• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ፋኖ እንደ ሁቲ እና አልሸባብ ካሉ ዓለም አቀፍ የሽብር ቡድኖች ጋር ለመሥራት ጥረት እያደረገ ነው”

November 23, 2026 10:52 pm by Editor Leave a Comment

በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ የፋኖ አመራሮች ፖለቲካዊ ዓላማቸውን ለማሳካት በቀይ ባህር ዳርቻና በቀጠናው ካሉ እንደ ሁቲ እና አልሸባብ ካሉ ዓለም አቀፍ የሽብር ቡድኖች ጋር ለመሥራት ፍላጎት እንዳላቸውና ጥረትም እያደረጉ መሆኑን የቀድሞው የፋኖ ከፍተኛ አመራር ማርሸት ፀሐዩ ገለጸ።

ማርሸት ፀሐዩ በኤንቢሲ (NBC) ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርቦ በሰጠው ቃለ መጠይቅ እንደተናገረው፣ ጉዳዩ መላውን የፋኖ አባላትና አመራሮች ባይወክልም፣ “በስልጣን ጥም የሰከሩ” ያላቸው ጥቂት የቡድኑ አመራሮች ግን ከዓለም አቀፍ አሸባሪ ኃይሎች ጋር በመተባበር ሽብርተኝነትን ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባትና ሀገር ለማተራመስ ወደኋላ የማይሉ ናቸው ብሏል።

“ዛሬ እያደረጉ ያሉት ዘረፋ እና የአፈና ተግባር የፈለጉት ዓላማ ላይ ካላደረሳቸው፣ የትም ዓለም ካለ የሽብር ቡድን ጋር ተገናኝተው—ልክ ትላንት ከትህነግ እና ከሻዕቢያ ጋር እንደተገናኙት—ነገ ከነገ ወዲያ ደግሞ ከሌላ አህጉርና ከሌላ ዓለም ካለ የሽብር ቡድን ጋር ተገናኝተው ሽብርተኝነትን ወደ ኢትዮጵያ ጎትተው በማስገባት በህዝባችንና በሀገራችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያመጡ ይችላሉ” ሲል አስጠንቅቋል።

ጉዳዩ በቸልታ ሊታይ እንደማይገባው አጽንኦት የሰጠው ማርሸት ፀሐዩ፣ ስለ ሁቲ ታጣቂ ቡድን ያለውን መረጃ እንዲህ ሲል አብራርቷል፦ “ይህ እንደ ቀልድ ሊታይ የሚገባ ጉዳይ አይደለም፤ ፍላጎትም አለ ጥረትም እያደረጉ ነው። በተጨባጭ እኔ የማውቀው፣ አሁን ሁቲ ቢያገኛቸውና ቢያናግራቸው—እንደሚታወቀው ሁቲ ከፍተኛ ቢሊዮን ዶላር አለው፣ መሳሪያም አለው—አይናቸውን አያሹም፤ ከሁቲ ጋር ተገናኝተው ሁቲን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት ሀገሪቱን ለማተራመስ ወደኋላ አይሉም።”

አክሎም ቀደም ሲል ከትህነግና ከሻዕቢያ ጋር በመተባበር ስልጣን ለመያዝ የነበራቸው እቅድ መክሸፉ ለዚህ አዲስ አደገኛ አካሄድ እንደዳረጋቸው ሲገልጽ፣ “በትህነግ እና በሻዕቢያ በኩል ጋልቦ ስልጣን ለመቆናጠጥ ከፍተኛ ፍላጎትና ጉጉት የነበራቸው ግለሰቦች፣ የትህነግ መመታት ቀድሞውኑ ቅስማቸውን ስብር አድርጎታል። የመጣባቸው የፖለቲካ ኪሳራና የተንኮላሸ እቅዳቸው ሌላ ቀውስ ውስጥ ስላስገባቸው፣ እንደ ሁቲ እና እንደ አልሸባብ ካሉ ኃይሎች ጋር ለመተባበር ቢሆን አያመነቱም” ብሏል።

በሌላ በኩል ማርሸት ፀሐዩ በክልሉ ውስጥ በነጋዴዎችና በህዝቡ ላይ እየደረሰ ያለውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ አንስቷል። ከባህር ዳር ጀምሮ እስከ ሜጫና ደምበጫ ድረስ የሚንቀሳቀሱ ነጋዴዎችና ባለንብረቶች ተሽከርካሪዎቻቸው በአስፋልት ላይ እየተያዙ “አንድ ሚሊዮን፣ ሁለት ሚሊዮን ብር አምጡ” እየተባሉ ለከፍተኛ ዘረፋና እገታ መዳረጋቸውን አስረድቷል። በዚህም ምክንያት በርካታ ነጋዴዎች የባንክ እዳቸውን መክፈል አቅቷቸው ለኪሳራ መዳረጋቸውን፣ ቤተሰቦች እየተበተኑ መሆናቸውንና ዜጎች ቀያቸውን ጥለው ወደ አዲስ አበባ ለመሰደድ መገደዳቸውን ተናግሯል።

“ዛሬ የባንክ እዳ ላለበት ምስኪን የአማራ ነጋዴ ያልራራ አካል፣ ነገ ከማንም የሽብር ቡድን ጋር ተገናኝቶ ሀገር ለማፍረስ ምንም ዓይነት ርህራሄ እንደማይኖረው ግልጽ ነው” በማለት ሁኔታው አደገኛ አዝማሚያ ላይ መሆኑን ገልጿል።

በመጨረሻም ማርሸት ፀሐዩ ይህ ችግር “የእንቁላሉ ጊዜ በቀን ሳለ” (ስር ሳይሰድ) እና የከፋ የሀገር ስጋት ከመሆኑ በፊት፣ መንግሥት ልበ ሰፊ በመሆን ፈጣን የፖለቲካ ማዕቀፍና መፍትሄ አበጅቶ ጉዳዩን በጊዜ መቋጨት እንዳለበት አሳስቧል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: News, Slider Tagged With: al-shabaab, Amhara Fano, ethiopian terrorists, Fano, houthi, masresha, operation dismantle tplf, tplf terrorist

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • “ፋኖ እንደ ሁቲ እና አልሸባብ ካሉ ዓለም አቀፍ የሽብር ቡድኖች ጋር ለመሥራት ጥረት እያደረገ ነው” November 23, 2026 10:52 pm
  • በፋኖ ስም ከአማራ ገበሬና ከዳያስፖራ የሚሰበሰበው በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የጥቂት አመራሮች መበልጸጊያ ሆኗል November 20, 2026 08:54 am
  • የቴሌኮም ጌትዌይ፣ የዳታ ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ደህንነት – የዌብስፕሪክስ ጉዳይ ከባለቤትነት ክርክር በላይ ነው! November 17, 2026 11:54 pm
  • “የጫካ ቱጃሮች!”— የፋኖ አመራሮች ስለተሰማሩበት የገንዘብ ዝርፊያ አስደንጋጭ መረጃ November 17, 2026 05:43 pm
  • በየወሩ 4 ሚሊዮን ብር እየተከፈለው ሀገር ሲያፈርስ የነበረው ሪፖርተር November 16, 2026 01:17 am
  • ሻርኮቹ ከውጭ እስከ ሀገር ውስጥ ያደሩት ድር፣ ዌብስፕሪክስን (WebSprix) የመጠቅለሉ ድራማና ብሔራዊ ስጋት November 14, 2026 12:42 am
  • የመለስ ዜናዊን ጭንብል የገፈፈው የትህነግ ሚዲያ (EMF) ምስክርነት November 13, 2026 03:32 pm
  • ትህነግ በወታደራዊና በፖለቲካዊ መስክ እንደሞተ ሁሉ በሪፖርተር በኩል የሚዲያ ግብዓተ መሬቱ ተፈጽሟል November 13, 2026 01:13 am
  • በከባድ ታክስ ማጭበርበር የሚፈለጉት አቶ አበባው ደስታ፣ አማራጭ የቴሌኮም ጌትዌይ ፕሮጀክትን ሊጠቀልሉ ነው November 12, 2026 03:50 am
  • “ፋኖ ወደ ኦሮሚያ ገብቶ ሕዝብ እየገደለ ነው” የኦነግ ሸኔ (OLF/OLA) ተወካይ ጃል ጅረኛ November 10, 2026 05:12 pm
  • ከትህነግ የተማረኩና ከውጭ ሀገራት የገቡ ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎች በቃሊቲ ለእይታ ቀረቡ November 6, 2026 03:36 pm
  • የመንግሥት ኃላፊዎች ወደ ሁርሶ የተወሰዱበት ምሥጢር November 5, 2026 12:43 pm
  • መንግሥት ሰማ፤ ሪፖርተር ተዘጋ፤ ግን ለምን? ምሥጢሩ ምንድነው? November 3, 2026 12:09 am
  • ኢትዮጵያ በሰማይ ላይ ነዳጅ የሚሞሉ የኢሉሺን (Il-78) አውሮፕላኖችን ከሩሲያ ልትገዛ ነው October 30, 2026 08:57 am
  • ካይሮ ያጣችውን የሩሲያ ጄቶች አዲስ አበባ የታጠቀችበት ምሥጢር October 29, 2026 10:26 am
  • ኢትዮጵያ ሱ-35 ተዋጊ ጄቶች እና የኤስ-400 ዘመናዊ የአየር መከላከያ ስርአት በመታጠቅ ከሰሃራ በታች ብቸኛዋ ሀገር ሆናለች October 28, 2026 11:00 am
  • ሻዕቢያ ኢትዮጵያን በ“ካሚካዜ” ድሮኖች ለመምታትና በዘር ግጭት ለማፍረስ ሰፊ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተሰማ October 27, 2026 11:14 pm
  • ጆን መዲድ “ቀዝኖ እና ልብሱ ተበላሽቶ” ነው መከላከያ የማረከው October 27, 2026 08:41 pm
  • በጆን መዲድ መማረክ አደረጃጀቱ እየተፈረካከሰ በመሆኑ እነ ወዲ እምበይተይ፣ ምግበይ፣ ቀጣዮች ሊሆኑ ይችላሉ October 27, 2026 09:17 am
  • ከታክስ ስወራ እስከ ሐሰተኛ ጋብቻ፦ በኢትዮጵያ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊ ዳያስፖራዎችን ለማደን የተዘረጋው አዲሱ የአሜሪካ መረብ October 21, 2026 09:26 am
  • ኔታንያሁ የሶማሊላንድን ሉዓላዊነት ያረጋገጠ አዲስ ቀጣናዊ ካርታ ይፋ አደረጉ October 20, 2026 03:20 pm
  • ትውልደ ሶማሊያዊቷ ናፊሳ በተዘቀዘቀ የአሜሪካ ሠንደቅ ፊት በሶማሊኛ ምርጫ ቅስቀሳ ማድረጓ ቁጣ ቀሰቀሰ October 20, 2026 09:21 am
  • በአሜሪካ የሚገኙ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊዎች ላይ የተደቀነው አዲስ ስጋት October 19, 2026 08:58 pm
  • ዜግነት ሊያሰርዝ በሚችለው የኢልሃን ዑመር ምርመራ ላይ አዳዲስ መረጃ ተገኝቷል October 19, 2026 04:45 pm
Copyright © 2026 · Goolgule