
በትግራይ ክልል ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ምሽት ጀምሮ ለ25 ቀናት በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ቡድንና በመከላከያ ሠራዊቱ መካከል ሲደረግ የሰነበተው ውጊያ፣ ቅዳሜ ኅዳር 19 ቀን ከሰዓት በኋላ የመከላከያ ሠራዊቱ የክልሉ ዋና ከተማ መቀሌን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ(ዶ/ር) እና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ አረጋግጠዋል።
መከላከያ ሠራዊቱ ባካሄደው ዘመቻ ንጹኃን ዜጎች ዒላማ ሳይሆኑና ቅርሶች ሳይጎዱ መቀሌ ለመግባት መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አስታውቀዋል።
ሠራዊቱ የመቀሌ ከተማ ነዋሪ ላይ ጉዳት ሳይደርስ እንዴት ከተማዋን መቆጣጠር ይቻላል በሚለው ላይ ኅዳር 18 ቀን ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን በመግለጫቸው ያስታወሱት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ፣ በዕቅዱ መሠረት ከተማዋን መቆጣጠር መቻሉን ገልጸዋል።
የመከላከያ ሠራዊቱ በደረሰባቸው አካባቢዎች ሁሉ የትግራይ ሕዝብ ለአገሩ ያለውን ፍቅርና ለመከላከያ ሠራዊቱ ያለውን ክብር ማሳየቱንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሳይገልጹ አላለፉም።
“የሕወሓት ቡድን ካስታጠቃቸው ጥቂት የክፋት ኃይሎች ውጭ ያለው የትግራይ ሕዝብ መቐለ እስኪገባ ድረስ ለመከላከያ ሠራዊቱ የሚጠበቅበትን ድጋፍ ሁሉ በማድረጉ የሠራዊቱን ድልና የቡድኑን ሽንፈት አፋጥኖታል፤” ብለዋል።
“ቡድኑ በየትኛውም መመዘኛ ለትግራይ ሕዝብ አይመጥነውም” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣
ለድጋፉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
“የሕወሓት ቡድን በሸሸበት ከተማና አካባቢ ሁሉ የጤና ተቋማትን፣ ትምህርት ቤቶችን፣ ድልድዮችን፣ መንገዶችን፣ መሥሪያ ቤቶችን አውድሞ ሄዷል፤” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ያፈረሳቸውን መሠረተ ልማቶች በፍጥነት በመገንባት ሕዝቡ ወደ ሰላማዊ ኑሮው እንዲመለስ ለማድረግ የተቻለው ሁሉ እንደሚደረግ ቃል ገብተዋል።
በተያያዘ ዜና የመከላከያ ሠራዊት ኅብረት ሥልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተና ጄኔራል ሀሰን ኢብራሂም ዓርብ ኅዳር 18 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት በሰጡት መግለጫ፣ የመከላከያ ሰራዊት ሀውዜን፣ አልነጃሺ፣ አዲቀየህ፣ ማይመሳኖንና ውቅሮን ከሕወሓት ታጣቂ ኃይል ሙሉ በሙሉ ነፃ ማድረጉን አረጋግጠዋል።
የሕግ ማስከበር ዘመቻው በውጤታማነት መከናወኑን ያስታወቁት ጄኔራል መኮንኑ በዓድዋ ግንባር የተንቀሳቀሰው ሠራዊት ሀውዜንን፣ አብርሃ ወአፅብሃንና ውቅሮን የተቆጣጠረ መሆኑን፣ አጉላን ደግሞ በግማሽ ቀን መያዙን ገልጸዋል። በሁለተኛው ግንባር ማለትም በአዲግራት በኩል ሠራዊቱ ሰንቀጣንና አል ነጃሺን በመቆጣጠር ውቅሮን መያዙን በመግለጫው አስረድተዋል።
በሦስተኛው የራያ ግንባር የሚገኘው ሠራዊት አዲቀይህን ከያዘ በኋላ ሔዋነን በመቆጣጠር የትግራይ ልዩ ኃይልን ሁሉንም ምሽጎች ደርምሶ ወደፊት መገስገሱን አስታውቀዋል። በአጉላን በኩል መንገድ ለመዝጋት ቢሞክርም እንዳልተሳካለትና ወደኋላ ማፈግፈጉን ጠቁመው፣ አሁን ግን መቀሌ ከተማ ብቻ መቅረቱንና በጥቂት ቀናት ወስጥ ዘመቻው እንደሚጠናቀቅ ገልጸዋል።
የሦስተኛው ምዕራፍ ዘመቻ ዓላማ የሕወሓት አመራሮችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ለሕግ ማቅረብ መሆኑን ያስታወሱት ሌተና ጄኔራል ሀሰን፣ ሠራዊቱ ነፃ ባወጣባቸው ሥፍራዎች ሁሉ የትግራይ ሕዝብ በሠራዊቱ ላይ አልተኮሰም ብለዋል። ይህም የሕወሓት አመራሮችና ሕዝቡ አንድ አለመሆናቸውን ማረጋገጫ ነው ሲሉ አክለው፣ ሕዝቡ እንዲያውም ለሠራዊቱ ወገንተኝነት አሳይቷል ሲሉ ሁኔታውን አስረድተዋል።
የሕወሓት አመራሮችና ቡድናቸው በፕሮፓጋንዳ ጭምር እያፈገፈጉ መሄዳቸው ሽንፈታቸውን እያረጋገጠ እንደሆነም ጄኔራል ሀሰን ጠቁመዋል።
የደቡብ ግንባር የበላይ አዛዥ ሌተና ጄኔራል ባጫ ደበሌ ከሥፍራው በሰጡት ሌላ መግለጫ፣ ከባድ ምት ያረፈበት የትግራይ ልዩ ወደ አዲጉደም እንደሸሸ አስረድተዋል። ሠራዊቱ አካባቢውን በተቆጣጠረበት ወቅት ልዩ ኃይሉ ይጠቀምባቸው የነበሩ ስድስት ታንኮች፣ ሁለት ዙ23 የአየር መቃወሚያዎችና በርካታ መሣሪያዎች መደምሰሳቸውን አስታውቀዋል። ሠራዊቱ አስቸጋሪ መልክዓ ምድር በብቃት በማለፍ ከፊቱ የቆመውን ኃይል መደምሰሱን አስረድተዋል። (ሪፖርተር)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
ጉልጉሎች እናመስግናለን
እንኳን ደስ አላችሁ!
ወያኔ ከሻገተ አስተሳሰቡና ከሰይጣናዊ ተንኮሉ ጋር ወደ እንጦርጦስ ወርዷል!
ኢትዮጵያ አንድ የጨለማ ዘመን ታሪክ ዘግታለች
ቀደም ብለን የወያኔ አወዳደቅ የሮም አወዳደቅ ይሆናል ስንል ከርኩስ ተግባራቸው ተነስተን ሁሉም ቀን ጠብቆ እንደሚፍረከረክ በታሪክ ስለተረዳን ነበር እንጂ እንደ ዘመኑ ነብያት ውሸትን ተቃምሰን አልነበረም። የሚሰማና የሚያይ አይን ይዘው መስማትና ማየት የተሳናቸው የእነዚህ የሃገር ኩርንችቶች መጨረሻ እንዲህ መሆኑ አምነው ለተደገፉባቸውና ዘርፈው ላዛረፏቸው ሁሉ ኦሮማይ ያሰኛል። በመሰረቱ ወያኔ ዲያብሎስ ነው። ገና ብዙ ጉድ እንሰማለን። ወያኔ ከ 40 በላይ በዘለቁ አመታት በትግራይ ህዝብና በመላው የሃገሪቱ ህዝብ ላይ የፈጸመው በደል ናዚ ጀርመኒ በአይሁዶች ላይ ከፈጸመው ይልቃል። አሁን በማይካድራ አማራዎችን መጨፍጨፉ ከግፉ በጭልፋ የሚያሳይ እኩይ ተግባር እንጂ የተንኮል መጽሃፉ ገና አልተከፈተም። በዙ ጉድ እናያለን እንሰማለን ገና!
