ይህ ድምፅ የምዕራባውያኑ የመጨረሻው ድምፅ ነው። ወስነዋል። የመጨረሻውን ጫና ጀምረዋል። ጫናው እየጨመረ ይሄዳል። ለምን በአዲስ መልክ ጫናውን ጀመሩ ብንል ተስፋ አድርገውት የነበረው የተመድ የፀጥታው ም/ቤት እነሱ እንደሚፈልጉት ባለመወሰኑ ይመስላል። በክፍል 3 የመጨረሻ ካርዶችን እንይ:-
1ኛ) የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን ዶክተር አብይ ጋር ደውሎ ነበር። በትግራይ ረሃብ ሊከሰት ስለሚችል ያሳስበኛል። በሃገሪቱ ያለው የብሄር ውጥረቶችም ያሳስበኛል። የኤርትራ ጦር ይውጣ። ሁሉም አካላት ጦርነት አቁመው ወደ ድርድር መምጣት አለባቸው። ወዘተ የሚል ውይይት አድርጓል። የዚህ ስልክ አላማ በአጭሩ ከሞተው ጁንታ ጋር “ድርድር እና እርቅ” አድርግ የሚል ነው። ካልሆነ ግን (የብሄር ውጥረቶች ያልኩህ ሌላ መልክ እንዲይዙ እናደርጋለን። እርስበርስ ትፋጃላችሁ። ከዚያም አልቻልክም ተብለህ ከስልጣንህ እናስወግድሃለን…) ዓይነት የሚመስል ቂም ያዘለ መልዕክት ነው። ይህን የምትረዱት ቀጣይ ነጥቦች ጋር ስታያይዙት ነው። ተከተሉኝ። የሚገርመው ካናዳም ተመሳሳይ የድርድር እና የእርቅ ፍላጎቷን ትላንት በኤምባሲዋ በኩል ለመጀመሪያ ጊዜ ገልፃለች።
2ኛ) ባለፈው ሳምንት የአውሮፓ ህብረቱ ጆሴፍ ቦሬል “ከምርጫው በፊት ዶክተር አብይ ብሄራዊ ድርድር (ዲያሎግ) ሊያደርግ ይገባል” ሲል በድፍረት ተናግሯል። ምርጫውን ትቶ ድርድር ካላደረገና በኢትዮጵያ ያለው ግጭት ካልቀነሰ ግን የምርጫ ታዛቢ አንልክም ብሏል። ግጭት የሚለውን አስምሩበት። ቦሬል አክሎም ከብሊንከን ጋር በስልክ እንዳወራና “በኢትዮጵያ ላይ አዲስ የዲፕሎማቲክ ጫና መፍጠር አለብን” በሚል እንደተስማሙ ገልጿል። ስለዚህ ኢትዮጵያን በአዲስ መልኩ የሚወጥሩበት ጊዜው አሁን ነው። ፍላጎታቸው ግልፅ ነው። እርዳታ የሰጡንና ብድር የፈቀዱልን ይህን የመጨረሻ ጫና ለማስከተል መሆኑን መረዳት አያዳግትም። መንግስት ይህን ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ደስተኛ ነኝ። skeptical (ተጠራጣሪ) ሆኖ እያያቸው ይመስለኛል።
3ኛ) የእንግሊዙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶሚኒክ ራብ ከሶስት ቀናት በፊት “ድርድር እንዲካሄድ pressure (ጫና) እንፈጥራለን: ግፊት እናደርጋለን” የሚል አቋሙን ገልጿል። የG7 ሃገራትም ተመሳሳይ አቋም እንዳላቸው አስታውቋል። የሚገርመው እንግሊዝ: EU እና አሜሪካ … ሁሉም ብቻ የኤርትራ ጦር ይውጣ ብለዋል። ይህን የሚሉበት ዋነኛ ምክንያት የጁንታው ትራፊዎች እና ደጋፊዎቹ “የኤርትራ ጦር ከወጣ የኢትዮጵያን ሰራዊት እናሸንፈዋለን” የሚል ከንቱ ምኞት ስለነገሯቸው ይህ ቀቢፀ ተስፋ እውን እንዲሆን በሚል ነው። የሰብዓዊ መብት ጉዳይ እነሱን የሚያሳስብ ሆኖ አይደለም!!!
4ኛ) ከሶስት ቀናት በፊት ቴድሮስ ከኒውዬርክ ታይምስ ጋር ቃለምልልስ አደርጏል። ቴድሮስ እስከዛሬ የዘመተብንና ያስዘመተብን አልበቃ ብሎት ጭራሽ እያለቀሰ ቃለመጠይቅ አደረገ። ኢትዮጵያን ለማፍረስ እና ጁንታውን ለማትረፍ እስከዛሬ የቻለውን ሁሉ ተሸፋፍኖ ቢያደርግም ስላስልተሳካለት ተስፋ በመቁረጡ በግልፅ አወጣው። ከምዕራባዊያኑ ጋር ተነጋግሮ አሁን ላሰቡት አዲስ ጫና ግብዓት ለመሆን በሚል ይመስላል ስቅስቅ ብሎ እያለቀሰ ኢንተርቪው ያደረገው። ከዚያም በገንዘብ የተገዙ ታዋቂ ጋዜጠኞች: ሚዲያዎች: የትላልቅ ድርጅት ሃላፊዎች ወዘተ የሱን ለቅሶ እስከትላንት ድረስ አራገቡት። ከ110 ሚሊዮን ህዝብ ይልቅ ለአንድ ሰው አስበው ሳይሆን ከነሱ ፍላጎት ጋር የተስማማ በመሆኑ ነው። MSF (ድንበር የለሽ ሐኪሞች) እና ዩኒሴፍም ከቴድሮስ ኢንተርቪው አንድ ቀን ቀደም ብለው ኢትዮጵያን የሚከስ ሪፖርት አቀረቡ። ይህ ሁሉ ተደማምሮ ጫናው በአዲስ መልክ ቀጥሏል።
5ኛ) አሜሪካ ለምስራቅ አፍሪካ ልዩ ዲፕሎማት መሾሟን አርብ አስታውቃለች። በቅርቡ ኢትዮጵያ እንደሚገባም ታውቋል። ጀፍሪ ዴቪድ ፌልትማን ይባላል። ጡረተኛው ዲፕሎማት ተመድን ጨምሮ በብዙ ሃገራት የአሜሪካ ዲፕሎማት በመሆን ከ 26 አመታት በላይ ሰርቷል። መለስ ዜናዊ ሲሞትም የቀብር ስርዓቱ ላይ ንግግር ካደረጉት የትህነግ ወዳጆች አንዱ ነው። የዶክተር ቴድሮስ ጓደኛ ነው። የአሌክሳንደር ሮንዶስም የቅርብ ወዳጅ ነው። ሮንዶስን በሚመለከት ከዚህ ቀደም በሰፊው ፅፌያለሁ። ሰውየው አሁን ሲመጣ የተሰጠው ተልዕኮ በዋናነት “ድርድርና እርቅ” የሚለውን እንዲያሳካ ነው። ይህ ካልሆነለት ኢትዮጵያን በግጭት ለማተራመስ እና ዶክተር አብይን ከማስገደል አይመለስም።
ሰውየው ከአንድ ወር በፊት ስለ ኢትዮጵያ እና ስለ ቀጠናው የተናገረው ነገር ጉድ ያሰኛል። ጭራሽ “ግብፅ፣ ቱርክና የአረብ ኢምሬት ቀጠናውን ለማረጋጋት ሚና ሊኖራቸው ይገባል” ብሏል። አስቡት ግብፅ ለኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት ስትሰራ?! የጉምዝን ሽፍታ የሚያስታጥቀው ማን ሆነና? ኦነግ ሸኔን በተለይም ወለጋ ላይ ያለውን ሽፍታ ማን ነው እያስታጠቀ ያለው? ባለኝ መረጃ ወለጋ ላይ በየቀኑ የሚገባው መሳሪያ ለጉድ ነው። ዘመናዊ መሳሪያ ጭምር ነቀምት ውስጥ በየጊዜው ይጎርፋል። ከግብፅ የመጣ እንደሆነም ነዋሪዎች ይናገራሉ። የሰሞኑ ገጀራ በማን እና ከየት የመጣ ነው? ፅንፈኛውንስ በገንዘብ የሚደጉመው ማን ነው? ነባር እና አዳዲስ ዩቱይቦችን እና ቻናሎችን የሚረዳው ማን ነው? በአንድ ጊዜ ይህ ሁሉ የምንሰማው እና የምናየው የጥላቻ ንግግር ማን ያቀደው ነው?? ብዙ ነገር አለ።
ብቻ እዚህ ላይ እንዳይቆጨኝ መናገር የምፈልገው ስለሚመጣው ዲፕሎማት ነው። ሰውየው በሴራ የተካነ ነው። ለዚያውም በግድያ ሴራ የካበተ ልምድ አለው። ግጭት በማስፋፋት በቂ እውቀት እና ልምድ አለው። ዶክተር አብይን ኢሳያስ አፈወርቂን እና ፈርማጆን በክፉ አይን የሚመለከት ሰው ነው። የሶስቱን ጥምረት በጭራሽ አይፈልግም። “ቀጠናው መረበሹ አይቀርም: ኢትዮጵያ እንደ ሶሪያ ልትበታተን ትችላለች: የብሄር ውጥረቱ ወደ እርስበርስ ግጭት ያመራል” ብሎ ያምናል።
ፌልትማን ለፎሬይን ፖሊሲ በሰጠው ቃለመጠይቅ… “የመጨረሻውን አስቸጋሪ ውይይት ከጠ/ሚ አብይ ጋር አደርጋለሁ”። ይህም ከባድ እንደሆነ ከገለፀ በኋላ … “አብይ ጠንካራ እና አንድነቷ የተጠበቀች ኢትዮጵያን እንጅ የተከፋፈለች ኢትዮጵያን ማየት የሚፈልግ አይመስለኝም” ይላል በሾርኔ። ከዚያም… “Ethiopia has 110 million people, if the tensions in Ethiopia would result in a widespread civil conflict that goes beyond Tigray, Syria will look like child’s play by comparison.” ብሏል። አንድምታው ምንድነው ብንል ዶክተር አብይ የአሜሪካንን ምክረ ሃሳብ ካልተቀበለ ግጭቱ ከትግራይ ይዘልና ኢትዮጵያ ሶሪያን የምታስንቅ ሃገር እናደርጋታለን እንደማለት ነው። ዛቻ ነው!!!!
ይህ ሰው የአሜሪካ የመጨረሻ ካርድ ነው። አብይን ለማስገደል ይሰራል ስል የዚህን ሰውየ የግድያ ሴራ ተሞክሮውን እንይ። ፌልትማን ከ2004 – 2008 በሊባኖስ የአሜሪካ አምባሳደር ሆኖ ሰርቷል። በወቅቱ ጠ/ሚ/ር ራፊቅ የሊባኖስ ጠሚ ነበር። ሊባኖስ የተመደበው ራሽያ ቻይና ሶሪያ እና ኢራን ከሌባኖስ ጋር ቅርብ ጉድኝት የፈጠሩበት ወቅት ስለነበርና እንዲሁም ጠሚ ራፊቅ በእስራኤል የተያዘውን የሊባኖስ ደቡባዊ ግዛት ለማስመለስ እንቅስቃሴ የጀመረበት ወቅት ነው። ጠ/ሚ ራፊቅ ለሃገሩ ብዙ የሰራ እና ብዙ ህልም የነበረው ነበር።
አሜሪካም ሴረኛውን ዲፕሎማት ወደ ሊባኖስ ላከችው። ሰውየው በገባ በጥቂት ወራት የሊባኖስ ፕሬዝዳንት እና ጠ/ሚሩ ተጋጩ። አመፅ ተነሳ። ሊባኖስ ተናጠች። ፍትጊያው በዛ። ጫናው ከበደ። ራፊቅ ከስልጣኑ resign አደረገ። ለቀቀ። ከወራት በኃላም መኪናው ውስጥ በFebruary 2005 በቦንብ ተገደለ። ገዳዮቹ እስከዛሬ አይታወቁም። ጠ/ሚ ራፊቅ ከአሜሪካና ከእስራኤል ፍላጎት በተቃራኒ ቆመሃል ስለተባለ በፌልትማን ሴራ እንደተገደለ ይነገራል። ከዚያ በኋላ ሃገሪቱ ብዙ አመፅ እ ና ኪሳራ አስተናገደች። ከሱኒ የተወለደው ራፊቅ የሱን መገደል ተከትሎ በሱኒ እና ሸአ መካከል ከፍተኛ ልዩነት ተፈጠረ። ግጭቱ ቀጠለ። ተባባሰ። ሊባኖስ ብዙ መከራ ገጠማት። መስማማትና አንድነት ጠፋ። ብዙ ተጎዱ!
ዛሬም ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣው ምርጫውን አስቆሞ ጁንታውን እና ሽፍቶችን ወደ ስልጣን በድርድር ለማምጣት … ካልሆነም በተለይ የኦሮሞ እና አማራን ግጭት በማፋፋም ኢትዮጵያን በማስጨነቅ “አብይ መቆጣጠር አልቻለም” ለማስባል እና ቀጥሎም በግድያም ይሁን በሌላ ዘዴ አብይን ለማስወገድ ነው ብዬ አምናለሁ። ይህን አጀንዳ የሚያስፈፅሙ ባንዳዎች ቀድመው ይህን ስራ ጀምረዋል። ጥላቻ እያራገቡ ነው። የዶ/ር አብይን ስም ከተገቢው በላይ ለማጠልሸት እየተሞከረ ያለው አብይን ለማስወገድ ምዕራባዊያኑ ከግብፅ እና ከእስራኤል ጋር የጀመሩት የመጨረሻው ፕሮጀክት አካል ነው። አሁን የምናየው እጅግ አደገኛ የጥላቻ ንግግሮችም የዚሁ አካል ነው። ገጀራና መሳሪያ እያስገቡ ነው። ቦንብም አለ። የተደገሰልን ብዙ ነው። ተቀናጅተው እየሰሩ ነው። በመሆኑም፤
1ኛ) መንግስት የንፁሃንን ግድያ ያስቁም! በቃ ይህ ንግግር እና ድርድር አያሻውም! ዋናው ይህ ነው!!!! መንግስት ከጨከነ ሞትን መቀነስና ማስቆም ይችላል!
2ኛ) መንግስት አሁንም ይፍጠን! ውስጡን ያጥራ! ብልፅግና ውስጥ ብዙ አስፈጻሚዎች አሉ! በተለይ ኦሮሚያ እና አማራ ብልፅግና ውስጥ አሉ! ምንም ርህራሄ አያስፈልግም! እርምጃ ይወስድ!!!! Home arrest is also an option! (ቤት ውስጥ ማቆየት)
3ኛ) በአዲስ አበባ እና ዙሪያዋ መንግስት ክትትሉን ጠበቅ ያድርግ! በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚኖሩ ወገኖቻችን ይመልከት! ውይይት ያድርግ! ድጋፍ ለሚያሻቸውም ይስጥ! በቂ የፖሊሳና ወታደራዊ ጥበቃ ይደረግ!
4ኛ) የጥላቻ ንግግርን የሚሰብኩ ሚዲያዎች ይዘጉ! መሃል አዲስ አበባ ቦሌ መድኃኒአለም ላይ ተቀምጦ ጥላቻን የሚነዛ ቴሌቪዥን ከቶ ምን እየተጠበቀ ዝም ይባላል? ለጥላቻ የተከፈቱ ዩቲዩቦች ምን እየተጠበቀ ነው? ጥላቻን የሚነዙ፤ ወጣቱን በጎበዝ አለቃ እንዲተዳደር የሚሰብኩ፤ መከላከያን የሚያንቋሽሹ እና የሚከፋፍሉ ሰዎችስ ሃይ አይባሉም ወይ?? መንግስትም ሆነው አክቲቪስትም ሆነው የሚሰሩ ሰዎች አንድ አይባሉም ወይ??? ማንም ቢሆን ህግ ይከበር!!
ደጀኔ አሰፋ
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
ነፃ ሕዝብ says
ጉድ ያለው ገንፎ እያደር ይፋጃል ይባላል ፥ የኢትዮጵያ ቀንደኛው ጠላትና ከፋፋይ ነፍሰ_ገዳዩ አብይ አህመድ አሊ መሆኑ ቀረ እንዴ ? በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ውስጥ የአማራን ሕዝብ የሚያስገድለው እርሱ ያስታጠቃቸው የኦሆዲድ ሸኔዎች አይደሉም እንዴ ? ይህንን ነፍሰ_ገዳይ ማስገደል አይደለም ከዚያም በላይ ቢያደርጉት ምንኛ እግዚአብሔር በታረቀን ነበር ፥ በትናትናው ምሽት በአ/አበባ _ጎጃም መንገድ ላይ አያሌ ሾፌሮች ተገደሉ ፥ ቆሰሉ ፥ በተከታታይ በጎሃ ፅዮን ከተማ ከፍተኛ ግፍ እየተፈጸመ ይገኛል ፥ ስለዚህ የአብይን መገደል ብቻ ሳይሆን ኦነግ መራሹን ፀረ_ኢትዮጵያ ማጥፋት ለነገ የማይባል ወሳኝ መዕራፍ ነው ፥ ምዕራባውያኑም የጀመሩትን እንዲቀጥሉበት በውጭ የምንገኝ ኢትዮጵያውን አስፈላጊውን ድጋፍ እናደርጋለን ፥ የእናንተ ፀረ_አማራ ኢትዮጵያ የት እንደምትደርስ እናያለን ፥ ኢትዮጵያ በአማራ ሕዝብ ደምና አጥንት ተገንብታ ዛሬ ግን ለመኖር ሲኦል ሆናበታለች ፥ ይህንንም ያደረገው ከሃዲውና ዘረኛው ብሎም ነፍሰ_ገዳዩ አብይ አህመድ የግራኝ አህመድ የጥፋት ውላጅ ስለሆነ ሞቱን እንዲፋጠን ይደረጋል ፥ ሞት ለኦሮሙማው አፓርታይዳዊ አገዛዝ ይሁን !!!
Tesfa says
መቸም እንደ ሃበሻ ያለ በደፈናው ፈራጅ በምድር ላይ ያለ አይመስለኝም። የሰው መተራረጃ ጀገራ ከሚያስገባ ተውሳክ ጋር እንዴት ባለ የሂሳብ ስሌት ነው የሰው ልጅ ቁጭ ብሎ ልዪነትን በመነጋገር የሚፈታው? ጌታቸው ረዳ አፉን በከፈተ ሰአት ሁሉ ይህን ክፍለ ጦር ደምስሰን ያን ጨፍልቀን ሲል እንዴ ሃገሪቱ ምን ያህል ክፍለጦር ነው ያላት ያስብላል። በሌላ መልኩ የሃገሪቱ የጦር መሪዎች ወያኔን ደምስሰን፤ በንፋስ ፊት የተበተኑ ድቄት ናቸው ወዘተ ሲሉ ግራ ያጋባል። ማን ይታመናል። በተንኮል፤ ሃገር በማፍረስ፤ በውሸት፤ በዘርና በቋንቋው ዙሪያ ከሰከረ ጋር ምንም ህብር ነገር አይገኝም። የምዕራባዊያን ለወያኔ ጠበቃ መቆም ዋንኛ ምክንያቱ ሰርቀው ስለሚያካፍሏቸውና ተላላኪዎቻቸው ስለነበሩ ነው። የግብጽ ሆስኒ ሙባረክ ከ 40 ዓመት በህዋላ ሳይወድ በግድ ከስልጣን ሲወገድ አሜሪካ ዝም ብላ ነው ያየችው። ከዚያም ምርጫ ተብሎ ዶ/ር ሞሃመድ ሞርሲ ሲመረጥ በዚህም በዚያም ብለው የራሳቸውን ሰው ወታደራዊውን አል ሲሲን በስፍራው አስቀመጡ። ከቆየ ታሪክ ስንነሳ ደግሞ የፓናማው ጄ/ኖሬየጋ አቅፈው ደግፈው ስልጣን ላይ እንዳላወጡት ሃገሩን ወረው አስረው ከፈረድበት በህውላ የአሜሪካ እስር ጊዜውን ሲጨርሽ ፈረንሳይ በሌላ ወንጀል ትፈልግሃለች ተብሎ በዚያው ነው ተወርውሮ የቀረው። ረጋ ብሎ በአለም ላይ የተደረጉና የሚደረጉ ግጭቶችን፤ የመንግስት ግልበጣዎችን በመረጃ ተደግፎ ለተመለከተ የምዕራባዊያን እጅ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እንዳለበት ልብ ያለው ይረዳል።
አንድ ነገር ትዝ አለኝ ከመቀሌ ወደ አክሱም እየተጓዝን ነው። ጊዜው ረጅም ነው። በየስፍራው የፍተሻ ኬላዎች አሉ። ፍተሻው ላይ ውረድ ተባለ እና ወርደን መታወቂያ እየተጠየቀ ሰው ወደ መቀመጫው ሲመለስ አንድ ቄስ ቁመው ቀሩ። ከዚያ በትግርኛና በአማርኛ መታወቂያ ይላቸዋል። ልጄ የእኔ መታወቂያ መስቀሌ ነው በማለት መስቀላቸውን አውጥተው ያሳዪታል። ለቅዳሴ ነው የምሄደው ቢሉት ፈታሹ ፈገግ ብሎ ይግቡ ይላቸው። ከገቡ በህዋላ ቄሱ በአማርኛ ሰው በሃገሩ እንዲህ ሃበሳ ማየት ይላሉ። አንድ ከአዲስ አበባ የመጣ ሰው አባቴ አዲስ አበባ ታቦት ይዘውም ቢለምኗቸው እሺ አይሉም። አያማርሩ ተመስገን ይበሉ ቢላቸው ፈገግ ብለው መቼ ይሆን ምድሪቱ የምታርፈው ቢሉ ሰው ፈርቶ ዝም ይበሉ አባ እንዳላቸው ትዝ ይለኛል። ዛሬ ኢትዮጵያ እንድትፈርስ ቀዳሚዎቹ አትፈርስም እያሉ የሚነግሩን ለፍላፊዎች ናቸው። ሃገርህ ችግር ላይ ናት ና/ነይ ሃገርሽን በውትድርና አገልግሉ ሲባሉ ከሃላፊነት ከሚሸሽ ትውልድ የሃገርና አንድነትና የህዝቦችን እኩልነት የመጠየቅ መብት የላቸውም። አሜሪካ ሁልጊዜም ሃይሉ ወደ አጋደለበት ነው የሚያዘነብሉት። ይህ የአሁኑ የአዞ እንባ ማንባትና በተለያዬ መንገድ ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማድረግ የሚደረገው ሴራ የሩቅ ጊዜ ህልማቸው ነው። አሁን በአዲሱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የኢትዮጵያን ሁኔታ እንዲከታተል ባለስልጣን የሆነው ሲናገር ” ኢትዮጵያ ከሶሪያ የከፋ ትሆናለች” ይለናል። መቼ ነው ጥቁሩ ዓለም የነጩ ዓለም ለአፍሪካ በፊትም ዛሬም ወደፊትም እንደማያስብ የሚረዳው? አሁን በብዙ እዳ በወለድ አገድ የተጠፈሩ ሃገሮች ስንት ናቸው? ለምንስ የአለም ባንክና ሌሎችም የመክፈል አቅም እንደሌላቸው እያወቁ እዳ ላይ እዳ በእነዚህ ሃገሮች ላይ ይጭናሉ? መልሱ ከታላቁ ሴራችው አንድ ብልሃት ሃገሮችን በብድር ስም በእዳ ቀፍዶ መያዝ ነው። የአሜሪካም ሆነ የአውሮፓ ህብረት ለወያኔ እንባ ቢያፈሱ አይፈረድባቸውም። የጠለቀው ሚስጢር ግን ነጩ ህበረተሰብ ለጥቁር ህዝብ ደህንነትና ብልጽግና ደንታ አይሰጠውም። ሁሉም የየሃገሩን ጥቅም ብቻ ነው ቀዳሚ መመሪያቸው የሚያደርጉት። የእነዚህ ሃገሮች ስለ ሰው ልጅ ህልውና፤ ነጻነት፤ ዲሞክራሲ፤ የመሰብሰብና የማምለክ ነጻነት ወዘተ የሚያላዝኑት በሃሳብ የዘገዪትን ለማምታታ እንጂ የእነርሱ ተንኮል ሥር የሰደደ በመሆኑ በቀላሉ ከሃገሮች የሚነቀል አይሆንም። የሱዳን በኢትዮጵያ ድንበር ላይ ትንኮሳ መጀመርዋ በአሜሪካና በተለያዪ የአረብ ሃገሮች አይዞህ ባይነት ነው። ስለሆነም ምንም ሃገር ይህን ደግፎ ያን ነቅፎ በአደባባይም ሆነ በሚስጢር፡ ሲነቅፍ ለምን እንዴት ማን በዚህ ያተርፋል ለህዝባችንሽ ምን ይጠቅማል በማለት መመርመር እንጂ እንዳለ ጨልጦ የወሬ ወሬ አናፋሽ መሆን ገልጃጃነት ነው። የትግራይ ህዝብ በሰላም እንዲኖር፤ ኢትዮጵያ በኢትዮጵያዊነቷ እንድትቀጥል ከተፈለገ የዘር፤ የቋንቋ፤ የክልል ፓለቲካ ከስሩ መደርመስ አለበት። ወያኔን አባሮ የኦሮሞ ጠባብ ብሄርተኞች ከመጣሁ ሃይል ጋር ተለጣፊ ከሆነው የአማራ አምራር ጋር የህዝባችን ሰቆቃ ማራዘም የሮም አወዳደቅ በመውደቅ እንደተባለው ሃገሪቱን ፍርክርኳን ለማውጣት እንጂ በሃገሪቱ መፍረስ የውጭም ሆነ በምድሪቷ የሚርመሰመሱ ሁሉ ተጠቃሚ አይሆንም። አሁን ሃገሪቱ ያለችበት ሁኔታ አፋፍ ላይ እንዳለ ትልቅ ድንጋይ ነው። ገፊዎችም እዚያው ለመድረስ በመፏንቀቅ ላይ ናቸው። ድንጋዪ ሲገፈተር ምድሪቱም አብራ የደም መሬት ትሆናለች። ለነገሩ አሁንም የምናየው ደም በየስፍራው ሲፈስ ነው። የመጨረሻው መፍረስ ግን በታሪካችን ያልታዬ ይሆናል። ይህን ስጽፍ የሚሰማኝ የሞተን ሰው ነፍሱን ይማረው እንደማለት ነው። ፌዝ ነገር። ከሞቱ በህዋላ ምህረት የለም። በጎነትና ምህረት በምድር ላይ ነው። የሞተው/ተችው በፈጣሪ ስለመማራቸው ምንም ማስረጃ የለንም። በምድራችን ላይ ያለውን ሰቆቃና እሪታ እያየን እኔን ካልነካኝ ምን አገባኝ ለሚሉ ጠብቅ ደጃፍህ ላይ ይደርሳል። ያኔ የአንተን ጭኹት ማን ይሰማሃል። ነፍስ ይማር ይሉሃል ተራፊዎች። ለዚያውም ዘርና ቋንቋህን ተደግፈው። አያድርስ ነው። የ 3ሺ ዘመን ነጻነት አለኝ የምትል ሃገር እንዲህ በየሰፈሩ ሰንደቅ ተካዮችና ቆንጨራ ይዘው የሰው አንገት የሚቀሉ ይብቀሉባት? ማህረነ ክርስቶስ። ጠብቀን እንይ፡፡ በቃኝ!
Mussie Abraha says
ኣገሪቱ የሴረኞች ፋብሪካ ናት።ኢትዮጵያን እያፈረሳት ያለው ዋናውና ቀንደኛው ጉዳይ የኣማራ የተሳሳተና ዕርባናቢስ የታሪክ ትርክት ነው።ይቺ በደም የተጨማለቀች ኣገር፡ እንደ ኣገር የመቀጠልዋ ትርክት ኣብቅተዋል።
ከሁሉም ወገን የሚፈሰው የንፁሃን ደም የሚያሳዝን ቢሆንም ፡ትግራይን በመደምሰስ የምትበለፅግ ኢትዮጵያ ኣትኖርም። ገና ብዙ ጉድ እንሰማለን። የትግራይ ሕዝብ ደም በከንቱ ፈሶ ኣይቀርም።
Tesfa says
ልጅ ሙሴ – በዘርህ አታልቅስ። እንባና ሃዘኔታህ ለሁሉም ወገን ይሁን። አሁን ማን ይሙት ከወያኔ የባሰ ጨካኝ በሃበሻ ምድር ተፈጥሯል? የትግራይ ህዝብ ሰቆቃ ምንጭና ባህሩ ወያኔ እንደሆነ እንዴት አይገባህም? ማን ነው ትግራይን የሚደመስሰው? መልሱ ማንም ነው። አይቻልም! የወያኔ ካድሬዎችና ወያኔዎች ችግራቸው ዘር ተኮር ነው። አማራ አማራ ትላለህ አሞራ ይብላህ እንጂ። አማራ የትግራይን ህዝብ ይወዳል፤ ያከብራል። ግን እንዳንተ ያሉ የፓለቲካ ሸፋፎች ሁልጊዜም ዘርና ቋንቋን ተገን አድርገው ሰው በማናከስ ትርፍ የሚያካብቱ ወሮበሎች ናቸው። ወያኔ ማለት ማፊያ ማለት ነው። ወያኔ በምድሪቱ የሰራው ግፍ ጣሊያን በወረራው ጊዜ አልፈጸመውም። ይህ እውነት እንጂ እንዳንተ ጡሩንባ የፈጠራ ወሬ አይደለም። ሰው በሰውነቱ ብቻ የሚመዘንባት ምድር እንድትሆን የራስህን አስተዋጾ አድርግ።
አሁን ባለው ወያኔ ሰራሽ ግብግብ ደማቸው የሚፈሰው ወገኖች ሊያሳዝኑን ይገባል። ግን በአመዛኙ አሁን ትግራይ ውስጥ ያለው ግድያ ትግራዋይን ትግራዋይ ነው እየገደለ ያለው። ሸር፤ ሸፍጥ፤ የፈጠራ ወሬ፤ ደርግን ደምስሰናል አሁንም እናሸንፋለን ገለ መሌ በማለት የትግራይን ልጆች የሚያስጨርሰው ወያኔና በጊዜአዊ አስተዳደር ውስጥ የተሰገሰጉት የወያኔ የሥራ አስፈጻሚዎች ናቸው። የትግራይ ህዝብ እፎይ እንዲል ከተፈለገ ወያኔና የአሰራር መዋቅሩ ለአንድ ጊዜና ለመጨረሻ ጊዜ ተደርምሶ በሥፍራ ነጻ በሆነ መልኩ የትግራይ ህዝብ የመረጣቸው አመራሮች በሥፍራው ሲተኩ ብቻ ነው። አሁን የተያዘው ወሬ ደመሰስን፤ ተደመሰሱ ብቻ ነው። የውስልትና ወሬ። አንተም ከዚህ የሞት ፓለቲካ አስተሳሰብ ውጣና ህዝብህን በምትችለው መልካም መንገድ አገልግል።
ዮሐንስ ዮናታን says
ከላይ የሰፈረው ዝብዝብ አብይን አድኑልኝ ነው። አብይ ከመጣ ጀምሮ ፣በትግራይ በተጀመረው ጦርነት ይበልጥ የአማራው ብሄሔረሰብ ተጨፍጭፏል። በእርግጥ ለጊዜው የህወሀት ሎቢ በዓለም ላይ የተከሏቸው ዘረኞች የተሳካላቸው ይመስላል።ገዜው በተራዘመ ቁጥር ምኞታቸው እንደማይሳካ ከአሁኑ ገብቷቸዋል፣አንተም።
ያልገባህ አብይ በምን መነሻ እንደመጣ ሁላችሁም ረስታችሁታል። ሕዝብ ሳይሆን የአጭር ጊዜ ማስታወሻ አይምሮ የተሳነው ፣እናንተው ናችሁ። ራስን የግዛት ዘመን እንደሚሰብከው በ”ብልፅግና” ኢትዮጵያን ለማረማመድ ሳይሆን የራሱንና የኦሮሙማን ተእልኮ ለማስረዘም በመሆኑ ለውድቀት ከአሁኑ ተጋልጧል። የሚያሳዝነው የኦሮሞ ወንድሞቻችን ይሄን አለመገንዘባቸው ነው። ኦሮሞ ወደፊት የአጥፊነት፣የገዳይነት ፣የጨፍጫፊነት ምሳሌነት መሆኑ ያሳዝናል።ይሀንንም ወደፊት የኢትዮጵያ ታሪክ በማፈሪያነት ይመዘግበዋል።
Love says
Dear my brother Yohanes yonatan, you are talking two opposing ideas in thinking for the oromo people; This is a childish approach to create the usual ethnic conflict.
Anyways don’t worry Ethiopia and its people will live /are living in peace as usual except some few bad happenings in % which is tolerable and found even in developed countries and full of military power.
Everything goes and will go as per the command from God!!! My friend the small stone that you are throwing may hit your own soul nothing else.
Cheers!
Love says
Dear my brother Yohanes yonatan, you are talking two opposing ideas in thinking for the oromo people; This is a childish approach to create the usual ethnic conflict.
Anyways don’t worry Ethiopia and its people will live /are living in peace as usual except some few bad happenings in % which is tolerable and found even in developed countries with full of military power.
Everything goes and will go as per the command from God!!! My friend the small stone that you are throwing may hit your own soul nothing else.
Cheers!