• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ህወሃት እንደአጀማመሩ እየተጠናቀቀ ነው

November 18, 2020 04:23 am by Editor 1 Comment

ድልድይ በማፍረስ፤ መሠረተ ልማቶችን በማውደም ከየቦታው በተለቃቀሙ ወንበዴዎች መሪነት ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም በግፍ ሲገዛ የነበረው ህወሃት/ትህነግ እንደ አጀማመሩ አፈጻጸሙም እየሆነ እንዳለ ተጠቆመ።

ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት/ትህነግ) በማለት የሚጠራውና በኢትዮጵያ እጅግ አስከፊ የሚባልና ትውልድን ያወደመ ርዕዮት በመከተል አገር ያፈረሰው የወንበዴዎች ጥርቅም፤ እስካሁንም በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት በአሸባሪነት ተመዝግቦ የሚገኝ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል። አባላቱና ደጋፊዎችም በዚሁ ሁኔታ የሚታዩ መሆናቸውን ብዙዎች የሚስማሙበት ነው።

ከዚህ በታች የሚገኘው መረጃ በዓለምአቀፉ የአሸባሪዎች ቋት ተመዝግቦ የሚገኝ የህወሃት ወንጀል ዝርዝር ነው።

በበረሃ ዘመኑ ህወሃት ካወደማቸው በጥቂቱ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ትላንት በፌስቡክ ገጹ ባወጣው መረጃ መሠረት የህወሃት ጁንታ የትግራይ መሠረተ ልማቶችን እያፈረሰ ነው። 

የመከላከያ ሠራዊት ወደፊት መገሥገሡ ያስጨነቀው ጁንታ፣ በሁሉም አቅጣጫ ወደ መቀሌ በሚወስዱት መንገዶች ላይ የሚገኙ አራት ድልድዮችን አፍርሷቸዋል። የተማመነባቸው ከባድ ምሽጎቹ ፈራርሰው፣ በሽሬ መንገድ የደረሰበት ሽንፈት ያንገበገበው ጁንታ፣ በሽሬና በአኩስም መካከል የሚገኘውን አስፓልት በግሬደር ቆፍሮ ወደ ጉድጓድነት ቀይሮታል። 

የሕወሃት ጁንታው እስከዛሬ ከፈጸማቸው ወንጀሎች በተጨማሪ ባወደማቸው መሠረተ ልማቶች በቅርቡ ይጠይቅባቸዋል።

ከዚህ ወንጀል ጋር በተያያዘ ከላይ የቀረበው መረጃ ተጠቅሶ ወንበዴዎቹ ተጠያቂ እንዲሆኑ ለሚመለከተው ክፍል አቤት እንላለን።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Middle Column, News Tagged With: operation dismantle tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    November 22, 2020 12:19 pm at 12:19 pm

