ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ከትናንት በስቲያ አመሻሹን ከጋዜጠኞች ጋር ተገናኝተው ነበር። ሚዲያው በምርጫው ላደረገው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ለማመስገን በተዘጋጀው በዚህ መርሀ ግብር ላይም ሚዲያውን ካመሰገኑ በኋላ ስለ ምርጫው እና ስለ ትግራይ ሁኔታ ለጋዜጠኞች አብራርተዋል። ካነሷቸው ነጥቦች መሀከልም የተወሰኑትን በግርድፍ እንዲህ አስታውሻቸዋለሁ በምርጫው እኛም ሆነ ተቃዋሚዎች የተመኘነውን ያህል ቡራቡሬ ፓርላማ አላገኘንም! ተቃዋሚዎች በምርጫው ውጤት ደስተኛ ባይሆኑም በምርጫ ቦርድ፥ በፍርድ ቤት እና በሚዲያ ላይ ቅሬታ እንደሌላቸው ተስማምተናል! ሚዲያው የትርክት ለውጥ ላይ በደንብ መስራት አለበት። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ከዚህም በላይ መስበክ አለበት! በትግራይ ባካሄድነው ዘመቻ ተይዘውብን የነበሩትን መሳሪያዎች በሙሉ አስመልሰናል። ማስተካከል የምንፈልገውንም … [Read more...] about “መቀሌን ከሽሬ ወይም ከበሻሻ የሚለያት የስበት ማዕከል የለም”
abiy ahmed
ምዕራባውያን – “ለድርድር እናስገድዳለን ካልሆነ ወደ ዶ/ር ዐቢይ እንዞራለን”
ይህ ድምፅ የምዕራባውያኑ የመጨረሻው ድምፅ ነው። ወስነዋል። የመጨረሻውን ጫና ጀምረዋል። ጫናው እየጨመረ ይሄዳል። ለምን በአዲስ መልክ ጫናውን ጀመሩ ብንል ተስፋ አድርገውት የነበረው የተመድ የፀጥታው ም/ቤት እነሱ እንደሚፈልጉት ባለመወሰኑ ይመስላል። በክፍል 3 የመጨረሻ ካርዶችን እንይ:-1ኛ) የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን ዶክተር አብይ ጋር ደውሎ ነበር። በትግራይ ረሃብ ሊከሰት ስለሚችል ያሳስበኛል። በሃገሪቱ ያለው የብሄር ውጥረቶችም ያሳስበኛል። የኤርትራ ጦር ይውጣ። ሁሉም አካላት ጦርነት አቁመው ወደ ድርድር መምጣት አለባቸው። ወዘተ የሚል ውይይት አድርጓል። የዚህ ስልክ አላማ በአጭሩ ከሞተው ጁንታ ጋር "ድርድር እና እርቅ" አድርግ የሚል ነው። ካልሆነ ግን (የብሄር ውጥረቶች ያልኩህ ሌላ መልክ እንዲይዙ እናደርጋለን። እርስበርስ ትፋጃላችሁ። ከዚያም አልቻልክም ተብለህ … [Read more...] about ምዕራባውያን – “ለድርድር እናስገድዳለን ካልሆነ ወደ ዶ/ር ዐቢይ እንዞራለን”
“በኢትዮጵያ ክብርና ጥቅም ከመጣችሁ አንገቴ ይቀላል እንጂ አልደራደርም”
“ተላላኪ መንግስት አይኖርም” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለበርካታ ዓመታት የነጮ ተላላኪ በመሆን ያገለገለው እና ሞት እንደ ቡሽ ክዳን ያስፈነጠረው መለስ ዜናዊ በግፍ ኢትዮጵያን በገዛበትና ከዚያ በኋላ ባሉት ዓመታት ፈጽሞ ባልተሰማ ሁኔታ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለአገራቸው ያላቸውን ስሜት በግልጽ ተናግረዋል። ኢትዮጵያን ተቀጥሮ እንደሚያስተዳድራት መሪ “አገሪቱ” እያለ ሲጠራት ከኖረው መለስ ዜናዊ በኋላ ፍጹም በተጻረረና ልብን በሚያሞቅ የአገር ስሜትና ወኔ ከእንግዲህ በኢትዮያ ተላላኪ መንግሥት እንደማይኖር ነው ለሕዝባቸው በፓርላማው ውይይት የተናገሩት። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ “በኢትዮጵያ ክብርና ጥቅም ከመጣችሁ አንገቴ ይቀላል እንጂ አይደረግም” ሲሉ ተጽዕኖ ለማሳደር ለሚሞክሩ አካላት ተናግረዋል። ዛሬ (ማክሰኞ) ለፓርላማ ባቀረቡት ንግግር … [Read more...] about “በኢትዮጵያ ክብርና ጥቅም ከመጣችሁ አንገቴ ይቀላል እንጂ አልደራደርም”
