በትግራይ ክልል ከተከሰተው ቀውስ ጋር በተያያዘ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በ167 ሰዎች ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣቱን ይፋ አደረገ።
ይህ የተባለው የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ትናንት በጋራ በሰጡት መግለጫ ነው።
ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ በመግለጫው ላይ በህውሓት ኃይሎች የተፈጸሙት ተግባራት በአገሪቱ የወንጀል ሕግ አንጻር በከፍተኛ ወንጀል የሚያስጠይቁ ናቸው ብለዋል።
በአገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የተፈጸመው ጥቃት ‘የመንግሥትን አገሪቱን የመከላከል ኃይል ለማዳከም’ በተፈጸመ ወንጀል በሚል የሚያስጠይቅ መሆኑን ጠቁመዋል።
በባሕር ዳር እና ጎንደር ከተሞች ላይ የተፈጸሙትን የሮኬት ጥቃቶች በተመለከተም፤ ድርጊቱ በሽብር ወንጀል እንደሚያስጠይቅ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን መናድ፣ ታጥቆ አመጽ መቀስቀስ እና በአገር ክህደት ወንጀሎች የሚያስጠይቁ ወንጀሎች መፈጸማቸውን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ተናግረዋል።
ይህንንም ተከትሎ በበርካታ ተጠርጣሪዎች ላይ የእስር ማዘዣ መውጣቱን አስታውሰዋል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply