የትግራይ ጊዜአዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሙሉ ነጋ በጊዜአዊ አስተዳደሩ የሚሰሩ ስራዎችን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።
ዶ/ር ሙሉ በመግለጫቸው የትግራይ ክልል መዋቅር ዳግም እንደሚደራጅ ተናግረዋል።
የክልሉ ካቢኔና የዞን አስተዳደርም እንደአዲስ እንደሚዋቀርም የተናገሩት ዶ/ር ሙሉ የወረዳና የቀበሌ ምክር ቤቶች እንዳሉ ይቀጥላሉ ብለዋል።
መንግስት የጀመረውን የህግ ማስከበር እርምጃ እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ይሰራልም ብለዋል።
ከፅንፈኛው ህወሓት ቡድን ነፃ የወጡ አካባቢዎች ላይ መዋቅሮችን በመዘርጋት ህዝቡ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴው እንዲመለስ እንደሚሰራም ተናግረዋል።
የህወሓት ፅንፈኛ ቡድን ላለፉት ሁለት ዓመታት ተኩል በክልሉ ምንም አይነት የልማት ስራ አልተሰራም ያሉት ዶክተር ሙሉ ህግ የማስከበሩ ስራ ሲጠናቀቅ የክልሉን ምጣኔ ሀብት ለመታደግ የልማት ስራዎች ይጀመራሉ ብለዋል።
ጥያቄ የሚነሳባቸው አካባቢዎች ላይም የወሰን ማስከበርና በማንነት ኮሚሽን በኩል በሚሰጡ አቅጣጫዎች መሰረት ይከናወናሉ ብለዋል።
ዶ/ር ሙሉ የክልሉን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ፣ የተጎዳውን ምጣኔ ሀብት ለመመለስ የልማት ስራዎች ማከናወንና ፍትሃዊ የአመራሮች ምርጫ እንዲካሄድ ማድረግ ዋነኛ የጊዜአዊ አስተዳደሩ አቅጣጫ መሆናቸውንም ተናግረዋል። (ዋልታ)
Leave a Reply