“ከዚህ በኋላ ህወሓት ማለት በነፋስ የተበተነ ዱቄት ነው” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ
ዛሬ (ማክሰኞ) በተካሄደው 5ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሰጡት ማብራሪያ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፤ የኢኮኖሚው አጠቃላይ ገጽታ፤ የፍኖተ ብልጽግና እቅዳችን ያለፉትን 3 አመታት የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ ነው፤የአገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም መሰረታዊ አጀንዳዎቻችንየብድር ጫና መቀነስተጀምረው የቀሩ በርካታ ፕሮጀክቶች በፈጠነ መንገድ ማጠናቀቅየወጪ ንግዱን ማሻሻልና ማሳደግገቢን ማሻሻልገበያን ማረጋጋትና የዕድገት ቀጣይነትን ማረጋገጥ፤የህዳሴ ግድብ በነበረበት ችግር ምክንያት የአገር ኢኮኖሚ እግሩ ተፈትቶ መሄድ እንዳይቻል አድርጎ ነበር፤የወጪ ንግድም ትልቅ ችግር ውስጥ ነበር፤ ባለፈው አመት ለመጀመሪያ ገፊዜ መሻሻል አሳይቷል፤እነዚህን አጀንዳ ስንቀርጽ ኮቪድ … [Read more...] about “ከዚህ በኋላ ህወሓት ማለት በነፋስ የተበተነ ዱቄት ነው” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ
ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በመቀሌ ከከፍተኛ የጦር መኮንኖች ጋር ተወያዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሕግ ማስከበር ሂደቱን ከመሩ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ጋር መቀሌ ላይ ተወያይተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአካባቢው ለሕዝቡ እየተደረገ ያለው ሠብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። መቀሌ ላይ በተካሄደው ውይይት ጄኔራል አበባው ታደሰና ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ተሳትፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መሆኑን በውይይቱ ላይ ተናግረዋል። በጁንታው ላይ የተገኘው ድል የሚያኩራራ ሳይሆን 'የምንማርበትና የኢትዮጵያን ቀጣይነት የምናረጋግጥበት ነው' ማለታቸውን ኢዜአ ከስፍራው ዘግቧል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የትግራይን ክልል መልሶ ለማቋቋም መንግስት … [Read more...] about ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ፓርላማ ፊት ቀርበው ከተናገሩት
በለውጡ ዋዜማ የገጠመን መፈናቀል በሚሊዮን የሚቆጠር እንደነበርና በአንድ ጉድጓድ በርካቶችን የመቅበር ሂደት ይታይ ነበር፤ከለውጡ በፊት የአገርን ደህንነት ለማስጠበቅ የተቋቋመ ተቋም የኦነግን ባንዲራ በገፍ በማሳተምና እሱን የያዙ ሰዎችን ኢሬቻ በዓል የሚከበርበት ቦታ ውስጥ በማስገባት ሰዎችን ለማፈን ይጠቀምበት ነበር፤ ሎጎ የሌላው ባንዲራም በተመለከተ ተመሳሳይ ነው፤ይህም በስልጣን ላይ የነበረው ቡድን ዜጎችን ለማሳዘንና የተፈራው ለውጥ እንዳይመጣ ለማድረግ ነው፤ከለውጡ ጋር በተያያዘ ለውጡን በቅርበት በሚመሩት አካላት ላይ የደህንነት አስጨናቂ ክትትልና ዛቻ እንዲሁም የእስር ማዘዣ እስከማውጣት ተደርሶ ነበር - በጁንታው ስብስብ፤ከኢህአዴግ ሊቀመንበር ምርጫ ጋር በተያያዘ የፈለጉት ሰው ለማስመረጥ የጁንታው አባላት ያልፈነቀሉት ድንጋይ አልነበረም - ግን አልተሳካላቸውም፤ፍላጎቱ እኛን … [Read more...] about ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ፓርላማ ፊት ቀርበው ከተናገሩት
ኤርሚያስ ለገሰ፤ “ለምኖ ያጣ ለማኝ ተሳድቦ ይሄዳል”
የኢህአዴግ ካድሬና እያለቀሰ ስለኢህአዴግ ይሰብክ የነበረው የበረከት ስምዖን የጡት ልጅ ኤርሚያስ ለገሠን በተመለከተ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ “አልቃሻው ሚኒስትር ደኤታ” እና “የኤርምያስ ለገሰ ቪዲዮዎች ፉከራ ሲጋለጥ” በሚል ሁለት የአስተያየት ጽሁፎችን አቅርቦ ነበር። በወቅቱ እነዚህን ጽሁፎች በማተማችን ከፍተኛ ተቃውሞ ደርሶብናል። የተሰጡትንም አስተያየቶች አሁንም በጽሁፎቹ ግርጌ ማግኘት ይቻላል። ኤርምያስ ለረጅም ጊዜ እንደ ትልቅ ነገር አድርጎ ሲያወራው የነበረው ቪዲዮ የኔታ ቲዩብ ይፋ አድርጎታል። አበበ ገላው ደብቆ ያስቀመጠውና ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚናገር ትልቅ ምሥጢር የያዘ የድምጽ ቅጂ አለ በማለት ኤርምያስ ቅጂው አንዲወጣ አበበን ባደባባይ ይገዳደር ነበር። አሁን በወጣውና ኤርምያስ ምሥጢር ሲለው በነበረው ድምጽ ቅጂ ውስጥ ግለሰቡ … [Read more...] about ኤርሚያስ ለገሰ፤ “ለምኖ ያጣ ለማኝ ተሳድቦ ይሄዳል”
ዶ/ር ዐቢይ፤ ህወሃት ሚሊዮኖች ለምርጫ ከሚያባክን የውሃ ጉድጓድ ለምን አይቆፍርም?
የትግራይ ህዝብ የማይሳተፍበት የኢትዮጵያ ፖለቲካ አይኖርም❗️ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በትግርኛ ቋንቋ በነበራቸው ቆይታ፥ “በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የፌዴራል መንግስት ይሁን እኔ በበኩሌ የትግራይ ህዝብ የማይሳተፍበት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ይኖራል ብለን በፍፁም አናስብም” ብለዋል። “የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ ምስረታ ጀምሮ እስከሁን ድረስ የማይተካ ሚና እየተጫወተ ቆይቷል አሁንም እየተጫወተ ነው” ሲሉም ገልፀዋል። “ሀቁ ይህ ሆኖ ሳለ አሁን ባለንበት ወቅት ሶስት ችግሮች አሉ” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ፥ ከእነዚህም የመጀመሪያው ከለውጥ ጋር የተያያዘ ችግር ነው፣ ሁለተኛው የብልፅግና ፓርቲና ህወሐት ካላቸው ግንኙነት ጋር የተያያዘ ነው፣ ሶስተኛው ደግሞ ልዩነት ማስፋት የሚፈልጉ አካላት የሚፈጥሩት … [Read more...] about ዶ/ር ዐቢይ፤ ህወሃት ሚሊዮኖች ለምርጫ ከሚያባክን የውሃ ጉድጓድ ለምን አይቆፍርም?
ህወሃት “የመጨረሻ” ያለው ሤራ መክሸፉን መቀበል አቅቶታል
መንግሥት ህወሃትን ቀስ በቀስ ሥሩን እየቆራረጠ ቢቆይም አብዛኞች ባለመረዳትና በተገዙ ኃይሎች ውዥንብር ዕድሜው ሊራዘም እንደቻለ ለህወሃት ቅርበት ያላቸው እየገለጹ ነው። በተቀነባበረ ዕቅድ ሃጫሉ እንዲገደል ተደርጎ መንግሥትን ለመገልበጥ የታቀደውና የመጨረሻ የተባለው ሤራ መክሸፉ ህወሃት መንደር ግራ መጋባት መፍጠሩ ተስምቷል። የዐቢይ አስተዳደር እንደሚባለው ደካማ እንዳልሆነም አንዳንዶቹ በይፋ ