በደብረ ታቦር 800 መቶ ብር የነበረ የምግብ ዘይት እስከ 1500 ብር ድረስ እየተሸጠ ነው በአማራ ክልል በትልልቆቹ ከተሞች በዛሬው ዕለትም ተኩስ ሳይሰማባቸው መዋላቸውን፤ ነገር ግን መደበኛ እንቅስቃሴ እንዳልተጀመረ ነዋሪዎች ገልጸዋል። ነዋሪዎች ምን አሉ? ባሕር ዳር ዛሬ የተኩስ ድምጽ አለመሰማቱን ፤ ግጭትም ይሁን ውጊያ እንዳልነበር ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። ነገር ግን መደበኛ እንቅስቃሴ አልጀመረም። የንግድና የተለያዩ ቋማት በአብዛኛው ባለመከፈታቸው ከተማዋ ጭር ብላ ነው የዋለችው። የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ መኪኖች እና ባጃጆች ወደ ሥራ ባለመመለሳቸው የነዋሪው እንቅስቃሴ ተገትቶ ውሏል። ተቋርጦ የነበረው የ 'ኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ' ወደ ባሕር ዳር መጀመሩን ነዋሪዎች ገልጸዋል። ነገር ግን ከአውሮፕላን ማረፊያ ወደ ከተማ የሚወስድ ትራንስፖርት … [Read more...] about የአማራ ክልል ትልልቅ ከተሞች ተኩስ ዓልባ ሆነው ውለዋል
News
በሕዝቡ ድጋፍ ከተሞች ከዘራፊው መንጋ ሥጋት ነጻ መሆናቸው ይፋ ሆነ
ከአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ ያከናወናቸውን የመጀመሪያ ምዕራፍ ተግባራት ገምግሟል፡፡ የዕዙ የመጀመሪያ ምዕራፍ ዕቅድ በባሕር ዳር፣ ደብረ ማርቆስ፣ በደብረ ብርሃን፣ በላሊበላ፣ በጎንደርና በሸዋ ሮቢት አካባቢ የተሰባሰበውን በዘረፋ እና በጥፋት የተሰማራ ቡድን በመምታትና ከተሞቹን ወደ ሰላማዊ ሁኔታ መመለስ ነበር። እነዚህ አካባቢዎች የተመረጡት ብዙ ሕዝብ የሚኖርባቸው፣ ከፍተኛ የንግድና የቱሪስት እንቅስቃሴ ያለባቸው፣ የፖለቲካና የኢንዱስትሪ ማዕከላት በመሆናቸው ነው። በዚህ መሠረት በስድስቱ ከተሞች ዙሪያ የመጣው የጥፋት ቡድን መሣሪያውን እንዲያስረክብና እጁን እንዲሰጥ የተሰጠውን ዕድል ባለመጠቀሙ እርምጃ ተወስዶበታል፣ የሕግ የበላይነትም እንዲከበር ተደርጓል። የክልሉ ሕዝብ በዚህ ዘራፊ ቡድኑ … [Read more...] about በሕዝቡ ድጋፍ ከተሞች ከዘራፊው መንጋ ሥጋት ነጻ መሆናቸው ይፋ ሆነ
ትህነግ አራተኛውን ሞት ሞተ
የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ትህነግ) ወይም ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ተብሎ በሚጠራው የወንበዴ ቡድን ስም አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ለመመስረት የቀረበውን ውሳኔ ፍርድ ቤት ውድቅ አደረገ። በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የምርጫ ጉዳይ ክርክር ችሎት በምርጫ ቦርድና እነ’ገ/ሚካኤል ተስፋዬ መካከል የተደረገው ክርክር ውሣኔ አግኝቷል። በህወሓት ስም የሚጠራ ለረጅም ዓመታት የሚታወቅ ፓርቲ የነበረ በመሆኑ በዚሁ ስም አዲስ ፓርቲ ማቋቋም መራጩን ያደናግራል ተብሏል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕ.ወ.ሓ.ት) ስም ክልላዊ ፓርቲ ለመመሥረት የቀረበለትን የቅድመ ዕውቅና ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል። ይህንን ተከትሎ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ያቀና ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና በእነ’ገ/ሚካኤል ተስፋዬ መካከል … [Read more...] about ትህነግ አራተኛውን ሞት ሞተ
“ሃሳብ ሲነጥፍ ነፍጥ አንግቤ እዋጋለሁ” የሚሉ አካላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል – የመከላከያ ሠራዊት
አሁናዊ የመከላከያ ሠራዊቱን ያለበትን ሁኔታ በተመለከተ የኢፌዴሪ የመከላከያ ሠራዊት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት መግለጫ ሰጥቷል። መግለጫውን የሰጡት የሠራዊቱ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ፣ መግለጫው በተለያዩ አካላት በሠራዊቱ ላይ እየተናፈሱ ያሉ ብዥታዎችን ለማጥራት የተሰጠ ነው ብለዋል። ሠራዊቱ ካለፉት ዓመታት በነበረበት ቁመና ላይ እንዳለ የሚያስቡ አካላት ካሉ የቆሙት እነርሱ እንጂ ሠራዊቱ ተራማጅ ነው ያሉት ኮሎኔል ጌትነት፣ ሠራዊቱ ዘርፈ ብዙ ግዳጁን እየተወጣ ነው ብለዋል። "ሃሳብ ሲነጥፍ ነፍጥ አንግቤ እዋጋለሁ" የሚል አካል ላይ ሠራዊቱ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል። ሠራዊቱን መቋቋም ያልቻሉ አካላት በሠራዊቱ ላይ ሰፊ የስም ማጥፋት ዘመቻ ላይ ይገኛሉም ነው ያሉት ኮሎኔል ጌትነት። በተለይ አሁን ላይ … [Read more...] about “ሃሳብ ሲነጥፍ ነፍጥ አንግቤ እዋጋለሁ” የሚሉ አካላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል – የመከላከያ ሠራዊት
ደቡብ አፍሪካ የመሸጉ ወንጀለኞች ለሕግ ተላልፈው ሊሰጡ ነው
ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን አሳልፎ ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል። አራተኛው የኢትዮ-ደቡብ አፍሪካ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ በአዲስ አበባ ተካሂዷል። በስብሰባው ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የደቡብ አፍሪካ የዓለም አቀፍ ግንኙነቶችና ትብብር ሚኒስትር ዶክተር ናሌዲ ፓንዶር እንዲሁም የሁለቱ አገራት ባለስልጣናት ተሳታፊ ሆነዋል። በዚህ ወቅት ሁለቱ አገራት በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን አሳልፎ ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱን የፍትሕ ሚኒስትር ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ እና የደቡብ አፍሪካ የዓለም አቀፍ ግንኙነቶችና ትብብር ሚኒስትር ዶክተር ናሌዲ ፓንዶር ተፈራርመዋል። ሁለቱ አገራት በስብሰባው ንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ሳይንስ፣ ኢኖቬሽን፣ ትምህርት፣ … [Read more...] about ደቡብ አፍሪካ የመሸጉ ወንጀለኞች ለሕግ ተላልፈው ሊሰጡ ነው
“ከማንም ጋር ግጭት አንፈልግም በማንነታችን ላይ ግን ዳግም ለአፍታ እንኳን ተዘናግተን የተራዘመ መከራ እና ባርነት ለመቀበል ፍጹም” አንፈቅድም ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ
የግማሽ ምዕተ ዓመት ገደማ ሴራ እና ተንኮል መጋለጫ፣ የሩብ ምዕተ ዓመት አምባገነናዊ አገዛዝ መሸኛ፣ የሦስት አስርት ዓመታት የጨለማ ጉዞ ምዕራፍ መቋጫ እና የአዲሱ ትውልድ የነጻነት አደራ ርክክብ ትናንት በቅርቡ የተስተዋለ ክስተት ነበር፡፡ እልፎች ማንነታችን ይከበር ብለው አደባባይ ድረስ ዘልቀው በመውጣት የከበረ መስዋዕትነት ሲከፍሉ ከተፈጥሯዊ ነጻነት ባሻገር የጠየቋቸው እና ለትግል የሚያበቁ አያሌ ምክንያቶች ነበሯቸው፡፡ ማኀበረሰባዊ ማንነትን የሚያስቀጥል ትግል ደግሞ በትውልድ ቅብብሎሽ መካከል የሚጸና የነጻነት መርከብ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ለማንነት መከበር በሚደረግ ትግል ውስጥ ውስኖች እንደ አብሪ ኮከብ ጎልተው ቢታዩም የትግሉ ባለቤት እና ሞተር ግን ሕዝብ መኾኑ አይካድም፡፡ የወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት እና ራያ ሕዝብ የዘመናት የነጻነት ትግል መልህቅ በታሪክ አጋጣሚ በአዲሱ … [Read more...] about “ከማንም ጋር ግጭት አንፈልግም በማንነታችን ላይ ግን ዳግም ለአፍታ እንኳን ተዘናግተን የተራዘመ መከራ እና ባርነት ለመቀበል ፍጹም” አንፈቅድም ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ
የተሰረቁ የሞባይል ስልኮች (215) በህጋዊ ስም በተከፈቱ የንግድ ሱቆች ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋሉ
በተለያዩ አካባቢዎች የተሰረቁ ከሁለት መቶ በላይ የሞባይል ስልኮችን በህጋዊ ስም በተከፈቱ የንግድ ሱቆች ውስጥ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖለስ አስታውቋል፡፡ በቦሌ ክፍለ ከተማ በህጋዊ የሞባይል ስልክ እና የቴሌቪዥን ጥገና ሱቅ ሽፋን ከግለሰቦች የተሰረቁ ስልኮችን እየገዙ ሲሸጡ ከነበሩ ግለሰቦች ሱቅ ውስጥ 215 ሞባይል ስልኮች መያዛቸው ታውቋል፡፡ የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ እና ባደረገው ክትትል በወረዳ 3 ኤድናሞል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሞባይል ጥገና ስራ በሚሰሩ አራት የንግድ ሱቆች ላይ ትናንት ሃምሌ 19 ቀን 2015 ዓ.ም በህግ አግባብ በተከናወነ ብርበራ ነው ከተለያዩ ቦታዎች ተሰርቀው የተከማቹ ሞባይል ስልኮች ሊያዙ የቻሉት፡፡ ከሞባይል ስልኮቹ በተጨማሪ የወንጀል ፍሬ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ እና በጥገና ቤቶቹ ውስጥ የተገኙ የተለያየ … [Read more...] about የተሰረቁ የሞባይል ስልኮች (215) በህጋዊ ስም በተከፈቱ የንግድ ሱቆች ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋሉ
የዓለም ባንክ የ400 ሚሊዮን ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ ለኢትዮጵያ ሰጠ
