በአማራ ክልል በሚንቀሳቀሱ የፋኖ አደረጃጀቶች ውስጥ ከኬላዎች፣ ከነጋዴዎችና ከዳያስፖራው በየወሩ በአስር ሚሊዮኖች እና በዓመት በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ቢሰበሰብም፣ ገንዘቡ ለተዋጊ አባላትና ለቁስለኞች ህክምና ሳይውል የጥቂት አመራሮች የግል ሀብት ማፍሪያ መሆኑን የቀድሞው የፋኖ ከፍተኛ አመራር ማርሸት ፀሐዩ አጋለጠ።
ማርሸት ፀሐዩ በኤንቢሲ (NBC) ቴሌቪዥን ቀርቦ በሰጠው ሰፊ ቃለ መጠይቅ እንደተናገረው፣ ቡድኑ በየአካባቢው ባሉ “ጉልተኛ የጦር አበጋዞችና የጎበዝ አለቆች” የሚመራ በመሆኑ የፋይናንስ ግልጽነትና ተጠያቂነት ፈጽሞ የለም ብሏል።
“ጎንቻ ያለውን ፋይናንስ ጎንቻ ያለው ነው የሚሰበስበው፤ ቆቦ ያለውን ቆቦ ያለው ነው የሚሰበስበው፤ የምንጃሩን ምንጃር ነው የሚሰበስበው። ወደ ላይ ሄዶ ማዕከላዊ ሆኖ ቋት አይሠራለትም፤ ኦዲት አይደረግም፤ ማንም ማንንም ኦዲት አድርጎ አያውቅም” ያለው ማርሸት፣ አንድ ወረዳ ላይ 10 እና 15 አባላት ቆስለው ህክምና ሳያገኙ ባሉበት ተቀምጠው፣ የተሰበሰበው በጀት ግን አመራሩ እጅ ገብቶ እንደፈለገው እንደሚመዘበር አስረድቷል።
በኬላዎች የሚሰበሰበውን ከፍተኛ ገንዘብ በምሳሌነት የጠቀሰው ማርሸት ፀሐዩ፣ “በቀን አንድ ሚሊዮን ብር የሚሰበሰብበት ኬላ አለ። በትንሹ በቀን 500 ሺህ ብር ይሰበሰባል ቢባል እንኳ በወር 15 ሚሊዮን ብር ነው፤ በዓመት ሲባዛ መቶ ምናምን ሚሊዮን ብር ይመጣል። ‘የት ገባ?’ ብለህ ብትጠይቅ ‘እዚህ ገባ’ የሚልህ አንድ አካል የለም፤ ስምጥ [ይግባ እምጥ] አይታወቅም። ለአባሉ ልብስና ጫማ አልተገዛበትም፤ ለቆሰለ አባል የተሻለ ህክምና አልተገኘበትም” ሲል ተናግሯል።
ከዳያስፖራው የሚላከው ገንዘብም በተመሳሳይ መልኩ “በሰፈር ልጆች” እና በግለሰብ አመራሮች ስም እየተሰበሰበ ያለ አንዳች ተጠያቂነት እንደሚባክን ገልጿል። በእስክንድር ነጋ እና በዘመነ ካሴ ደጋፊዎች መካከል የተፈጠረውም ልዩነት የርዕዮተ ዓለም ወይም የማኒፌስቶ ሳይሆን የስልጣን ሽኩቻና የፋይናንስ አቅም ፉክክር መሆኑን አስረድቷል።
በተለይም “የጫካ ቱጃሮች” በማለት የጠራቸው አንዳንድ አመራሮች በትግሉ ስም ከፍተኛ ሀብት ማካበታቸውን በተጨባጭ መረጃ አስደግፎ ሲያጋልጥ እንዲህ ብሏል፦
- በአሜሪካና በሀገር ውስጥ የተከማቸ ሀብት፦ ከጎጃም አመራሮች መካከል የአንዱ ስልክ ተይዞ በተደረገ ፍተሻ፣ በአሜሪካ ሀገር በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ማስቀመጣቸውን የሚያሳይ አስደንጋጭ መረጃ መገኘቱን ገልጿል። እንዲሁም ዶላር በሻንጣ ይዘው የሚዞሩ፣ ባህር ዳርና ሌሎች ከተሞች ላይ በዘመዶቻቸውና በወንድሞቻቸው ስም ቤት የገነቡና ሀብት ያፈሩ መኖራቸውን አረጋግጧል።
- ባለሀብቶችን በማስፈራራት የሚፈጸም ዝርፊያ፦ ለባለሀብቶች የማስፈራሪያ ደብዳቤ በመጻፍ “ካላመጣህ ተሽከርካሪህ በዚህ አያልፍም፤ አንተም አትኖራትም” በማለት ከ20 እስከ 30 ሚሊዮን ብር መቀበላቸውንና በአስፋልት ላይ መኪና አቁመው ባለቤቱን በማገት 2 ሚሊዮን ብር እንደሚጠይቁ ተናግሯል።
- የመሳሪያና የመገናኛ ሬዲዮ ሽያጭ፦ “ከግብጽ በኤርትራ አድርጎ ጎጃም የገባን ጥይት ሽጠውታል። ከአዲስ አበባ እስከ ጎጃም የሚያገናኝ ትልቅ አንቴና ያለው ሀገር አቀፍ የመገናኛ ሬዲዮ መጥቶ፣ ትልቁን ሸጠው ትንንሾችን አከፋፈሉ” ሲል አመራሮቹ ለትግሉ የመጣውን ትጥቅና ሎጂስቲክስ ጭምር መሸጣቸውን ይፋ አድርጓል።
ማርሸት ፀሐዩ ራሱ በቅርቡ በሰጠው መግለጫ ላይ በአሁኑ ወቅት ፋኖ ምንም ዓይነት ሕዝባዊ ዓላማ (Cause) እንደሌለው ማጋለጡ የሚታወስ ሲሆን፣ አመራሮቹ የፋኖን ስም እንደ ሽፋን በመጠቀም ከአማራ ገበሬ በግፍ የሚስብስቡትንና ከዳያስፖራው እየተሰበሰበ የሚላክላቸውን ለግል ጥቅማቸው እያዋሉት እንደሆነ መሬት ላይ ያለው ሐቅ ያሳያል። ሆኖም በዚህ ተጠያቂነት በሌለበት የዝርፊያ መዋቅር ውስጥ በአመራር እርከን ላይ የነበሩት በሙሉ ይብዛም ይነስም ተሳታፊ በመሆናቸው እንደ ጲላጦስ ከደሙ ንጹሕ ነኝ ለማለት የሚደፍር እንደማይኖር የራሱ የማርሸት ምስክርነት ማስረጃ ነው።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Hundreds of Millions Collected in Fano’s Name From Amhara Farmers and the Diaspora Are Enriching a Handful of Leaders
Tens of millions of birr collected monthly, and hundreds of millions annually, from road checkpoints, local merchants, and the diaspora in the name of Fano are being pocketed by a handful of commanders rather than funding fighters or medical care for the wounded, according to former senior Fano leader Marshet Tsehaye.
Speaking in a wide-ranging interview on NBC television, Marshet said the armed factions operating in the Amhara region are controlled by localized warlords and self-styled “strongmen,” leaving the movement completely devoid of financial transparency or accountability.