የዛሬን አያድርገውና ሃገራችን የሰላም አየር ተንፍሳ፤ ሰው በሰውነቱ በሚሰላበት ዘመን የተዘፈነ አንድ የዘፈን ግጥም ትዝ አለኝ። ዘፋኙ እውቁ ጥላሁን ገሰሰ ሲሆን ገጣሚውና ግጥሙን ከዜማው ጋር ያዋሃደው ሰው ትዝ አይለኝም። የዘፈኑ ስንኝ እንዲህ ይላል።
“ግማሽ ጎኔ በሳቅ ግማሽ ጎኔ በሃዘን ተጨንቋል መንፈሴ ልሳቅ ወይስ ልዘን”። እንዲያ ነው የሚሰማኝ አሁን በሰሜን ሰራዊት ላይ የሆነውንና በወያኔ መቃብር ላይ ሰዎች አበባ ሲያስቀምጡ ስመለከት መጭውን የሃገሬን እድል ፈንታ ሳስብ ጭንቅ ጭንቅ ይለኛል። መሳቅም ማልቀስም ይቃጣኛል። መቼ ይሆን ያዘው ጥለፈው በለውና በያት የሚለው ቀርቶ በሰው መስፈሪያ ወገኔ ተሰፍሮ በሰላምና በጤና የሚኖረው? ያ ቀን ይመጣ ይሆን? ወይስ እንዲሁ እንደተናቆርን ከጊዜ ጋር እንሻገራለን?
አሁን ወደ ሱዳን የኮበለሉት የወያኔ ወመኔዎች ስደተኞች አይደሉም። የወያኔ የኋላ የክፉ ጊዜ ደጀን ሃይሎች እንጂ። ወያኔ እነዚህ ሰዎች የማይካድራን ሰዎች ጭፍጭፈው ወደ ሱዳን እንዲሻገሩ ያደረጋቸውም ለራሱ የወደፊት እኩይ ተግባር በማሰብ ነው። መመለስ ስለማይችሉ በሰሩት ግፍ የተነሳ የወያኔ አዲስ ምልምልና ጠበንጃ ተሸካሚ በግብጽና በሱዳን እየተረድ በዚህም በዛም ትንኮሳ ማድረጋቸው አይቀሬ ነው። ወያኔ የሚያስበው በበረሃ በተገጠመለት ጭንቅላት ነው ስንል እብዶች ናቸው ማለት ነው። የሳይኮሎጂ ሳይንስ አንድን ነገር ደጋግሞ ያለምንም ለውጥ እና የረባ ውጤት ማድረግ የጭንቅላት በሽታ ነው ይለናል። እነርሱ እንዲያ ናቸው። የክፋት ኮሮጆዎች በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ጭራቆች ናቸው። ከእነርዝራዣቸው ግባዕተ መሬታቸው ካልተፋጠነ ለትግራይ ህዝብም ሆነ ለቀሪው የሃገራችን ህዝብ ውጋት መሆናቸው አይቀሬ ነው። መንግስት በመረጃ የተደገፈ ወንጀል ከመሰረተባቸው የትኛውም የአለም ክፍል ቢሆን አሳልፎ እንደሚሰጣቸው እርግጠኛ ነኝ። ማንም አያስጠጋቸውም። ክሳቸው ግን ሲፈለግ የሚገኝ፤ በእውነት ላይ የተመሰረተ መሆን ይኖርበታል። ጊዜው መረጃ ይሻልና። አሁን በተደጋጋሚ ወደ አስመራ መተኮሳቸው መብገናቸውን ያሳያል እንጂ አቅሙ እንኳን አሁን ድሮም የላቸውም። ግን የኤርትራው መሪ ዝምታ የበለጠ አሳሯቸዋል። እንዲህ ነው ዝምታም መልስ ነውና! እስቲ ማን ይሙት ከቅርብ ጊዜ በፊት የኤርትራ ህዝብ ህዝባችን ነው ሲሉ እንዳልነበሩ አሁን በተውሶ ሮኬት ሊገድሉት ይፈልጋሉ? ይህ ፍጽም እብደት ነው። ግን ሙት ይዞ ይሞታል አይነት ስለሆነ ከተስፋ መቁረጥ የሚመነጭ ጭካኔ ለመሆኑ ይገባናል። ወያኔ ግን አፈር ለብሷል። የሽምቅ ውጊያ፤ የከተማ ውጊያ ገለ መሌ ቢሉም የትም አይደርሱም። የወያኔ አራጊ ፈጣሪነት ተቀብሯል።
ጠ/ሚ አብይ በሌሎቹ የሃገራችን ክፍሎች በወያኔ እየተላኩም ሆነ በራሳቸው ተነሳሽነት ወይም የግብጽ ክፍያ እየደረሳቸው በሃገራችን ህዝቦች ላይ የሚፈጸመውን በደል ለማስቆም አይቀጡ ቅጣት ሊሰጣችው ይገባል። በመሰረቱ ዋና ማሰልጠኛ ጣቢያው ሱዳን መሆኑን የአይን ምስክሮች ይናገራሉ። የተጠናከረ በውጭም በውስጥም የስለላ መረብ ሊኖር ይገባል። ድሮ በስለላ ስራ የተካኑ የንጉሱም ሆነ የደርግ ሰዎችን በአማካሪነት በማሰባሰብ አሁን ካለው ከዘመኑ የኤሌክትሮኒክስ የስለላ ስራ ጋር አጣምሮ ገዳዪችን በማፈን ለፍርድ ማቅረብ፤ ካልተቻለ ባሉበት መግደል፤ ሌሎችም ለሃገርና ለህዝብ ደህንነት ችግር የሆኑ ነገሮችን የሚያመክን ለህዝብና ለሃገር ተቆርቋሪ የሆነ የስለላ መረብ መዘርጋት አለበት፡፤ በዘሩና በሃይማኖቱ የሚያስብ ግለሰብ ለሃገራችን አይጠቅምም። ሃገራችን ገና ብዙ ውጣ ውረድ ይጠብቃታል። ሁላችንም ለሃገር አንድነትና ለህዝባችን ደህንነት ተጣምረን እንቁም። በቃኝ!
ባላውቅህም ተስፋ ሃሳብህንና መቆሮቆርህን እጋራለሁ::አንዳልከውም እብዶቹ የሚሰሩትን መገመት አስቸጋሪ ነውና መጠንቀቁ ተገቢ ነው::
ግና የዛሬ ሃምሳ ዓመት የነበረ የፖለቲካ: የኢኮኖሚ: የቴክኖሎጂና የባህል መልከዕምድር ዛሬ የለምና ስጋት አይኑረን::
በድሮ በሬ ያረሰ ወያኔ ብቻ ነው!!!!
ወዳጄ ታዛቢ እንደ እኔ እምብዛም ሥጋት ስለማይገባህ ደስ ይለኛል፡፡ አዎን በድሮ በሬ ያረሰ የለም፡፡ ግን እየከፈሉ እያሰለጠኑ እንደ በፊቱም ባይሆን በሚቻላቸው ሁሉ ሃገር ሰላም እንዳትሆን መፍጨርጨራቸው አይቀሬ ነው፡፡ ልንረዳ የሚገባው ነገር በሃገራችን የረጅም ጊዜ ታሪክ ውስጥ እንደ ወያኔ ያለ መርዘኛና ከፋፋይ ድርጅት ተፈጠሮ አያውቅም፡፡ የሰሜኑን እዝ ጄኔራል ገና ታሞ ሄደ የሚተካውንም ጄኔራል አንቀበልም አሉ ሲሉ ለጓደኞቼ መርዝ አብልተውት ነው ስላቸው ስቀውብኛል፡፡ የሆነው እንደዛ ነው፡፡ በ 27 ኣመት የመከራ አገዛዛቸው በልዪ ልዪ ሆስፒታሎች ባሰለፏቸው ገዳይ ሃኪሞች ለህክምና ወደዚያው ያቀኑ ሰዎች መርፌ በመውጋት የተገደሉ ብዙ ናቸው፡፡ ወያኔ የወንበዴዎች ጥርቅም ነው ስንል ቀማኛና በሰው ደም ነጋጅ መሆኑን አይናችን አይቶና ኑረንበት እንጂ በስማ በለው አይደለም፡፡ በምንም ሂሳብ ወያኔና የወያኔ አፍቃሪዎች አይታመኑም፡፡ የሃገራችን ጠላቶች የውጭ ሃይሎችና በዘርና በቋንቋ የሰከሩ እብዶች ናቸው፡፡ የወደፊት የሃገሪቱን እድል ፈንታ በተመለከተ እንዳንተ/ቺ የረጋ ልብ እንዲኖረኝ እታገላለሁ፡፡ ለአሁኑ መጨኔቄ አልቀረም፡፡