• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“በዚህ ውጊያ አላምንበትም” አብረኸት

November 17, 2020 11:51 pm by Editor Leave a Comment

አብረኸት የጁንታው ታጣቂ የነበረችና እጃቸውን ለመከላከያ ሰራዊት ከሰጡ ውስጥ አንዷ ነች። ገና የ21 ዓመት ወጣት ናት። ወጣቷ በ2011 ዓ.ም የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ለመቀላቀል በብርሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ስልጠና ወስዳለች። የኢትዮጵያ መካላከያ ሰራዊት አባል ሁና ነገሌ ቦረና ተመድባም ግዳጇን እየተወጣች ሳለ በጠና ታምማ ከውትድርናው ዓለም ተሰናብታ ወደ ቤተሰቦቿ መመለሷን በስፍራው ተገኝቶ ላነጋገራት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅይ ዘጋቢ ገልጻለች።

የአብረኸት ህመም መጥናት ከምትወደው መከላከያ ቢለያትም ከጁንታው ዕይታ ግን መሰወር አልቻለችም። በጠላ ንግድ የሚተዳደሩትን እናቷን  እያገዘች ኑሮን ብትቀጥልም፤ የጁንታው አባላት የአብረኸትን ወታደርነት ያውቁ ነበርና የጁንታውን ታጣቂ እንድትቀላቀል በእናቷ በኩል ግፊት ማድረግ ጀመሩ። ጁንታው የአብረኸትን እናት ሌት ተቀን በማስፈራራታቸው ልጃቸውን ሳይወዱ በግድ ለታጣቂው አስረከቡ፤ አብረኸትም ቤተሰቦቼን ለአደጋ ከማጋልጥ በሚል ታጣቂውን ተቀላቀለች።

“ሌላ ስራ በቀላሉ ማግኘት ስላልቻልኩና ጫናውና ማስፈራሪያው ሲበዛብኝ ታጣቂውን ተቀላቀልኩ። የቤተሰቡ አባላት ሰባት ነን፤ አባቴ በህይወት የለም። እናቴ ብቻዋን ነው ጠላ ሽጣ ያሳደገችኝ። እሷን ለማገዝ ስልም ነው ወደዚህ የገባሁት” ስትልም ነው የታጣቂው አባል የሆነችበትን አጋጣሚ የምታስታውሰው።

አብረኸት የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ እየወሰዱት ባለው ህግ የማስከበር እርምጃ ላይ እጇን የሰጠችው አንድም ጥይት ሳትተኩስ መሆኑን ትናገራለች፤ “150 ጥይት ተስጥቶኝ አንድም ጥይት ሳልተኩስ ነው እጄን የሰጠሁኝ። ምክንያቱም በዚህ ውጊያ አላምንበትም። እየሞተ ያለውም የደሀው ልጅ ነው። እጄን ከሰጠሁ በኋላም ቢሆን ሶስት ቀን ሙሉ የሰራዊቱ አባላት ከሚበሉትና ከሚጠጡት እያካፈሉኝ ቆይቻለሁ”።

በትግራይ ክልል  በየአካባቢው ያለው ወጣት ተገዶ ወደ ግዳጅ  እንዲገባ ተደርጓል የምትለው ወጣቷ፤ ስልጠና የሚሰጠውም የይድረስ ይድረስ መሆኑን አልሸሸገችም፤ “ለአጭር ጊዜ ክላሽ እንዴት እንደሚፈታና እንደሚገጠም፣ ኢላማ እንዴት እንደሚመታ አሳይተው ብቻ ነው ወደ ጦርነት የሚማግዷቸው። ይህ ደግሞ የህወሓት አመራሮች ለትግራይ እናቶችም ሆነ ወጣቶች ደንታ እንደሌላቸውና የራሳቸውን የስልጣን ጥም ለማርካት ፍላጎት ያላቸው መሆኑን ያሳያል” ነው ያለችው፤ አብረኸት።

“የህወሓት አመራሮች፤ የትግራይን ህዝብ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደሚጠላው፣ የትም ሄደው በሰላም መኖር እንደማይችሉ አድርገው ወጣቱንም ሆነ ህጻናትን ጭምር ይሰብካሉ። ሁሉም የትግራይ ህዝብ የዚህ አይነት አስተሳሰብ ስላለውና ህወሓትን ስለሚፈራ የሚሉትን ለማድረግ ይገደዳል። ይህ ሰላም የማይወድ ድርጅት ውጤት ለማያመጣ ነገር ወጣቱን እያስፈጀ ነው” ብላላች፤ አብረኸት።

የህወሓት ጁንታ ወጣቱን መስዋዕት የሚያስከፍሉት የማይሆን ነገር እየሞሉት፣ እያስገደዱትና፣ በገንዘብም እያታለለሉት  ጭምር መሆኑን አብረኸት ትናገራለች።

የትግራይ ህዝብ መከላከያን እንዲወጋ አይፈልግም፤ ምክንያቱም መካላከያ የትግራይ ህዝብን ደህንነት ከመጠበቅ ጎን ለጎን ለህብረተሰቡ ትምህርት ቤት እየሰራ፣ ጤና ጣቢያ እየገነባ የኖረ ወገን ነው፤ የምትለው አብረኸት፤ “ወርቅ ለአበደረ ጠጠር እንዲሉ እኛን አታለው እንደ ቤተሰብ የምናየውን መከላከያ ሰራዊትን እንድንወጋ አድርገውናል” ያለችው በከፍተኛ ጸጸት ውስጥ ሆና ነው።

“የህወሓት ቡድን እንደሚለው መከላከያ እኛን ቢጠላን ኖሮ እንዴት ትግራይን ይጠብቃታል” ስትልም ትጠይቃለች። “እኛ ምንግዜም ኢትዮጵያዊ ነን፤ አጸያፊ ስራ እስካልሰራን ድረስ ህዝቡ ዝም ብሎ አይጠላንም። በመሆኑም የትግራይ ወጣቶች ዓላማ የሌለው ጦርነት ውስጥ መግባት የለባቸውም። ለመከላከያ ሰራዊት እጃቸውን በመስጠት በሰላም መኖር ይኖርባቸዋል” ስትል ሀሳቧን ቋጭታለች። (ጌትነት ምህረቴ፤ ኢፕድ)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Middle Column, Social Tagged With: operation dismantle tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
Copyright © 2026 · Goolgule