• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በዌብስፕሪክስ ኃ.የ.ግ.ማ. ባለአክሲዮኖች መካከል የተፈጠረው የሕግ ክርክር እና መሥራቹ አቶ ዳዊት ብርሃኑ

November 26, 2026 01:41 pm by Editor Leave a Comment

በኢትዮጵያ የብሮድባንድ ኢንተርኔት እና ዲጂታል አገልግሎት በግሉ ዘርፍ የመጀመሪያ የሆነው ዌብስፕሪክስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (Websprix PLC) መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳዊት ብርሃኑ እና በሌሎች ተከሳሾች መካከል የተፈጠረው የባለአክሲዮኖች አለመግባባት ወደ ፍርድ ቤት ክርክር ማምራቱ ዜና ከሆነ ከራርሟል።

“ጉዳዩ ከዜና በላይ ነው፤ እንደተራ የጨውና የበርበሬ አክሲዮን የሚታይ አይደለም። ዘርፉን ለሚረዱና አሁን ላይ ዓለምን እየናጠው ያለውን የሳይበር ጥቃት ለሚረዱ ጉዳዩ ብሔራዊ ስጋት በመሆኑ መንግሥት ዝም ሊል አይገባም”  በሚል ጥቅል አቋም “የቴሌኮም ጌትዌይ፣ የዳታ ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ደህንነት – የዌብስፕሪክስ ጉዳይ ከባለቤትነት ክርክር በላይ ነው!” መነሻ አሳብ የማሳሰቢያ ጽሁፍ አቅርቤ ነበር።

የቴሌኮም ጌትዌይ፣ የዳታ ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ደህንነት – የዌብስፕሪክስ ጉዳይ ከባለቤትነት ክርክር በላይ ነው!

ጽሁፉን ሳቀርብ “ጉዳዩ ለገባችሁ” ወገኖች መምታታት እንዳይኖር የፍርድ ቤቱን ጥቅል ይዘት፣ የአቶ ዳዊት ብርሃኑንም የትምህርት ሁኔታና እዚህ የደረሱበትን ልምድ ብጠቁም ደግ እንደሆነ አስታውቄ ነበር።

ከበርካታ የሽምግልና ሂደት በኋላ ወደ ፍርድ ቤት የሄደው ጉዳይ እንዴትና በምን ሁኔታ እንደሆነ ለማመላከት እንዲህ ለያይቼ አቅርቤያለሁ።

1.     የክርክሩ መነሻ እና የግንኙነት ዳራ

በፍርድ ቤቱ መረጃ መሠረት፣ ከሳሽ አቶ ዳዊት ብርሃኑ ከሌሎች ባለአክሲዮኖች ጋር ለበርካታ ወራት ድርድር እና ሽምግልና ቢያደርጉም ስምምነት ባለመፈጠሩ ክሱን ለመመሥረት ተገድደዋል። በክርክሩ ውስጥ አበባው ደስታ፣ መቅደስ አክሊሉ፣ አብርሃም ምንውየለት፣ 1 አክሲዮን ወይም 0.01% ድርሻ ያላቸው ዳንኤል አዳነ እና ሚካኤል አበባው እንዲሁም የሕግ ሰውነት ያለው ዌብስፕሪክስ ኃ.የ.ግ.ማ. እንደ ተከሳሽ ተጠቅሰዋል።

በክሱ ተከሳሾቹ በአቶ አበባው ደስታ መሪነት በመሰባሰብ መሥራቹን አቶ ዳዊት ብርሃኑን ያለተገቢ ምክንያት እና ሥርዓታዊ ሽግግር ከኃላፊነት ለማስወገድ ሞክረዋል ተብሎ ቀርቧል (የዚህ አለመግባባት መነሻ እዚህ ሊንክ ላይ ተብራርቷል)። እንዲሁም አቶ ሚካኤል አበባው የአቶ አበባው ደስታ ልጅ መሆኑ፣ አቶ ዳንኤል አዳነ ከአቶ መቅደስ ጋር የሥጋ ዝምድና እንዳላቸው እና አቶ አብርሃም ምንውየለት ደግሞ አቶ አበባው ደስታ በስደት ወይም በሕግ ጥላ ሥር ባሉበት ወቅት በአገር ውስጥ እንደ ተወካይ ሆነው እየሠሩ መሆኑ ተጠቅሷል። ከዚህም በተጨማሪ በመሥራቹ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻዎች መከፈታቸውና ኩባንያው ለጉዳት የሚዳርግ አካሄድ ተከትለዋል የሚል ስጋት መፈጠሩ ተመላክቷል።

2.    የመፍትሄ ሐሳቦች እና የፍርድ ቤት መዛግብት

 አቶ ዳዊት ብርሃኑ ባለፉት 16 ዓመታት ጊዜያቸውን፣ ዕውቀታቸውን እና ሀብታቸውን ያፈሰሱበትን ድርጅት ለመታደግ በሰላም የመለያየት አማራጮችን (ድርጅቱን እርሳቸው መግዛት ወይም ለሌሎቹ መሸጥ የመሳሰለ ሃሳብ) ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኘም። በዚህም መሠረት ሁለቱ ወገኖች ተለያይተው ኩባንያው ሀገራዊ ፋይዳውን ጠብቆ እንዲቀጥል በመንግሥት ቁጥጥር ሥር እንዲውል፣ በገለልተኛ አስተዳደር እንዲመራ ወይም ተሸጦ የአክሲዮን ድርሻ እንዲከፋፈል አቶ ዳዊት ጠይቀው ነበር።

በክሱ ላይ መቅረቡ ብቻ ሳይሆን እኔ የዚህ መረጃ አቅራቢ አራቱንም አማራጮች ከላይ የተጠቀሱት ተከሳሾች እንደማይቀበሉ ሲያስታውቁ አውቃለሁ። ግዙ፣ ሽጡ፣ ገለልተኛ አካል ያስተዳድረው ወይም ለሌላ ሦስተኛ ወገን ይሸጥ ሲባል “አንቀበልም” ካሉ፣ ፍላጎታቸው ምን ይሆን? በሚል እንደ ዜጋ እዚህ ጉዳይ ውስጥ ዘው ብዬ እንድገባ መገደዴን እዚህ ላይ ማስታወስ እወዳለሁ።

ወደ ክሱ ማብራሪያ ስንመለስ፣ የመጀመሪያው በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በ3ኛ ንግድ እና ኢንቨስትመንት ችሎት በመዝገብ ቁጥር 25351 ሰኔ 03 ቀን 2018 ዓ.ም. የተመዘገበው የክስ አግባብ፣ ዓላማውም ኩባንያው ተሸጦ የአክሲዮን ድርሻ እንዲከፋፈልና እስከዚያው በመንግሥት ቁጥጥር ወይም በገለልተኛ አስተዳደር እንዲተዳደር ተጠይቋል። ውሳኔ ሳይሰጠው ጉዳዩ በቀጠሮ ላይ ይገኛል።

ሁለተኛው መዝገብ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በ4ኛ ንግድ እና ኢንቨስትመንት ችሎት በቁጥር 26039 የተመዘገበ ሲሆን፣ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት የተሰጠ ሕገ-ወጥ የውክልና ወይም የማረጋገጫ ሰነድ በአስቸኳይ እንዲታገድና እንዲሰረዝ ዳኝነት ተጠይቆበት በቀጠሮ ላይ ይገኛል።

ሦስተኛው መዝገብ ደግሞ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በልደታ ምድብ 6ኛ ንግድ ይግባኝ ሰሚ ችሎት በቁጥር 366871 የቀረበ የይግባኝ አቤቱታ ሲሆን፣ በመዝገብ ቁጥር 25351 አፋጣኝ ጊዜያዊ እግድ ባለመገኘቱ ገለልተኛ አስተዳደር እንዲመራ ተጠይቆ በቀጠሮ ላይ ይገኛል።

ቀደም ብዬ የግል አስተያየቴን ዘርዝሬ፣ በሂደት ዝርዝር የምሄድባቸውን ጉዳዮች ጠቋቁሜ፣ ለግንዛቤ ያህል የፍርድ ሂደቱ ያለበትን ደረጃ በማጋራት ጉዳዩን ይበልጥ ግልጽ ለማድረግ ሞክሬያለሁ። ስለ ፍርድ ሂደቱ ራሴን አቅቤና ጨዋ ለመሆን እየታገልኩ ይህን ካልኩ፣ ለመሆኑ አቶ ዳዊት ብርሃኑ ማን ናቸው? የሚለውንም ማስታወቅ የተነሱትን ጉዳዮች፣ በጉዳዩ ዙሪያ ያሉትን ተዋናዮች ለመረዳት፣ ብሎም ለመመዘን ያግዛልና እነሆኝ!

 3. የአቶ ዳዊት ብርሃኑ ሙያዊ ፕሮፋይል እና የዌብስፕሪክስ አመሠራረት

አቶ ዳዊት ብርሃኑ (CCIE 5602) በቴሌኮሙኒኬሽን እና ኔትዎርኪንግ መስክ የረጅም ጊዜ ልምድ ያላቸው የቴክኖሎጂ መሪ፣ ሥራ ፈጣሪ እና ደራሲ ስለመሆናቸው ግለ ታሪካቸው ይናገራል።

ዌብስፕሪክስ (Websprix): ከ2003 ዓ.ም (እ.ኤ.አ. 2011) ጀምሮ መሥራች እና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው በማገልገል በኢትዮጵያ የብሮድባንድ ኢንተርኔት እና የFTTH መሠረተ ልማት ዝርጋታ ፈር ቀዳጅ ሥራ የሠሩ ባለሙያ ናቸው።

  • ደስታ (Destta, Inc.): በ2018 በአሜሪካ የተቋቋመው የDestta, Inc. ተባባሪ መሥራች እና ሥራ አስኪያጅ ናቸው።
  • ሲስኮ ሲስተምስ (Cisco Systems): ከ1992 እስከ 2008 ዓ.ም (እ.ኤ.አ. 2000–2016) በዓለም አቀፍ የአገልግሎት አቅራቢዎች ቡድን (World Wide Service Provider Practice) የቴክኒክ መሪ ሆነው በIOS XR፣ QoS፣ MPLS፣ BGP እና 5G አርክቴክቸር ዘርፎች ሠርተዋል።
  • ደራሲነት እና አካዳሚክ ልምድ፦ እ.ኤ.አ. በ2009 (2001 ዓ.ም.) በCisco Press የታተመው “IOS XR Fundamentals“ መጽሐፍ ደራሲ፣ ተባባሪ ሲሆኑ፣ ከ1982 እስከ 1988 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ክፍል እና በSISA መምህር (ሌክቸረር) ሆነው አገልግለዋል።

4. የዌብስፕሪክስ ጅማሮ እና የባለድርሻዎች አመጣጥ

አቶ ዳዊት በውጭ አገር ሳሉ ለኢትዮ ቴሌኮም፣ ለINSA እና ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነጻ ሥልጠናዎችን ሲሰጡና ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የኔትወርክ ሥርዓቶችን ሲገነቡ ቆይተዋል። የVISP ፈቃድ ለግል ዘርፍ እንዲከፈት የ5 ዓመት የፖሊሲ ሙግትና ዝግጅት ካደረጉ በኋላ ዌብስፕሪክስ የመጀመሪያውን የVISP ፈቃድ ሲያገኝ በቋሚነት ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ችለዋል።

በምሥረታው ወቅት ዘመዳቸው አቶ ምንውየለት አጥናፉ የቢሮ ቦታና የመነሻ ካፒታል አበርክተዋል፤ በኋላም የአቶ ምንውየለት ልጅ አቶ አብርሃም በ50/50 ድርሻ አባቱን ተክቶ ዌብስፕሪክስን ተቀላቅሏል። አቶ አበባው ደስታ እና አቶ መቅደስ አክሊሉ ደግሞ ኩባንያው ከተመሠረተ ከረጅም ጊዜ በኋላ እና አቶ ምንውየለት ካረፉ በኋላ ባለድርሻ የመሆን ዕድል አግኝተዋል።

በቀጣይ አቶ አበባው እንዴት አክሲዮን ይዘው እንደመጡ ግልጽ እንዲሆን፣ የአቶ አብርሃም እና ቤተሰቦቻቸውን የክስ ፋይል በገደምዳሜ እንደማስቃኝ ከወዲሁ ቃል እገባለሁ። ይህን ሳቀርብ ምን አልባትም ሌሎች ድምጾች አፈራቸውን እያራገፉ አየሩን መያዛቸው አየቀርምና እዛ ያድርሰን።

5. የአቶ ዳዊት ትምህርት እና ማረጋገጫዎች

  • CCIE (ቁጥር 5602)
  • ማስተርስ ዲግሪ (MST) በቴሌኮሙኒኬሽን — የፒትስበርግ ዩኒቨርሲቲ (University of Pittsburgh)፣ አሜሪካ (1987/88 – 1992/93 ዓ.ም.)
  • ማስተርስ ዲግሪ (MEE) በኤሌክትሮኒክስ ኢንጂነሪንግ — የአይንድሆቨን የቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (Eindhoven University of Technology)፣ ኔዘርላንድስ (1982/83 – 1984/85 ዓ.ም./1989-1991)
  • ባችለር ዲግሪ (BSc) በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ — አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ኢትዮጵያ (1977 – 1981 ዓ.ም./1984–1989)

ውድ ተከታታዮች በቀጣይ በገባሁት ቃለ መሠረት አቶ አበባው ደስታ ወደ አክሲዮን የገቡበትና የአቶ ምንውዬለት ቤተሰቦች የፍርድ ቤት ክርክር፣ አባታቸውን የተኩት አቶ አብርሃም ምንውየለት፣ እንዲሁም የአቢሲኒያ ባንክ ቢሮ ውስጥ ስለሚቦካው ምሥጢራት እመሰጥራለሁ።

ኤፍሬም ጓንጉል

Filed Under: Opinions, Politics, Slider Tagged With: Abebaw Desta, abraham minwuyelet, Cisco Systems, Daniel Adane, Dawit Berhanu, Destta, Eindhoven University, IOS XR Fundamentals, Mekdes aklilu, Michael Abebaw, University of Pittsburgh, VISP

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በዌብስፕሪክስ ኃ.የ.ግ.ማ. ባለአክሲዮኖች መካከል የተፈጠረው የሕግ ክርክር እና መሥራቹ አቶ ዳዊት ብርሃኑ November 26, 2026 01:41 pm
  • “ትብብሩ በግል ታይታና በመንደር ሽኩቻ ተተብትቦ [በተለይ ፋኖ] ትግሉን እያራዘመና የሕዝብ ዕዳ እየጨመረ ነው” ስደተኛው ይልቃል November 25, 2026 01:52 pm
  • የዲፕሎማሲ ሽብልቅ ሆኖ አልቡርሃንን አጣብቂኝ ውስጥ የከተተው የጠ/ሚ/ር ዐቢይ የሰላም ጥሪ November 25, 2026 12:07 pm
  • Defected Fano Spokesperson Alleges Orthodox Fano Is Pursuing Ties with Radical Islamist Groups Houthis and Al Shabaab November 24, 2026 06:38 am
  • “ፋኖ እንደ ሁቲ እና አልሸባብ ካሉ ዓለም አቀፍ የሽብር ቡድኖች ጋር ለመሥራት ጥረት እያደረገ ነው” November 23, 2026 10:52 pm
  • በፋኖ ስም ከአማራ ገበሬና ከዳያስፖራ የሚሰበሰበው በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የጥቂት አመራሮች መበልጸጊያ ሆኗል November 20, 2026 08:54 am
  • የቴሌኮም ጌትዌይ፣ የዳታ ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ደህንነት – የዌብስፕሪክስ ጉዳይ ከባለቤትነት ክርክር በላይ ነው! November 17, 2026 11:54 pm
  • “የጫካ ቱጃሮች!”— የፋኖ አመራሮች ስለተሰማሩበት የገንዘብ ዝርፊያ አስደንጋጭ መረጃ November 17, 2026 05:43 pm
  • በየወሩ 4 ሚሊዮን ብር እየተከፈለው ሀገር ሲያፈርስ የነበረው ሪፖርተር November 16, 2026 01:17 am
  • ሻርኮቹ ከውጭ እስከ ሀገር ውስጥ ያደሩት ድር፣ ዌብስፕሪክስን (WebSprix) የመጠቅለሉ ድራማና ብሔራዊ ስጋት November 14, 2026 12:42 am
  • የመለስ ዜናዊን ጭንብል የገፈፈው የትህነግ ሚዲያ (EMF) ምስክርነት November 13, 2026 03:32 pm
  • ትህነግ በወታደራዊና በፖለቲካዊ መስክ እንደሞተ ሁሉ በሪፖርተር በኩል የሚዲያ ግብዓተ መሬቱ ተፈጽሟል November 13, 2026 01:13 am
  • በከባድ ታክስ ማጭበርበር የሚፈለጉት አቶ አበባው ደስታ፣ አማራጭ የቴሌኮም ጌትዌይ ፕሮጀክትን ሊጠቀልሉ ነው November 12, 2026 03:50 am
  • “ፋኖ ወደ ኦሮሚያ ገብቶ ሕዝብ እየገደለ ነው” የኦነግ ሸኔ (OLF/OLA) ተወካይ ጃል ጅረኛ November 10, 2026 05:12 pm
  • ከትህነግ የተማረኩና ከውጭ ሀገራት የገቡ ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎች በቃሊቲ ለእይታ ቀረቡ November 6, 2026 03:36 pm
  • የመንግሥት ኃላፊዎች ወደ ሁርሶ የተወሰዱበት ምሥጢር November 5, 2026 12:43 pm
  • መንግሥት ሰማ፤ ሪፖርተር ተዘጋ፤ ግን ለምን? ምሥጢሩ ምንድነው? November 3, 2026 12:09 am
  • ኢትዮጵያ በሰማይ ላይ ነዳጅ የሚሞሉ የኢሉሺን (Il-78) አውሮፕላኖችን ከሩሲያ ልትገዛ ነው October 30, 2026 08:57 am
  • ካይሮ ያጣችውን የሩሲያ ጄቶች አዲስ አበባ የታጠቀችበት ምሥጢር October 29, 2026 10:26 am
  • ኢትዮጵያ ሱ-35 ተዋጊ ጄቶች እና የኤስ-400 ዘመናዊ የአየር መከላከያ ስርአት በመታጠቅ ከሰሃራ በታች ብቸኛዋ ሀገር ሆናለች October 28, 2026 11:00 am
  • ሻዕቢያ ኢትዮጵያን በ“ካሚካዜ” ድሮኖች ለመምታትና በዘር ግጭት ለማፍረስ ሰፊ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተሰማ October 27, 2026 11:14 pm
  • ጆን መዲድ “ቀዝኖ እና ልብሱ ተበላሽቶ” ነው መከላከያ የማረከው October 27, 2026 08:41 pm
  • በጆን መዲድ መማረክ አደረጃጀቱ እየተፈረካከሰ በመሆኑ እነ ወዲ እምበይተይ፣ ምግበይ፣ ቀጣዮች ሊሆኑ ይችላሉ October 27, 2026 09:17 am
  • ከታክስ ስወራ እስከ ሐሰተኛ ጋብቻ፦ በኢትዮጵያ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊ ዳያስፖራዎችን ለማደን የተዘረጋው አዲሱ የአሜሪካ መረብ October 21, 2026 09:26 am
Copyright © 2026 · Goolgule