ታጣቂው ህወሓት ልዩ ኃይል በሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ በአማራ ልዩ ኃይልና በሚሊሻ አባላት እየተደመሰሰ ይገኛል። በዚህ ታላቅ ጀብድ ሰራዊቱ የህወሓት ስግብግብ ኃይል ለጦርነት እየተጠቀመባቸው የነበሩ ከ230 በላይ ክላሽንኮቭ፣ ከ1 ሺህ በላይ የእጅ ቦምብና ሌሎች ተተኳሽ መሳሪያዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የደቡብ ዕዝ የሰው ሐብት ልማትና የሚዲያ አስተባባሪ ኮሎኔል ደጀኔ ጸጋዬ ተናግረዋል። እየተካሄደ ባለው ህግ የማስከበር ለህልውና ዘመቻ የአማራ ልዩ ኃይልና የሚሊሻ አባላት በተሰጣቸው ቀጣና በጠላት ላይ ከባድ ወታደራዊ ጥቃት በመፈጸምና በመደምስስ ግዳጃቸውን በብቃት እየፈጸሙ መሆኑንም ማመላከታቸውን ፋና ዘግቧል። በሌላ በኩል በጋምቤላ ከልል ዲማ ወረዳ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 5 ክላሽንኮቭ የጦር መሳሪያና አንድ F1 የእጅ ቦንብ ከስድስት ተጠርጣሪ ጋር መያዙን … [Read more...] about በርካታ ቁጥር ያለው የህወሓት የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ሥር ዋለ
operation dismantle tplf
ህወሃትን ያገለግሉ የነበሩ የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች እንዲታገዱ ተወሰነ!
በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ነበሩ ያላቸውን የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች እንዲታገዱ መወሰኑን ፌዴራል ፖሊስ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎቹ በቀጠሯቸው የጥበቃ አባላትና ተባባሪዎቻቸው ባንኮችንና የተለያዩ ድርጅቶችን ሲዘርፉ እና ሲያዘርፉ ነበርም ብሏል። በተጨማሪም 'የህወሓትን ተልዕኮ ለመፈፀም የተለያዩ ግለሰቦችን ወደ ኤጀንሲዎቹ አስርገው በማስገባት እና የጦር መሣሪያ በማስታጠቅ በኅብረተሰቡ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ ጥቃት ለመፈፀም እያሴሩ ነበር' ሲል አስታውቋል። በዚህም:- 1. ንስር የሰው ሃይል እና የጥበቃ አገ/ሃ/የተ/የግ/ማ 2. አጋር የጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ 3. ስብኃቱና ልጆቹ የንብረት አስ/ጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ 4. ሰላም ሴኩሪቲ ሶሉሽን ኃ/የተ/የግ/ማ 5. ኃይሌ ተክላይ … [Read more...] about ህወሃትን ያገለግሉ የነበሩ የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች እንዲታገዱ ተወሰነ!
በወጋገን ባንክ በርካታ የጦር መሠሪያ፤ በሱር ኮንስትራክሽን ደግሞ የሬዲዮ መገናኛ ተገኘ
በወጋገን ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ለጥበቃ አገልግሎት ከሚያስፈልገው ውጭ የጦር መሠሪያ ተከማችቶ መገኘቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ለሸገር ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡ ከተገኙት መሣሪያዎች አንዳንዱ በፀጥታ ኃይሉ እጅ የሌሉ ጭምር መሆናቸውን ነው የገለጹት፡፡ በተያያዘ ዜናም 97 የእጅ ሬድዮ 23 የረጅም እርቀት የትከሻ መገናኛ ሬድዮ ከሱር ኮንስትራክሽን በብርበራ መያዙን ትላንት በተሰጠ መግለጫ ተጠቅሷል፡፡ በከተማው የተያዙ ባለሀብቶችም እንዳሉ ይሰማል ይህስ በምን መስፈርት ነው ሲል ሸገር ላቀረበላቸው ጥያቄ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው የሕወሓትን ቡድን በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ የደገፉ ባለሀብቶች በማስረጃ ስለመያዛቸው ለጣቢያው ገልጸዋል፡፡ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about በወጋገን ባንክ በርካታ የጦር መሠሪያ፤ በሱር ኮንስትራክሽን ደግሞ የሬዲዮ መገናኛ ተገኘ
በ96 የህወሃት ወንበዴዎች ላይ የፍርድ ቤት ማዘዣ ወጣባቸው