    ከግድያ እና ከዝርፊያው በሱዳን በኩል ወቶ አሁን አዲስ አበባ ከገባ የመከላከያ ሰራዊት የተገኘ የአይን ምስክርነት መረጃ፡ – ወያኔ እቅድን ከማስፈጸሙ በፊት በጦሩ ውስጥ በተሰገሰጉት ሃገርና ወገን ከሃጂ የትግራይ ልጆች ይፈጽማቸው የነበሩ አሻጥሮች ውጊያው የተከፈተ ቀን የተሰሩ ሰቅጣጭ ተግባሮች
    1. የመለዋወጫ እቃዎች ለጦሩ እንዳይደርስ ማድረግ፡ ለምሳሌ ባትሪ ለታንክ ለመኪና እንዲሁም ሌሎች ቁሳቁሶችን ማዘግየት ወይም ማገድ
    2. ዘር ተኮር ቅስቀሳን ማድረግ – አንድ በአንድ ላይ እንዲነሳ መገፋፋት – ይህ በጄ/ባጫ ደበሌ በጥቂቱም ተገልጾአል
    3. ማን ማን መሆኑን በዘርና በቋንቋ ለይቶ ማወቅና ማን መገደል እንዳለበት፤ ማን መያዝና መለቀቅ እንዳለበት፤ ማን ወደ እስር ቤት መሄድ እንዳለበት ተለይቶ ተይዟል
    4. ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት በአመራር ላይ ያላቸውን ባለስልጣኖች በመጠቀም ከዋርድያ (ተራ ዘበኞች) ሌላ የጦሩ ትጥቅ ግምጃ ቤት እንዲገባ ማድረግ
    5. የትግራይ ተወላጅ ሆነው በጦሩ ሹፌሮች፤ መካኒኮች ወዘተ የነበሩ የሲቪል ልብስ ለብሰው የሰሜን እዝ መኪኖችን በማንቀሳቀስ የወያኔን ሚሊሻና ልዪ ሃይል ወደ ውጊያውና ከበባው ለማስገባት በተቀናጀ መልኩ መስራት
    6. በሁመራና ዙሪያዋ ቀደም ብሎ ጌታቸው ረዳ ሲጎበኝ በተመለከታቸው ድክመቶችን አስተካክሎ ለውጊያ ሰአት ወታደሩ በተኛበትና ትጥቁ ግምጃ ቤት በገባበት ሰአት መጀመረ። ግምጃ ቤቱ በራፍ ላይ መትረጌስ ጠምዶ ትጥቅ ሊያወጡ የሚመጡ ወታደሮችን መግደልና ውጊያው ጋብ ሲል መኪና አቅርቦ ትጥቁን ሙሉ በሙሉ ዘርፎ ወደ ኋላ ማምጣት፡
    7. መሳሪያ በእጃቸው ኑሮ በየትኛውም ቦታ አሻፈረኝ የሚሉ ሃይሎችን ያለምንም ርህራሄ መደምሰስ በተለይ አማራ አመራር የሆኑትን ቀድሞ ማጥፋት፤ ውጊያው ከከረረ በሽምግልና እጃቸውን እንዲሰጡ መሞከር፤ ውሃና ምግብ መከልከል
    8. የወታደሩ የእርስ በርስም ሆነ ከበላይ አካል ጋር ያለው ግንኑኘት በመቋረጡ በሴል ፎንና በሌላ ግንኙነት እንዳይኖር የመብራት አቅርቦትና የሞቫይል አገልግሎትን መቁረጥ፡
    9. ጦርነቱ ወደ መሸነፍ ከደረሰ ዘር ተኮር የሆነ ፍጅት መፍጠር (የወያኔ ማፊያ የማነ የፈሪያት የማነ አባት) በማይካድራ የሰራው ይህ ነው። በሁመራ ከወያኔ በተላለፈ ለቃችሁ ውጡ ትዕዛዝ ሁመራ ሆስፒታል ውስጥ ተኝተው የነበሩ ከ 20 በላይ ሰዎች የሞቱት በዘር ላይ ባተኮረ አሰራር ነው። በዚያ ሆስፒታል ማን ማን እንደነበር መንግስት መርምሮ ሙያቸውን ከድተው ለወያኔ ያደሩትን በመያዝ ለፍርድ ሊያቀርብ ይገባል።
    10. ከተሸነፍን ሰዎች ወደ ሱዳን እንዲሰደድ በማደረግየአለምን ህብረተሰብ ድጋፍ መጠየቅና ከስደተኞቹ ጋር የወያኔ ካድሬዎች አብረው እንዲሰደድና ህዝቡን እንዲያደራጅ ማድረግ (ያው ተመልሶ ውጊያ ለመክፈት በማሰብ ነው)
    11. በአለም ዙሪያ ለተበተኑ የትግራይ ተወላጆች አማራና ዶ/ር አብይ የትግራይን ህዝብ እንዳጠቃ በፈጠራ ወሬ ማሳመንና ለአለም ህዝብ የውሸት ቱልቱላ ነፊዎች ማድረግ
    12. በውጊያ ላይ የሚማረኩ ሁሉ እኔ ገበሬ ነኝ በግድ ነው ያስገቡኝ በማለት ሲለቀቁ ተመልሰው ወደ ጦርነቱ እንዲገቡ ማድረግ
    13. ውጊያው ከመጀመሩ በፊት የሰሜን እዝ ደሞዝና ራሽን ሲደርስ በቁጥጥር ስር ማድረግ
    14. 1.3 ቢሊዪን አዲሱ ብር መቀሌ መድረሱ ሲረጋገጥ ተኩስ እንዲከፈት። በቁጥር 13 ና 14 ላይ ያለቱን ንብረቶች ለወያኔ ሚሊሻ፤ ለልዪ ጦርና በየስፍራው ከወያኔ ጋር አብረው አንገት ለሚቆርጡ የኦሮሞ ጽንፈኞች ማዳረስ።
    15. በመተከል፤ በቤኔሻንጉልና በሌሎችም ስፍራዎች ዘር ተኮር ጥቃቶችን ማፋፋም – ለአለም ህብረተሰብ ዶ/ር አብይ ሃገሪቱን ወደ ቀውስ እየወሰዳት ነው ብሎ ማሳጣት የሚሉ ንድፎች ናቸው በዶ/ር ደብረጽዪንና በሌሎች ታልመው ስራ ላይ የዋሉት።
    ለዘመናት ወያኔ ውሻ ነው; ወያኔ አራዊት ነው ስንል ዝም ብለን ስም ለማጥፋት አልነበረም። ወያኔ ተማርከው እጃቸውን ባነሱ የደርግ ወታደሮች ላይ ታንክ የነዳና ጥይት ያርከፈከፈ ወክየዋለሁ ለሚለውም የትግራይ ህዝብ የውሸት ታምቡር ሲመታ የኖረ እቡይ ፍጡር ነው። በዘሩ የሰከረ፤ በቋንቋው የሰከረ እኔ ብቻ የሚል እንደ ጣሊያኑ ሞሶሎኒ በትቢዕት የተወጠረ ከሰው ዘር የወጣ ቡድን ነው። የትግራይን ህዝብ ሲሸውድት የኖሩት በሃሳብና በጉልበት እያስፈራሩ ነው። 1 ለ 5 በተባለ የኮሚኒሳት ትስስር ሁሉም ተፈራርቶ እንዲኖር እነርሱ ግን ጠጅና ጮማ እየቆረጡ የሚበሉትን ሳይሆን የሚያረጓቸውን ሴቶች ሳይቀር እየተካፈሉ የኖሩ በሞራልም ሆነ በሌላው የሰው መስፈርት እንስሳ የሆኑ ማፊያዎች ናቸው። አሁን ግን ማብቂያቸው በበራቸው ላይ ነው። የገደለ ይገደል፤ የገረፈ ይገረፍ፤ የዘረፈ የዘረፈውን ይመልስ፤ በዘርና በቋንቋ የሰከረው ይህ ቡድን ግባ ዕተ መሬቱ ባፋጣኝ መፈጸም አለበት። በሞታቸው እፎይታ ለትግራይ ህዝብ እፎይታ ለጎረቤት ሃገሮችና ለመላ ኢትዮጵያ ይሆናል። በቃኝ!

    5. ጦሩ የተዋለደ፤ ልጆችና ሚስት ያላቸው በመሆኑ ኡኡታና ግርግር እንዳይመጣ ልጆችንና ሚስቶችን ለስብሰባ ነው ብሎ ማሳመን

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm
  • አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን March 15, 2023 08:52 am
  • ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ March 15, 2023 08:48 am
  • በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ March 15, 2023 01:43 am
  • ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ March 15, 2023 12:52 am
  • አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች  March 10, 2023 10:45 pm
  • ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ March 2, 2023 09:56 am
  • በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ? March 2, 2023 09:43 am
  • አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት February 24, 2023 10:44 am
  • በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል February 24, 2023 08:39 am
  • የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ! February 24, 2023 08:19 am
  • “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ February 21, 2023 10:09 am
  • አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ February 21, 2023 10:01 am
  • በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት February 17, 2023 06:39 pm
  • ኦነግ ሸኔ አሸባሪነቱ ሳይነሳለት በሽመልስ የሰላምና የእርቅ ጥሪ “በክብር” ቀረበለት February 17, 2023 12:35 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule