September 14, 2025 04:27 am
  • ኢትዮጵያ የውኃ ኑክሊየር ማብላያዋን ልታስመርቅ ነው  August 29, 2025 11:46 pm
  • መከላከያ በፋኖ አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ፤ ዘመነ በ“አንድ ማንኪያ ቅንነት” አንድ እንሁን አለ August 23, 2025 12:35 am
  • ፋኖን በፋይናንስና በሎጂስቲክስ የሚደግፉ የጎጃም ባለሃብቶች ከስደት ሊመለሱ ነው August 14, 2025 12:42 am
  • የበቀለ ገርባ የአሜሪካ ጥገኝነት ማመልከቻ ውድቅ ተደረገ August 13, 2025 12:16 pm
  • ሞዐ ተዋሕዶ “ነጻ አውጪ ግምባር” – ሞነግ August 13, 2025 12:58 am
  • የሃይማኖትና የመንግሥት ጥምረት በረከት ወይስ መርገም?  August 5, 2025 09:18 pm
  • የባከነ የስደት ሕይወት ከደባርቅ እስከ ኖርዌይ July 29, 2025 05:44 pm
  • “በዚህ ዓመት መጨረሻ ትግራይን እንቆጣጠራለን”፤ ቲፒኤፍ July 22, 2025 01:28 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule