በአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ኮንግረስ) አባል የሆነችውና ትውልደ ሶማሊያዊቷ ኢልሃን ዑመር፣ የሀገሪቱ የፌደራል መርማሪዎች ባደረጉት ጥልቅ ፍተሻ ዜግነቷ ተሰርዞ (Denaturalize) ከአገር ልትባረር የምትችልበት ከባድ የወንጀል ምርመራ ውስጥ መውደቋ ታውቋል። በተጨማሪም የጎልጉል ምንጮች እንዳረጋገጡት፣ ይህችው የኮንግረስ አባል በኢትዮጵያ ላይ የጥፋት ስራዎችን ከሚሰሩ እና ሀገሪቱን ለማፍረስ ሌሊትና ቀን ከሚንቀሳቀሱ ፀረ-ኢትዮጵያ የታጠቁ ቡድኖች እና የፖለቲካ ኃይሎች ጋር በቅርበት ስትቀናጅና ስትሠራ እንደነበር ታውቋል። ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ የፌደራል ወኪሎች በዋሺንግተን ዲሲ የሚገኘውን የኢልሃን ዑመርን መኖሪያ ቤት በድንገት በመውረር ፓስፖርቷንና ስልኳን ይዘዋል። ምርመራው የተጀመረው በጆ ባይደን … [Read more...] about ዜግነት ሊያሰርዝ በሚችለው የኢልሃን ዑመር ምርመራ ላይ አዳዲስ መረጃ ተገኝቷል

