መንግሥት ህወሃትን ቀስ በቀስ ሥሩን እየቆራረጠ ቢቆይም አብዛኞች ባለመረዳትና በተገዙ ኃይሎች ውዥንብር ዕድሜው ሊራዘም እንደቻለ ለህወሃት ቅርበት ያላቸው እየገለጹ ነው። በተቀነባበረ ዕቅድ ሃጫሉ እንዲገደል ተደርጎ መንግሥትን ለመገልበጥ የታቀደውና የመጨረሻ የተባለው ሤራ መክሸፉ ህወሃት መንደር ግራ መጋባት መፍጠሩ ተስምቷል። የዐቢይ አስተዳደር እንደሚባለው ደካማ እንዳልሆነም አንዳንዶቹ በይፋ ሲናገሩ ተደምጧል። ለውጡን ተክትሎ ከህወሃት አሰልቺ የስብሰባና የግምገማ (ምይይጥ) ባህል በተቃራኒው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፍጥነት መጓዛቸውና ለህወሃቶች ከጅምሩ የማሰቢያ ጊዜ የከለከለ ነበር። የጎልጉል ታማኝ የመረጃ ምንጭ እንደሚሉት፤ የህወሃት ከፍተኛ አመራሮች ሲነጋ ልክ እንደማንኛውም ተራ ዜጋ ከፍተኛና አዳዲስ ውሳኔዎችን ይሰማሉ። በዚህም እነርሱ ለአንዱ ጉዳይ አንድ ወር ሲሰበሰቡና … [Read more...] about ህወሃት “የመጨረሻ” ያለው ሤራ መክሸፉን መቀበል አቅቶታል