የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴር (ፔንታጎን) በፎርት ሁድ ቴክሳስ ወታደራዊ ጣቢያ 13 ሰዎችን በመግደል እና 32 ሰዎችን በማቁሰል ጥፋተኛ የተባለው የቀድሞው የጦር ሠራዊት የሥነ-አእምሮ ሐኪም ሻለቃ ኒዳል ሀሰን የሞት ፍርድ በርሸና (Firing squad) ሲፈጸምበት በቀጥታ በቪዲዮ ሥርጭት (Livestream) ለሕዝብ እንዲታይ መወሰኑን አስታውቋል። ኒዳል ሀሰን ይህንን አሰቃቂ ጥቃት የፈጸመው በጥቅምት 26 ቀን 2002 ዓ.ም. (በአውሮጳውያኑ አቆጣጠር ህዳር 5 ቀን 2009) ሲሆን፣ ጥቃቱን ያደረሰበት ዋና ምክንያት የአሜሪካ ጦር በኢራቅ እና በአፍጋኒስታን የሚያደርገውን ወታደራዊ ዘመቻ በመቃወም እና በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ የሚደረግ ውጊያ አድርጎ በመመልከቱ እንደነበር በፍርድ ሂደት ወቅት ተገልጿል። ይህ የፔንታጎን ውሳኔ በአሜሪካ የፖለቲካ እና የሕግ ባለሙያዎች … [Read more...] about የኒዳል ሀሰን በርሸና የሞት ፍርድ ሲፈጸምበት በቀጥታ ሥርጭት እንዲተላለፍ መወሰኑ ውዝግብ አስነሳ