“The money collected in Goncha stays with the man in Goncha; what is collected in Kobo stays in Kobo; what is collected in Minjar stays in Minjar,” Marshet said. “It never goes up to a central treasury. There are no audits—nobody has ever audited anyone.” Meanwhile, he added, 10 to 15 wounded fighters in a single district are left languishing without medical treatment while local commanders embezzle the funds as they please.
Pointing to highway checkpoints as a major source of unaccounted revenue, Marshet laid out the math. “There is a checkpoint that brings in a million birr a day,” he said. “Even at a conservative estimate of 500,000 birr a day, that is 15 million birr a month—well over a hundred million birr a year. If you ask where it went, nobody can tell you. It vanishes without a trace. Not even clothes or shoes were bought for the fighters, nor was proper medical care provided for the wounded.”
Funds sent from supporters abroad follow the same opaque path, channeled through neighborhood cliques and individual commanders with zero oversight. Marshet also dismissed the bitter rift between factions loyal to Eskinder Nega and Zemene Kasse as purely a struggle over power and money rather than ideology or a political manifesto.
Describing a rising class of what he called “bush tycoons” (ye-chaka tujaroch), Marshet cited specific allegations of illicit enrichment among commanders:
- Millions Stashed Abroad and Property at Home: According to Marshet, a phone seized from a Gojjam-based commander revealed startling evidence that millions of dollars had been deposited in the United States. Other commanders, he alleged, travel with suitcases full of U.S. dollars and have built homes and acquired properties in Bahir Dar and other cities registered under the names of brothers and relatives.
- Extortion of Business Owners: Commanders allegedly send threatening letters to local investors demanding 20 to 30 million birr, warning them that neither their vehicles nor their lives will be safe on the roads if they fail to pay. On highways, drivers are routinely stopped and held for ransoms of up to 2 million birr.
- Selling Weapons and Communications Gear: “Ammunition that entered Gojjam from Egypt via Eritrea was sold off,” Marshet revealed. “A high-powered national communications radio with a massive antenna capable of linking Addis Ababa to Gojjam arrived, and they sold the main unit while distributing only the small handheld sets.”
Marshet himself recently acknowledged in a separate interview that Fano no longer possesses a genuine public cause, and realities on the ground indicate that commanders are using the Fano banner largely as a cover to extort Amhara farmers and divert diaspora donations into private fortunes. Yet within an unaccountable system rife with looting, virtually everyone who has held a leadership rank bears some degree of complicity, leaving none in a position to wash their hands like Pilate and claim innocence, a reality underscored by Marshet’s own testimony.
Golgul Online Newspaper

Leave a Reply