በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ስሙ ኢንፎኔት ኮሌጅ አካባቢ አንድ በርሜል ገንዘብ ወድቆ ተገኘ።
በዚህ ስፍራ በአንድ በርሜል ተጠቅጥቆ መገኘቱን የኢትዮ ኤፍ ኤም ሪፖርተር በአካል ተገኝቶ አረጋግጧል።
የተገኘው ገንዘብ የኢትዮጵያ ብር እና ዶላር ሲሆን ገንዘቡን ማን እንደጣለው ያልተተረጋገጠ ሲሆን የአካባቢው ፖሊስ በመኪና ጭኖ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንደወሰደውም ሪፖርተራችን አረጋግጧል።
በተያያዘ ዜና በዚሁ ወረዳ ጣልያን ሰፈር ልዩ ስሙ ጉሊት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አንድ አዛውንት ቤት ቁጥሩ እስካሁን ያልተረጋገጠ ገንዘብ በማዳበሪያ እና በመዘፍዘፊያ አስቀምጠው ተይዘዋል።
አዛውንቷ ለረጅም አመታት በልመና ስራ የሚተዳደሩ ናቸው የተባለ ሲሆን የገንዘቡን መጠን ለማወቅ የአካባቢው ወጣቶች እና ፖሊስ በጋራ ቆጠራ እየተካሄደ መሆኑን ሰምተናል።
አዛውንቷ አዲሱ እና አሮጌው የበር ኖት በተጨማሪ ወርቅ እና ዶላርም ባስቀመጡት ገንዘብ ውስጥ አብሮ መገኘቱ ተገልጿል። (ፎቶው ለማሳያነት ከፋይል የተወሰደ – ሔኖክ ወ/ገብርኤል፤ የኢትዮ ኤፍ ኤም)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
gidole gillo says
amazing history