መላ ሰውነቱ ይንቀጠቀጣል፤ ከንፈሩ ደርቋል። ለሁለት ቀናት ምግብ አላገኘም። ድንጋጤ አለቀቀውም። ከማይካድራ ግድያ አምልጦ ሁመራ ከተማ መከላከያ ሠራዊት ካምፕ በር ላይ ያገኘነው ወጣት ዳንኤል ማሚን።
የደቡብ ክልል የቴፒ ተወላጅ ነው፤ አገር ሰላም ብሎ በማይካድራ ልብስ እየነገደ መኖር ከጀመረ 13 ዓመት ሆኖታል። በዚች ከተማ ይህን ያህል ሲኖር የከፋ አይደለም፤ ቀለል ያለ ችግርም አጋጥሞት አያውቅም። በሚኖርባትና ህይወቱን ለማሻሻል በሚደክምባት ከተማ ቤትና ንብረትም አፍርቷል።
ከሰባት ቀናት በፊት ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ በማይካድራ ከተማ በአማራና በሌሎች ብሄሮች ተወላጆች ላይ ያልታሰበ፣ አስደንጋጭና ዘግናኝ ግድያ ሲፈጸም በዓይኑ ተመልክቷል፤ እሱም ከዚህ ዘግናኝ ጭፍጨፋ አምልጦ በመከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ስር ወደ ዋለችው ሁመራ ከተማ መምጣቱን ይናገራል።
የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሻዎች በአማራና በሌሎች ብሄሮች የፈጸሙት ግፍና ግድያ በጣም የሚያስደነግጥ ያልታሰበ ነበር የሚለው ወጣቱ፤ በትግራይ ክልል ማይካድራ ከተማ በምንኖር ንጹሐን ሰዎች ላይ በትግራይ ሚሊሻዎችና ልዩ ኃይሎች ዘግናኝ ጥቃት ይደርስብናል ብለን አስበንም አልመንም አናውቅም። ግን የጭካኔያቸው ጭካኔ በከተማዋ በሚኖሩ አማራን ጨምሮ በሌሎች ብሄሮች ዘግናኝ ድርጊት ፈጸሙ ይላል።
“መጀመሪያ ላይ ጥቃቱን የጀመሩት በወልቃይት አማራዎች ላይ መሆኑን የሚገልጸው ወጣት ዳንኤል ንጹሐን ሰዎችን በየመንገዱ እየደበደቡ፤ በሳንጃ አንገታቸውን እየቀሉ ሲገሏቸው ተመልክቻለሁ። ሰው ሮጦ እንዳያመልጥ እንኳን መንገዱ በሚሊሻ ተከቧል። ሩጠው ለማምለጥ የሚሞክሩትን በጭካኔ በጥይት እየመቱ ገድሏቸዋል” ብሏል።
በአይኔ ሰው ሲገደል አይቻለሁ። እኔም የዳንኤል ቤት የትኛው ነው እያሉ ሲጠይቁ ሰምቼ ሩጬ ማምለጥ ችያለሁ የሚለው ወጣቱ፤ በዚህ ቀውጢ ስዓት እሱም ሆነ ብዙ በርካታ ሰዎች እየሮጡ ጫካ ባይገቡና ባያመልጡ ኖሮ በማይካድራ ከተማ በግፍ እንደተገደሉት ንጹሐን ሰዎች ሁሉ የእሱም ዕጣ ፋንታ በህወሓት አሸባሪ ቡድን ይገደል እንደነበር ነግሮናል።
ሰዎች ሲገደሉ በዓይኑ ማየቱን የሚገልጸው ወጣት ዳንኤል ሁለቱ ከድብደባው ለማምለጥ ሲሮጡ በጥይት ሁለቱ ደግሞ በሳንጃ አንገታቸውን ተወገተው አስፓልት ላይ ሲወድቁ እግሬ አውጪኝ ብሎ ከአካባቢው ተሰውሮ ጫካ መግባቱን ንግሮናል። ሰው በጭካኔ እየተገደለ ባየሁበት ከተማ ለመኖር አልጓጓም ያለው ወጣቱ ከሁመራ ወደ ጎንደር ከዚያም ወደ ትውልድ አገሩ ቴፒ ለመሄድ መወሰኑን ገልጾልናል።
ወጣት ዳንኤል፤ በትግራይ ክልል ማይካድራ ከተማ የህወሓት ጸንፈኛ ቡድንን ያልደገፈ የሚደርስበት ጫና እንግልት ከፍተኛ መሆኑን ይናገራል። ለትግራይ ልማት የሚሆን ገንዘብ አዋጣ ሲሉኝ 100.00 ብር አዋጣሁ። ሁለተኛ ዙርም ለውጊያ አዋጣ አሉኝ። እኔም ውጊያውን ስለማላምንበት ብር የለኝም አልኳቸው። ለካስ ያላዋጣነው ሰዎች የቀበሌው የህወሓት ተላላኪዎች የስም ዝርዝራችንን ይዘው ኑሯል፤ ጊዜ ጠብቀው የበቀል ጭካኔያቸውን አወረዱብን።
“በየመኖሪያ ቤታችን እየዞሩ እስከ ወዲያኛው ሊያስናብቱን እየገሰገሱ መጡ። እግዚአብሔር አትርፎኝ ይኸው ሁመራ ከተማ አግኝተኸኛል” ሲል የጭካኔያቸው ጥግና የበቀል ዕርምጃቸው ከባድ መሆኑን ገልጾታል።
ማይካድራ ከተማ ውስጥ የሚኖር ማንኛውም የከተማው ነዋሪ ከትግራይ ቴሌቪዥንና ከወያኔ ድምፅ ቴሌቪዥን በስተቀር ሌሎች የቴሌዥን ጣቢያዎችን ማየት ወንጀል ነው የሚለው ወጣቱ፤ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን፣ ዋልታ፣ ፋና ቴሌቪዥንና ሌሎች ህወሓት የሚጠላቸውን የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ማየት ፈጽሞ የተከለከለና የሚያስቀጣ ነው። ሲያይ የተገኘም ካለ በህይወቱ የፈረደ ሰው ብቻ ነው ይላል።
ማይካድራ በመከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ስር ውሏል ማይካድራ ለምን አትምለስም የሚል ጥያቄ አቅርበንለት የወጣቱ ምላሽ ሌላ አካባቢ ሊስትሮም ቢሆን ሠርቼ መኖርን እመርጣለሁ እንጂ ሁለተኛ ትግራይ ክልል አልኖርም። ምክንያቱም ያየሁት የጭካኔ አገዳዳል ሌሊት በህልሜ ይመጣብኛል። ዘግናኝ ነው። ይህን እያስብኩ እዚያ ከተማ መኖር አልፈልግም። ህይወቴ ተመሰቃቅሏል ሲልም ያየው የጭካኔ ተግባር የቱን ያህል እንደጎዳው፣ ከቃላቶቹ በላይ ሁኔታውን ሲያስታውስ የሚሰማው ስሜት ይናገራል። (በጌትነት ምህረቴ፤ አዲስ ዘመን ህዳር 8 ቀን 2013 ዓ.ም)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Tesfa says
አለም ከወደ ቻይና መጣ በተባለው ቫይረስ እየታመሰች ባለበት በዚህ ክፉ ጊዜ ወያኔ አብሮ የበላውን ወገኑን ከውስጥና ከውጭ ጥቃት በመፈጸም መግደሉ፤ ማረድ ከዚያ ደግሞ ለአለም ህብረተሰብ የውሸት ፕሮፓጋንዳ በመንዛት ተበደልኩ ማለቱ ምን ያህል ለትግራይ ህዝብ እንደማይገደው አበክሮ ያሳያል። ምሎ የሚገዘትበት ይህ ህዝብ በስሙ ተነገደበት እንጂ አንድም የተረፈው ነገር የለም። 1 ለ 5 በተባለ ኮሚኒስታዊ አወቃቀር ተጠርፎ የተያዘው የትግራይ ህዝብ የቁም እስረኛ የሆነው ገና ድሮ ነው። የማይገባኝ ግን በየአለማቱ ተሰደውና በወያኔ የስለላ መረብ በትምህርትና በንግድ ተሰማርተው ያሉ የትግራይ ተወላጆች እውነትን ከውሸት መለየት አለመቻላቸውና ለዚህ አጥፊ ቡድን ደጋፊ መሆናቸው የበለጠ ያስገርመኛል። አሁን ማን ይሙት በትግራይ ውስጥ ዲሞክራሲ ኑሮ ያውቃል? ተጨፈኑና ላሞኛቹሁ የሚለው ወያኔ እኔ በስልጣን ቁንጮ ላይ ካልሆንኩ ማበዴ ነው በማለት የሚጠብቀውን የሰሜን እዝ መጨፍጨፉ የሂሳብ ስሌቱ ከመቀነስና መደመር ያላለፈ በተገዛ ዲግሪ ይህ አለኝ ያን ይዣለሁ የሚሉ ሙታኖች የተሰባሰቡበት መሆኑን ያመላክታል። የጠራ እይታ ላለው ባለንበት ጊዜ ጠበንጃ ይዞ አካኪ ዘራፍ ማለት የኋላ ቀርነት ምልክት ነው። ለነገሩ ወንድምና እህቱን ገድሎ በአስከሬናቸው ላይ የሚጨፍር ሙት የራሱን መሞት ለጊዜው ቢዘነጋም አይቀርለትም። የሃበሻው መገዳደል የወረፋ መጫረስ ነው። እኮ ታገሱ ላስረዳ። በንጉሱ ጊዜ በኮንጎ፤ በኮሪያ በሌሎችም የውጭና የሃገር ውስጥ ፊልሚያዎች የተካፈሉ ደርግ ሲመጣ የአባት ጦር በማለት አስጨረሳቸው። ወያኔና ሻቢያ በዳቦ ሲጣሉ ወያኔ ተወረርኩ ኑ ድረሱልኝ በማለት ጡረታ ላይ የነበሩ የደርግ ዘመን ወታደሮችን ያባረራቸውን ሁሉ በመጥራት አስፈጃቸው። አሁን ደግሞ አርፈው የሚያርሱትን፤ አታስፈልጉኝም ብሎ ከወያኔ ሰራዊት የቀነሳቸውን ትግራይ ትፈልጋቹሃለች በማለት ማገዳቸው። እንዲህ እያለ ገዳይን ሌላ ገዳይ እየገደለው፤ አመለጥኩ ተረፍኩ ያለውም ለሌላ ፍትጊያ እየተጠራ ምድሪቱ በደም ትታጠባለች። ይህ ነው የጉረኛውና የገዳዪ እጣ ፈንታ። እኖራለሁ ሲል እሳት ይነድበታል።
ወያኔ በአማራ ህዝብ ላይ ያለው ጥላቻ ከልቡ አልፎ አጥንቱ ውስጥ ነው። በአይናችን አይተነዋል። ገና ብዙ ጉድና ጉድጓድ ይማሳል። ይህ ድርጅት የማፍያ ድርጅት ነው ስንል ከተግባራቸው ተነስተን እንጂ ዝም ብሎ ከሚያልፍ ወንዝ የተቀዳ ወሬ ይዘን አይደለም። ወያኔ ከፍሎና አባብሎ ከሱዳን የለቀማቸውን የኢህአፓ አባላት ያለምንም ፍርድ በአንድ አሳቻ ስፍራ በጥይት ደብድቦ ገድሏቸዋል። ወያኔ የሃገራንች ነቀርሳ ነው። መግደል፤ ማፈን፤ መርዝ ማብላት፤ በመኪና ገጭቶ ገድሎ ተቀልብጦ ወይም ተጋጭቶ ሞተ ማለት የየቀኑ ሙሉ ስራቸው ነው። የራሳቸውን ስዎች ጭምር ገድለዋል። እውቁ ዘፋኝ እያሱ በርሄ፤ ታዋቂው አዋጊ ጄ/ሃያሎም ግድያ እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል። በውሸት ትርክት የሰከረው ወያኔ ሃርነት ትግራይ ለአማራ ህዝብ ናዚ ለአይሁዶች እንደነበረው ነው። ስንቶች በሜዳ ተገለዋል። ስንቶች ታፍነው የገቡበት ሳይታወቅ ቀርቷል። ስንቶች እንዳይወልዱ መርፌ ተወግተዋል። የስንቶች ሃብትና ንብረት ተዘርፎ ወደ መቀሌ ተጓጉዟል? ቤቱ ይቁጠረው። የአማራ ህዝብ ራሱን አስታጥቆ፤ ሁሌ ንቁ ሆኖ የጎረቤቱንና የሌላውን መብት ጠብቆ የራሱን መብት ማስጠበቅ እስካልቻለ ድረስ ወያኔና ጄሌዎቻቸው አማራን ከማጥፋት አይመለሱም። ዘግናኝና ሰቅጣጭ ተግባሮችን በእስር ቤት የፈጸመው ወያኔ እንስሳ እንጂ የሰውነት ባህሪ የላቸውም። ወንጀላቸውን በመረጃ በማሰባሰብና ፎቶአቸውን በአለም ላይ በመልቀቅ የትም ይደበቁ የትም በውጪው አለም ተይዘው ፍርድ እንዲያገኙ ማድረግ ይቻላል። ችግሩ መረጃ አልባ ፍርድ ቤት በስማ በለው ነገር አይቀበልም። የአይን ምስክሮች፤ ከሞት የተረፉ የቆሰሉ ሰዎች፤ የሞቱ ሰዎች ስምና አድራሻ፤ ሞታቸው ራሱ በፎቶ መደገፍ አለበት። እንዴት የሞተ ሰው ፎቶ ይነሳል የምትሉ ሁሉ ወገባችሁን ጠበቅ አርጋችሁ ማንሳትና መቅረጽ አለባችሁ። በማይካድራ የተሰራው ስራ በሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች በኦነግ ተላላኪዎቻቸው ከፈጸሙት ጭካኔ ጋር ይመሳሰላል። የተጠቀሙበት መሳሪያ፤ የአገዳደል ስልታቸው፤ እነማን ላይ እንዳተኮሩ ዋና አስተሳሳሪ ነገሮች ናቸው። ስለዚህ መረጃ አስፈላጊ ነው ይሰባሰብ፤፡
አሁን ድልድይ አፈረሱ፤ መንገድን ቆፈሩት ይሉናል መረጃው የት አለ? ግልጽ ሆኖ ለህዝብ መቅረብ አለበት። ደግሞ መግለጫ በመግለጫ ሆነናል። የሚባል ነገር አለ፤ የማይባል ነገር አለ፡፤ ዝም ብሎ መለፍለፍ ምን ይሉታል። የጦር መሪ ሆኖ ማስታወሻ ሳይዝ፤ የስፍራዎችን ቦታ ሳያውቅ፤ ጋዜጣዊ መግለጫው የሚዳክር የስንቱ ነው። እንዴት ሰው ረጋ ብሎ ደረጃ በደረጃ ነገሮችን ማስረዳት ይከብዳል? ሁሉም ጥያቄ መልስ የሚያስፈልገው አይደለም። ማለፍም መልስ ነው።
በመጨረሻም ድብቅ የወያኔ አባሎች በአዲስ አበባ፤ በሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች፤ በጦርና በፓሊስ፤ በአመራር ላይ አሉ። ትልቅ ጉዳት ሊያደርሱ ስለሚችሉ ጥንቃቄ መደረግ አለበት። ለምሳሌ በውጭ የሰላም አስከባሪ ጦር ጋር ያሉት ይበልጦቹ እነርሱ ናቸው። ተራ ወታደሩን መቶ አለቃ እያሉ ነው ገንዘብ የሚያገኙባቸው። ስለሆነም ሌሎችን እንዳይጎዱ ጥብቅ ምርመራ መደረግ አለበት። ወያኔ ያልገባበት፤ ያልቆፈረው ጉድጓድ በሃገሪቱ ውስጥ የለም። ያላቸው ማንኛውም ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀስ ሃብት ሁሉ ሊፈተሽና ገቢያቸው ሊደርቅ ይገባል። ሃገርን የወጋ ከወጋው ሃገር ሃብት ማፍራት አይችልም። የአማራ ህዝብ ንቃ ጠላትህን እወቅ። ትላንት በቅማንትና አማራ እየከፋፈለ ያጋደለህ ወያኔ ነው። ዛሬም አያርፉልህም። መደራጀት ተገቢ ነው። በቃኝ!