በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ቡድኖችን (ትህነግ፣ ፋኖ፣ ኦነግ-ኦነሠ እና ሌሎችንም) በገንዘብ፣ በማኅበራዊ ሚዲያና በተለያዩ መንገዶች የሚደግፉ የዲያስፖራ አባላት ላይ ከባድ የሕግና የኢሚግሬሽን ስጋት መደቀኑን የጎልጉል ምንጮች አስጠነቀቁ። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በቅርቡ በሰጡት መግለጫ፣ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ የጦር መሣሪያ ያነሱትንና በቅርቡ ጥምረት የፈጠሩትን የታጠቁ ቡድኖች እንቅስቃሴ “የመገንጠል እና የሽብርተኝነት” ተግባር ሲሉ ፈርጀውታል። ይህንን ተከትሎ ዋሽንግተን ለእነዚህ ቡድኖች የገንዘብና የፕሮፓጋንዳ ድጋፍ የሚያደርጉ የዲያስፖራ አባላትን መከታተልና መመርመር ወደሚችልበት ቀጣይ እርምጃ ልትሸጋገር እንደምትችል ተጠቁሟል። በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ የሚገኙ ምንጭ ለጎልጉል እንደገለጹት፣ በአሁኑ ወቅት የአሜሪካ መንግሥት … [Read more...] about ከታክስ ስወራ እስከ ሐሰተኛ ጋብቻ፦ በኢትዮጵያ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊ ዳያስፖራዎችን ለማደን የተዘረጋው አዲሱ የአሜሪካ መረብ
Denaturalization
በአሜሪካ የሚገኙ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊዎች ላይ የተደቀነው አዲስ ስጋት
* ውሳኔው ከዜግነት መነጠቅ እስከ ከአገር ማባረር ይደርሳል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፣ በ“ሽብርተኝነት እና በመገንጠል” ተግባር ላይ የተሰማሩ ትህነግ፣ ኦነግ ሸኔ፣ ፋኖ እና ሌሎችንም ያካተተውን የትብብር ለሕልውና ታጣቂ ቡድኖች ስብስብ አስመልክቶ ካስተላለፉት ጠንከር ያለ መልእክት በመቀጠል፣ ዋሽንግተን እነዚህን ቡድኖች በሚደግፉ አካላት ላይ የማያወላዳ እርምጃ መውሰድ እንደምትጀምር ጎልጉል ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ያገኘው መረጃ አመለከተ። በአሁኑ ወቅት የአሜሪካ መንግሥት ሕገወጥ ስደተኞችን ከማጽዳት ባለፈ፣ በማንኛውም ሕገወጥ እንቅስቃሴ ላይ የሚገኙና በመወለድ ሳይሆን በመሃላ (naturalized citizenship) ዜግነት ያላቸውን ጭምር ዜግነታቸውን በመሰረዝ ከአገር እስከማባረር የሚደርስ ከባድ አካሄድ ላይ እንዳለ የሚታወቅ ነው። ይህ አዲስ አካሄድ … [Read more...] about በአሜሪካ የሚገኙ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊዎች ላይ የተደቀነው አዲስ ስጋት


