ከ27 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በጠቅላይ ሚኒስትር የስብሰባ አዳራሽ የተገኙት ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም፤ ዶ/ር ዐቢይ የዕለቱን የመወያያ አጀንዳ ከገለጹ በኋላ እና የስብሰባው ተሳታፊዎች አሳባቸው እየገለፁ ባሉበት ወቅት ነው፤ የኔታ ወደ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ የገቡት። ዶ/ር ዐቢይን ጨምሮ በአዳራሽ ውስጥ የነበሩ ተሰብሳቢዎች የኔታ የመቀመጫ ወንበራቸውን እስኪይዙ ድረስ የተሰብሳቢው ዓይን በፍቅርና በአክብሮት እሳቸው ላይ ነበር ያረፈው። የተጀመረው ውይይት በተሰብሳቢዎች በሚነሱ ጥያቄዎችና አስተያየት ቀጥሎ ለሻይ ዕረፍት ስብሰባው ተቋረጠ። ሁላችንም ሻይ እና ቡና ወደተዘጋጀበት ቦታ አመራን፤ ዶ/ር ዐቢይ ለሻይ በወጣንበት ወቅት የቱ ጋር እንዳሉ እኔ ልብ አላልኩም፤ ይልቁንም ለየኔታ ትኩስ ነገር ምን ላምጣሎት ብዬ ስጠይቃቸው፤ “አንድ ሲኒ ቡና ትንሽ ስኳር ጨምረ አመጣልኝ፣ ከዚያ … [Read more...] about የኔታ እና ዶ/ር ዐቢይ፤ የኔታ ምን አሉ?!
abiy ahmed
አብዲ ኢሌይ “ከተጠያቂነት አያመልጥም” – ፊሊክስ ሆርን
ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት (ሂውማን ራይትስ ዎች) በቅርቡ በሶማሊ ክልል ስለሚፈጸመው እጅግ አሰቃቂ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች አዲስ ዘገባ ማውጣቱ ይታወቃል። የክልሉ ርዕስ መስተዳድር የሆነውን አብዲ ኢሌይን በቀጥታ ተጠያቂ የሚያደርገው ይህ ዘገባ ከወጣ በኋላ አብዲ የተለያዩ “ዕርምጃዎችን” ሲወስድ ተስተውሏል።እነዚህም “ዕርምጃዎች” እስረኞችን ሁሉ መፍታት፣ በክልሉ የሚፈጸመውን ስቅየት ማቆም፣ … ያካተቱ ናቸው ቢባልላቸውም ለምሳሌ በኦጋዴን እስርቤት የነበሩትን የመፍታት ሳይሆን ወደ ሌላ ቦታ የማዛወር ተግባር ነው የተፈጸመው በማለት “ዕርምጃዎቹን” ውድቅ የሚያደርጉ ጥቂቶች አይደሉም። ከዚህ ሌላ አብዲ ኢሌይ በክልል ምክርቤቱ ስብሰባ ላይ እስካሁን በክልሉ ለተፈጸሙት ወንጀሎች ህወሓትን በቀጥታ ተጠያቂ ሲያደርግ መስማታቸውን የክልሉ አክቲቪስቶች አረጋግጠዋል። … [Read more...] about አብዲ ኢሌይ “ከተጠያቂነት አያመልጥም” – ፊሊክስ ሆርን
ሕዝብ ከስሜትና ከተራ ብሽሽቅ በመራቅ በያለበት የአገሩ ዘበኛ ይሁን!
ቀደም ሲል በሃዋሳ፣ ባለፈው ቅዳሜ በመስቀል አደባባይ በተቀነባበረ ሁኔታ የደረሰውን የቦንብ ፍንዳታ፣ በቤኒሻንጉል በተለያዩ ቦታዎችና በተለይም በአሶሳ የደረሰንና እየደረሰ ያለውን የዘር ማጥራት ጭፍጨፋ፣ ሕዝብ ወደ ምሬት እንዲሄድ ሆን ተብሎ የሚደረግ የኢኮኖሚ አሻጥር፣ በጥሞና ለምትከታተሉ ሁሉ፤ በባህር ዳር ለጠቅከላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ ቀና ተግባርና የለውጥ ሩጫ እውቅና ለመስጠት የተጠራውን ሰልፍ ለማወክ ከወዲሁ ቦንብ ሲያዘዋውሩ መያዛቸውን ለሰማችሁ፣ የደኅንነት ኃይሉን ትብትብ በወጉ ለምትረዱና ለምትገነዘቡ፤ በተለያዩ የአገሪቱ የልማት ተቋማት ላይ የሚፈጸመውን የኢኮኖሚ አሻጥር በውል ለምትከታተሉ፤ ህዝብን ከህዝብ ጋር ለማጋጨት የሚሸረቡ ተንኮሎችን ለምታጤኑ፤ ለውጡ እንዲኮላሽና አገሪቱ ወደ ትርምስ ውስጥ እንድትገባ በተሸናፊነት ውስጥ ሆነው ለጥፋት የሚመደበውን በጀት ለምትሰሙ … [Read more...] about ሕዝብ ከስሜትና ከተራ ብሽሽቅ በመራቅ በያለበት የአገሩ ዘበኛ ይሁን!
በአዲስ አበባ፣ አውሮፓና አሜሪካ ለ“ዘመቻ ዓቢይ” የስውር ምልመላ ተጀምሯል!
ኃይሌ ገብረሥላሴ መልማይ መሆኑ ታወቀ የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በዳላስ ሊያካሂድ ያሰበው ሰላሳ አምስተኛ የስፖርት ፌስቲቫል ከወዲሁ እጅግ ጥንቃቄ በሚያሻው ጉዳይ ተወጥሯል። የጎልጉል የመረጃ አቀባዮች እንዳሉት በአገር ውስጥ፣ በአሜሪካና በአውሮፓ የሕዝብ ግንኙነት የሚሠሩ ክፍሎች በምሥጢር እየተመለመሉ ነው። ኃይሌ ገብረሥላሴ አገር ውስጥ ሆኖ ይህንኑ የምልመላ ሥራ እየሠራ ነው። አነጋጋሪ የሆነው ይህንን ዘመቻ የሚያከናውኑት ክፍሎች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ እውቅና ይኑራቸው አይኑራቸው አለመታወቁ ነው። ወደ ሥልጣን ከመጡ ጀምሮ በፖሊሲ ጉዳዮች፣ ሕዝብ ባነሳቸው መሠረታዊ ጥያቄዎች፣ አፋኝ ህጎችን ከማንሳት አኳያ፣ የፖለቲካ እስረኞችን ሙሉ በሙሉ ከመፍታትና የአስቸኳይ አዋጁን በማንሳት፣ ቀጣዩ ምርጫ ነጻና ገለልተኛ እንዲሆን ምርጫ ቦርድን ከማፍረስ ጀምሮ … [Read more...] about በአዲስ አበባ፣ አውሮፓና አሜሪካ ለ“ዘመቻ ዓቢይ” የስውር ምልመላ ተጀምሯል!
ፌዴሬሽኑ (ESFNA) የጠ/ሚ/ሩን ጥሪ ሊያጸድቅ ነው
የኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ (ESFNA) በዚህ ዓመት ሰኔ ወር መጨረሻ በዳላስ ከተማ በሚያደርገው 35ኛው የስፖርትና የባህል በዓል ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ ንግግር እንዲያደርጉ የቀረበለትን ጥሪ ሊያጸድቅ ነው። ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች ፌዴሬሽኑ ለጠ/ሚ/ሩ ስምና የገንዘብ መጠን ያልተጻፈበት ባዶ ቼክ ፈርሞ መስጠት የለበትም፤ ውሳኔው “አደገኛ ነው” ብለውታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ወደ ሥልጣን መንበሩ ከመጡ ወዲህ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታዩ ለውጦች መኖራቸውን ብዙዎች የሚስማሙበት እውነታ ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ በአገር ውስጥ እየተጀመረ ያለው የመግባባት መንፈስ ተደጋፊነት ያለውና መጎልበትም የሚገባውም ነው። በተመሳሳይ በዳያስፖራው ዘንድም እንዲሁ። ሆኖም ጠቅላዩ ሥልጣን ከያዙ ጀምሮ በዴሞክራሲያዊ አሠራሮች ላይ ይህ ነው የሚባል ለውጥ … [Read more...] about ፌዴሬሽኑ (ESFNA) የጠ/ሚ/ሩን ጥሪ ሊያጸድቅ ነው
ህወሓት እስክንድርን ከአገር እንዳይወጣ በመከልከል ባላሰበው ማነቆ ውስጥ ገባ
በኔዘርላንድ በሚደረግ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል 50ኛ ዓመት ክብረበዓል ላይ ለመገኘት ተጋብዞ የነበረው እስክንድር ነጋ ሐሙስ ሌሊት ለአርብ ጠዋት ቦሌ ላይ ከአገር እንዳወጣ ታግቷል። ጎልጉል ባገኘው መረጃ መሠረት ጉዳዩ ህወሓትን ትልቅ ቅርቃር ውስጥ ከቶታል። ጉዳዩን በቅርብ ሲከታተሉ የነበሩት የመብት ተሟጋቹ አቶ ኦባንግ ሜቶ በፌስቡክ ገጻቸው እንደገለጹት ይህ ፈጽሞ መከሰት ያልነበረበት ጉዳይ መሆኑን በመጥቀስ ጠ/ሚ/ር አብይ በጉዳዩ ላይ ፈጣን ምላሽ እንዲሰጡበት ጠይቀዋል። ሌላው ለጉዳዩ ቅርበት ያለውና ክስተቱ እንደተፈጸመ አጭር ዘገባ ያሰራጨው ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ “ከሌሊቱ 8 ሰዓት ቦሌ ያሉ የደህንነት አካላት ፓስፖርቱን ቀምተው አትሄድም ብለውታል። የከለከሉበትን ምክንያቱን ግን አልገለጹም” ብሏል። ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ከቦሌ አካባቢ ባገኘው መረጃ መሠረት እስክንድርን … [Read more...] about ህወሓት እስክንድርን ከአገር እንዳይወጣ በመከልከል ባላሰበው ማነቆ ውስጥ ገባ
A charismatic young leader tries to calm ethnic tension in Ethiopia
"The price of power may have been private assurances that aspects of the security establishment would be left untouched" Intelligence Expert at Georgetown University. IN ITS three decades of existence, the ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) has gone through only two leaders. Neither came to power through a competitive vote. So it was with a sense of novelty that Ethiopians awaited the outcome of a secret ballot held on March 27th to determine the new chairman of … [Read more...] about A charismatic young leader tries to calm ethnic tension in Ethiopia