የአገራችን “ሃብታሞች” ወግ ከፍቶ ውስጡን ላየው ያስደነግጣል። “ገንዘብ ባለበት ሁሉ ጩኸት አለ” የሚለው አባባል በተለይ በኢትዮጵያ እውነት እንደሆነ ማረጋገጫም ነው። ጎልጉል ባገኘው መረጃ መሠረት የኢትዮጵያን የንግድ ሥርዓት ሲጋልቡ የነበሩ አካላት፣ አሁን ላይ “ይህ ለምን ቀረብን?” ወይም “ገና ለገና ሊቀርብን ነው” በሚል ሥጋት አንድ ላይ አገር እየናጡ ነው። ከዚህ ቀደም “የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አእምሮና የደም ዝውውር ሊኖረው ነው” በሚል ርዕስ ስለ አዲሱ ማክሮ ኢኮኖሚክ ፖሊሲ ስንዘግብ ውሳኔው “በኢትዮጵያ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ሳይሆን አዲስ መጽሐፍ ነው፤ ከዚህ በኋላ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አእምሮና የደም ዝውውር ሊኖረው ነው፤ ከዚህ አኳያ ፖሊሲው እንከን የማይወጣለት ነው” በሚል አቶ ኤርሚያስ አመልጋን ጠቅሰን እንደነበር ይታወሳል። ይህን ዘገባ ተከትሎ የአዲስ አበባ … [Read more...] about ኢትዮጵያ የሚያልቧት እንደዚህ ነው፤ “ገንዘብ ባለበት ጩኸት አለ”