ኢትዮጵያ ከዓለምአቀፍ ተቋማት ምንም ዓይነት ብርድም ሆን ድጋፍ እንዳታገኝ ከአገር ውስጥ የራሷ ልጆችና ከውጭ ውድቀቷን የሚመኙ አገራት የተለያየ ተጽዕኖ ሲያደርሱባት ቆይተዋል። የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ትህነግ) ኢትዮጵያን የአንድ ቤተሰብ ጥቅም ማስጠበቂያ አድርጓት በነበረበት ጊዜ ከበጀት ድጎማ ጀምሮ ማንኛውንም ዓይነት ብድር፣ ዕርዳታ፣ ድጋፍ ወዘተ ለአጋዚ ጦር ደመወዝ የሚከፍለው ጭምር ዓለምአቀፋዊ የገንዘብ ተቋማት ድጎማ ሲደርግለት መቆየቱ የሚታወስ ነው። ትህነግ ከአራት ኪሎ ከለቀቀ ወዲህ ግን እሹሩሩ ሲሉት የነበሩት ዓለምአቀፋዊ የገንዘብ ተቋማት የተለያየ ምክንያት በመሰጠት ተገቢው ድጋፍ አቁመዋል፤ ብድር ለማግኘት እንኳን ትህነግ ሲዘርፍ የኖረውን ብድር እንደ ምክንያት በመጥቀስ ለዓቅመ ብድር አልደረሳችሁም እያሉ ኢትዮጵያን ለማዳከም ብዙ ጥረዋል። በውጪ ያሉት … [Read more...] about የዓለም ባንክ የ400 ሚሊዮን ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ ለኢትዮጵያ ሰጠ
የማዳበሪያ ዕጥረት አለ በሚባልበት የአማራ ክልል 400 ኩንታል ማዳበሪያ ተያዘ
አቶ ዮሐንስ ቧያለው በክልላቸው ምክር ቤት ፊት ስለ ማዳበሪያ አቅርቦት ዕጥረት አምርረው በተናገሩና የክልሉ ገብርና ቢሮ ሥራ መሥራት ያልቻለ ደመወዝ በነጻ የሚበላ ነው ብለው ባፌዙበት ማግስት በአማራ ክልል 400 ሺህ ኩንታል ማዳበሪያ በሕገወጥ መልኩ ሲሰራጭ መያዙን ኢቢሲ ዘግቧል። በአማራ ክልል ማዳበሪያን የፖለቲካ መጠቀሚያ ለማድረግ ሲወራ የሰነበተው ሤራ ምን እንደሆነ ማሳያ ነው። የዜናው ሙሉ መረጃ ከዚህ በታች ቀርቧል። 400 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር በቁጥጥር ሥር ዋለ መነሻውን ከጅቡቲ ወደብ አድርጎ መዳረሻውን ወረታ ከተማ ለማድረግ የተንቀሳቀሰው 400 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ የጫነ ተሳቢ ተሽከርካሪ፤ ከታሰበው ቦታ ሳይደርስ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡ ሕገ ወጥ ድርጊቱ የተፈጸመው በባህርዳር ከተማ … [Read more...] about የማዳበሪያ ዕጥረት አለ በሚባልበት የአማራ ክልል 400 ኩንታል ማዳበሪያ ተያዘ
33.5 ሚሊዮን ሕዝብ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ መቀበሉ ታወቀ
በሕዝቡ ተሳትፎ እጅግ ከፍተኛ ኩራት ተሰምቶኛል ሞራልም ሰጥቶኛል በማለት አድንቀዋል ሲነጋ … በመላ ሀገሪቱ በአንድ ቀን ውስጥ 500 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ዘመቻ ከጥዋት አንስቶ እየተካሄደ ይገኛል። ዘመቻው እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ እንደሚቆይ ነው የተነገረው። በችግኝ ተከላ ዘመቻው ላይ የሃይማኖት አባቶች፣ እናቶች ፣ ህፃናት፣ ታዳጊዎች፣ ወጣቶች፣ የተለያዩ ተቋማት ሰራተኞች፣ የውጭ ሀገር ዲፕሎማቶች እና ሌሎችም እየተሳተፉበት ይገኛሉ። የኢፌዲሪ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ ኢትዮጵያን አረንጓዴ የማልበስ ስራ የፖለቲካ ጉዳይ ፣ የፓርቲያቸው ፕሮግራም እንዲሁም የመንግሥት ጉዳይ እንዳልሆነ ከዚህ ቀደም ገልጸዋል። ይህ ጉዳይ " የኢትዮጵያ ጉዳይ " እንደሆነና በዚህ የችግኝ ተከላ ዘመቻ አረንጓዴ የምትለብሰው ኢትዮጵያ … [Read more...] about 33.5 ሚሊዮን ሕዝብ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ መቀበሉ ታወቀ