የአገር ክህደት ወንጀል በፈፀሙ የጁንታው ሕወሓት ቡድን ላይ የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ እንደወጣባቸው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የጥፋት ቡድኑ አባላት ከኦነግ ሸኔ እና ከሌሎች ፀረ-ሰላም ሃይሎች ጋር በመቀናጀትም ከተለያዩ ክልሎች አገርን የማፍረስ ተልዕኮ ያላቸውን ኃይሎች በመመልመል ትግራይ ክልል ድረስ በመውሰድ ለእኩይ ተልዕኮቸው ስኬት የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት እንዲሁም የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፎችን በማድረግ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ብሄርን ከብሄር በማጋጨት እና በሃይማኖት ሽፋን ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠር በማድረግ በርካታ ንፅሁን ዜጎች እንዲገደሉ፣ በአካልና በንብረት ላይም ከባድ ጉዳት እንዲደርስ ማድረጋቸውን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በላከው መግለጫ አመልክቷል፡፡ እነዚህ የሀገር ህልውናን አደጋ ላይ በመጣል እንዲሁም ህገ-መንግስቱንና … [Read more...] about በ96 የህወሃት ወንበዴዎች ላይ የፍርድ ቤት ማዘዣ ወጣባቸው
የማይካድራ ዕልቂት
በምዕራባዊ ትግራይ ሁመራ አቅራቢያ «ማይካድራ» በተባለው አካባቢ የትግራይ ልዩ ኃይል ባልታጠቁ የአማራ ተወላጆች ላይ በሌሊት አሰቃቂ ግድያ መፈፀሙን ከሞት ያመለጠ የዐይን እማኝ ገለፀ። ጥቃቱ የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው ሲል ደግሞ የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ዐስታውቋል። በምዕራባዊ ትግራይ ሁመራ አቅራቢያ «ማይካድራ» በተባለው አካባቢ የትግራይ ልዩ ኃይል ባልታጠቁ የአማራ ተወላጆች ላይ በሌሊት አሰቃቂ ግድያ መፈፀሙን ከሞት ያመለጠ የዐይን እማኝ ገለፀ። ጥቃቱ የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው ሲል ደግሞ የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ዐስታውቋል። ድርጊቱ የተጀመረውን ሕግ የማስከበር ሂደት ህወሓት ወደ የእርስ በእርስ ጦርነት እንዲቀየር የዘየደው መላ ነውም ብሎታል። አንዳንድ የአማራ ክልል ነዋሪዎች የህወሓት የተስፋ መቊረጥ ስሜት ነው፤ ኅብረተሰቡ ህወሓት በዘየደው የብቀላ ሂደት … [Read more...] about የማይካድራ ዕልቂት
የበረኻ ወንበዴዎቹ ያለከመከሰስ መብት ተነሳ
ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት/ትህነግ) በማለት የሚጠራውና በኢትዮጵያ እጅግ አስከፊ የሚባልና ትውልድን ያወደመ ርዕዮት በመከተል አገር ያፈረሰው የወንበዴዎች ጥርቅም፤ እስካሁንም በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት በአሸባሪነት ተመዝግቦ የሚገኝ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል። አባላቱና ደጋፊዎችም በዚሁ ሁኔታ የሚታዩ መሆናቸውን ብዙዎች የሚስማሙበት ነው። ዛሬ የተሰበሰበው የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ አቃቤ ህግ በተለያዩ ወንጀሎች የጠረጠራቸውን ግለሰቦች ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምጽ አፀደቀ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 4ኛ መደበኛ ስብሰባው በወንጀል የተጠረጠሩ የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብት አንስቷል። በዚህም መሰረት፦ 1. ደብረጸዮን ገብረሚካኤል 2. አስመላሽ … [Read more...] about የበረኻ ወንበዴዎቹ ያለከመከሰስ መብት ተነሳ
በወልዲያ ከተማ የወንበዴዎቹን ተልዕኮ ሊያስፈጽሙ የነበሩ 25 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
በሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ 25 የህወሓት ተልዕኮ ተቀብለው የጥፋት ሴራቸውን በንፁሃን ላይ ለማድረስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ውለዋል። የጥፋት ኃይሎቹ በነዋሪዎች እና በፀጥታ ኃይሉ የጋራ ጥረት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የወልዲያ ከተማ የህዝብ ሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኢንስፔክተር ትዕዛዙ ጫኔ አስታውቀዋል። ኢንስፔክተሩ ግለሰቦቹ በተያዙበት ወቅት የተለያዩ መታወቂያዎች መያዛቸውን ነው የተናገሩት። እንዲሁም ከአንድ ሰው ላይ እስከ ዘጠኝ የተለያዩ የባንክ ደብተሮች በውስጣቸውም እስከ 400 ሺህ ብር ድረስ ተገኝቶባቸዋል ነው ያሉት። ፖሊስ በተጠርጣሪዎች ላይ አስፈላጊውን ምርመራ እያደረገ እንደሚገኝም ከአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።©ፋና ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about በወልዲያ ከተማ የወንበዴዎቹን ተልዕኮ ሊያስፈጽሙ የነበሩ 25 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
“ምዕራብ የትግራይ ክልል ነጻ ወጥቷል” የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ
ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አሕመድ ከጥቅት ደቂቃዎች በፊት በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ይፋ እንዳደረጉት ምዕራባዊ የትግራይ ክልል ነጻ መውጣቱን ተናግረዋል፡፡ ሆኖም የበረሃ ወንበዴዎቹ ስብስብ በመከላከያ ሠራዊት ላይ ያደረሰው ዘግናኝ ግፍ ነጻ በወጡ ከተሞች እየታየ እንደሆነ በመልዕክታቸው በመግለጽ “ሙት ይዞን እንዳይሞት” በማት ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስበዋል። መልዕክታቸው እንዲህ ይነበባል፤ “ለስግብግቡ ጁንታ ግፍ እስትንፋሱ፣ ጭካኔ ነፍሱ ነው። ጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን ሽራሮን ሲቆጣጠር፣ እጅና እግራቸውን የፊጥኝ ታሥረው የተረሸኑ የመከላከያ አባላትን አግኝቷል። ጭካኔው ልብ ሰባሪ ነበር። ዓላማው ኢትዮጵያን መስበር ነው። አላወቁም ከአልማዝ የጠነከረች መሆኗን። ዓላማው ሠራዊታችንንና ሕዝቡን አስቆጥቶ ለበቀል ርምጃ ማነሣሣት ነው። አላወቁም … [Read more...] about “ምዕራብ የትግራይ ክልል ነጻ ወጥቷል” የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ
የፈረሰውን የክልል መስተዳድር በፈረሰው ስሙ መጥራት ሕገወጥነት ነው
ያለፈው ሳምንት መጨረሻ አካባቢ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በህወሃት የሚመራውን የትግራይ ክልል መስተዳድር አፍርሶታል። ምክር ቤቱ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የትግራይ ክልል በክልሉ በሚገኘው እና በአገር መከላከያ ሰራዊት ስር ባለው በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ ነው ብሏል። ምክር ቤቱ ዛሬ ቅዳሜ ጥቅምት 28 ቀን 2013 ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ውሳኔ አሳልፏል። ጊዜያዊ አስተዳደሩ ያከናውናቸዋል ተብሎ ከተሰጡት ስራዎች መካከልም ሀ) አስፈፃሚ አካሉን ይመራል፣ ያስተባብራል፤ ለ) የጊዜያዊ አስተዳደሩን ኃላፊዎች ይመድባል፤ ሐ) ሕግና ሥርዓት መከበሩን … [Read more...] about የፈረሰውን የክልል መስተዳድር በፈረሰው ስሙ መጥራት ሕገወጥነት ነው
በጉጂ ዞን በተወሰደ እርምጃ 14 የኦነግ ሸኔ አባላት ተደመሰሱ
በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ባለፉት ሁለት ሳምንታት በተወሰደ እርምጃ 14 የኦነግ ሸኔ አባላት መደምሰሳቸውን የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ኡዶ ተናግረዋል። በተጨማሪም በእርምጃው 17 የኦነግ ሸኔ አባላት መቁሰላቸውን እና የቡድኑ 13 አባላት ደግሞ በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ገልፀዋል። እርምጃው የተወሰደው የፀጥታ አካላት እና ህብረተሰቡ በጥምረት በሰሩት ስራ እንደሆነ መናገራቸውን ከኦሮሚያ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ከአጥፊው ህወሓት ቡድን ተላላኪዎች በተለያዩ አካካባዎች የሽብር ጥቃት ለማድረስ ተልዕኮ ወስደው በመንቀሳቀስ ላይ የነበሩ አካላት በቁጥጥር ሰር መዋላቸውን ደግሞ የጉጂ ዞን የፀጥታና አስተዳዳር ቢሮ ኃላፊ አቶ ዋሌ ዱንጎ ተናግረዋል። የዞኑ የፀጥታ አካላት በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ወረዳዎች እና ከተሞች እስካሁን ባደረጉት … [Read more...] about በጉጂ ዞን በተወሰደ እርምጃ 14 የኦነግ ሸኔ አባላት ተደመሰሱ










