የአገር ክህደት ወንጀል በፈፀሙና በተለያዩ እርከን በሚገኙ 27 ወታደራዊ ሹማምንት በፈፀሙት የዘረፋ ወንጀል ንብረታቸው የሚፈለግ የህወሃት ቡድን አባላት እና ዳንኤል ብርሃኔ፣ ዶክተር እዝቅኤል ገቢሳ፣ ዶክተር አወል አሎ ቃሲም እና ሌሎች አምስት ግለሰቦች በአገር ውስጥና ባህር ማዶ ሆነው የተለያዩ ሚዲያዎችን በመጠቀም አገር አፍራሽ መረጃ በሚያሰራጩ ግለሰቦች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ መውጣቱን ፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል።
በመግለጫው መሠረት ቀደም ሲል በፈፀሙት የአገር ክህደት ወንጀል የመያዣ ትዕዛዝ ከወጣባቸው 117 ጄኔራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ መኮንኖችና የበታች ሹማምንቶች በተጨማሪ ስማቸው ቀጥሎ የተገለፀው 7 በተለያየ እርከን ላይ የሚገኙ ወታደራዊ ሹማምንት ላይ የመያዣ ትዕዛዝ እንዲወጣ ተደርጓል።
በዚህም መሠረት፡-
1/ሜጀር ጀነራል ዘውዱ ኪሮስ ገብረኪዳን
2/ኮሎኔል ተወልደ ገብረትንሣይ
3/ ኮሎኔል ገብረእግዚአብሔር ዓለምሰገድ
4/ኮሎኔል የማነ ገብረሚካኤል
5/ሻምበል ተወልደ ገብረመድህን
6/ኰሎኔል ጌትነት ግደያ
7/ኮሚሽነር ረታ ተስፋዬ
ሲሆኑ በተያያዘም ቀደም ሲል የነበራቸው ወታደራዊ ኃላፊነት እና ከህወሃት ቡድን ጋር ያላቸውን ጥብቅ ትስስር ተጠቅመው ከፍተኛ የዘረፋ ወንጀል በመንግሥት ላይ በመፈፀም ከፍተኛ ንብረት ማካበታቸው የተደረሰባቸው 2ዐ ግለሰቦችም ስማቸው ቀጥሎ ተገልጿል።
1. ሌ/ጄ ታደሰ ወረደ
2. ሜ/ጀ ገብረ አድሃና /ገብረዲላ/
3. ተክለብርሃን ወልደአረጋይ /ሳንቲም/
4. ሜ/ጀ ብርሃነ ነጋሽ /ወዲመዲህን/
5. ሜ/ጄ ማዕሾ በየነ
6. ሜ/ጄ ኢብራሂም አብዱልጀሊል
7. ሜ/ጄ ዮሃንስ ወልደጊዮርጊስ
8. ሜ/ጄ ነጋሲ ትኩዕ
9. ብ/ጄ አባዲ ፍላንሳ
10. ብ/ጄ ፀጋየ ተሰማ /ፓትሪስ/
11. ብ/ጄ ምግበ ኃይለ
12. ብ/ጄ ተክላይ አሸብር /ወዲ አሸብር/
13. ብ/ጄ ኃይለሥላሴ ግርማይ /ወዲ ዕበይተ/
14. ብ/ጄ ሙሉጌታ በርሔ
15. ኮ/ል ተወልደ ገብረተንሳይ
16. ኮ/ል ገብረእግዚአብሔር ዓለምሰገድ
17. ኮ/ል ደጀን ግርማይ
18. ኮ/ል የማነ ገብረሚካኤል
19. ኮ/ል ገብረሀንስ አባተ/ /ወዲአባተ/
20. ሻምበል ተወልደ ገብረመድህን /ወዲ አድዋ/
ከሕዝብ የዘረፉትን ንብረቶች ማስመለስ ይቻል ዘንድ ንብረቶቹ የሚገኙበትን ትክክለኛ አድራሻ በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ቢሮ ስልክ ቁጥሮች፡- 011 1 55 12 00 ወይም የነፃ የጥሪ መስመር 861 ወይም በአካል ወንጀል ምርመራ ቢሮ በመገኘት እንድታሳውቁ ሲል ፖሊስ ጠይቋል።
በመጨረሻም በአገር ውስጥና በውጪ አገር ተቀምጠው የተለያዩ የሚዲያ አውታሮችን በመጠቀም አገር በማፍረስ ተግባር ላይ የተሰማሩ፡-
1/ዶክተር እዝቅኤል ገቢሳ
2/ዶክተር አወል አሎ ቃሲም
3/ዶክተር ኢታና ሀብቴ
4/አቶ ፀጋዬ አራርሳ
5/አቶ ዳንኤል ብርሃኔ
6/አቶ ፍፁም ብርሃኔ
7/አቶ አሉላ ሰለሞን
8/ ሠናይት መብርሃቱ
በፈፀሙት የአገር ማፍረስ ወንጀል በሕግ የሚፈለጉ መሆኑን እናስታውቃለን ሲል የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል። (ኢቢሲ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply