• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በአስመጪ ዳዊት የማነ ሀሰተኛ ሰነድ ወደ ሀገር ዉስጥ ሊገባ የነበረ ገጀራ ተያዘ

April 28, 2021 10:15 am by Editor 1 Comment

ከፌደራል ፖሊስ ፈቃድ እንደተሰጠው በማስመሰል በተጭበረበረ ሰነድ ርክክብ ተፈጽሞ ባለቤት የተባለው ሰው ከተረከበ በኋላ በተደረገ ክትትል 186 ሺህ 240 ገጀራ በቁጥጥር ስር ዋለ። በጅምላ ጭፍጨፋ በተካሄደባቸው አገራት በተገኘ ልምድ ገጀራ ክልከላ የጣለበት የእጅ የጥፋት መሳሪያ ነው። ገጀራው በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በማህበራዊ ሚዲያዎች ህጋዊ ፈቃድ እንዳለው እየተገለጸ የሚሰራጨው ደብዳቤ ሃሰት መሆኑም ተመልክቷል።

ከ15 ቀን በፊት በአስመጪ ዳዊት የማነ ስም ብዛቱ 186,240 የእጅ ገጀራ በአራት ባለ 20 ጫማ ኮንቴይነሮች ከቻይና ተጭኖ ሞጆ ጉምሩክ ይደርሳል። እቃው በዲክላራሲዮን ቁጥር 4-1919/21 ተመዝግቦ ወደ ሀገር ዉስጥ እንዲገባ ከፌዴራል ፖሊስ የተፈቀደለት በማስመሰል እና ሐሰተኛ ሰነድ የተዘጋጀለት ነው።

ይኸው ሃሰተኛ ሰነድ ለገቢ ዕቃ አወጣጥ የሰነድ መርማሪው አቅርቦ ሰነዱ ተመርምሮ ከ7.7ሚሊዮን ብር በላይ ቀረጥና ታክስ ይከፈልና እቃው ይለቀቃል። እቃው ከተለቀቀ በኋላ በጉምሩክ ኮሚሽን እና በሞጆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኢንተለጀንስ በኩል ክትትል ተደርጎ የቀረበው ሰነድ ሲጣራ ሐሰተኛ እና እቃዉም ወደ ሀገር ዉስጥ እንዲገባ ከፌዴራል ፖሊስ ፈቃድ ያልተሰጠው መሆኑ ተረጋገጠ።  

ጉዳዩ ከ15 ቀን በፊት የተፈጸመ ቢሆንም፤ አስመጪው “ያቀረብኩት ሰነድ ህጋዊ ነው” በማለት ቅሬታ ስላቀረበ ከፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጋር በጣምራ የማጥራት ስራ ተሰራ። እንደ ኦቢኤን ዘገባ ማጣራት የተካሄደበት ሰነድ ሐሰተኛ እና ከፌደራል ፖሊስ ፍቃድ ያልተሰጠው መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

በተጨማሪም በጉምሩክ ኮምሽን ሰራተኛ የእጅ ገጀራው ተገቢውን የጉምሩክ ስነ-ስርዓት በመፈጸም እንዲስተናገድ የሚገልጽ ሐሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት ለማውጣት የተሞከረ ሲሆን ይህም ሐሰተኛ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

ይህን መነሻ በማድረግም በፌዴራል ፖሊስ ለሞጆ የወንጀል ምርመራ ማስተባባሪያ ፅ/ቤት መረጃዉን በመስጠት በተደረገው እልህ አስጨራሽ ክትትል የእቃው ባለቤት እና ትራንዚተሩ ተይዘው ጉዳዩ በምርመራ ላይ ይገኛል። ገጀራ ክልከላ ከተደረገባቸው እቃዎች አንዱ ሲሆን ከፌደራል ፖሊስ ሕጋዊ ፈቃድ ሳያገኙ ማስገባት አይቻልም። በዚም ምክንያት ነው አስመጪው አቶ ዳዊት የማነ ከፌደራል ፖሊስ ህጋዊ ፈቃድ እንዳገኙ በማስመሰል ገጀራውን በሃሰተኛ መረጃ ያስገቡት።

በአንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በጉምሩክ ኮምሽን ባለሙያ እቃው እንዲወጣ የተፈቀደበት ደብዳቤ በማስመሰልና የሐሰተኛውን የደብዳቤ ፎቶ በመጠቀም አስመጪው ሕጋዊ እንደሆነ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ ሐሰተኛ መሆኑን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ማስታወቁን ዜናው ያመለክታል። በማህበራዊ ሚዲያ ገጀራው መያዝ የለበትም የሚሉትና ሃሰተኛ ደብዳቤውን በመለጠፍ የሚሞግቱት ወገኖች ላይ ክትትል እየተደረገ መሆኑም ተሰምቷል። የተያዘው ገጀራ መለቀቅ እንዳለበት እየሞገቱ ያሉት ክፍሎች ምኞታቸውና ሃሳባቸው ግልጽ መሆኑም ተመልክቷል። (ethio12)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Left Column, News

Reader Interactions

Comments

  1. MESFINACHEW A KASSA says

    April 29, 2021 01:51 pm at 1:51 pm

    IF YOU CAN CHANGE OR ANNOUCE A BID TO CHANGE ALL THAT MACCHETE INTO A NIDDLE TO HELP PEOPLE GET THE COVID-19 VACCINATION I WILL GIVE A DONATION.

    THANK YOU!
    GOD BLESS AND PROTECTINNOCENT ETHIOPIANS FROM EVIL!!

    MUCHFUN A KASSA.
    OTTAWA,CANADA.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule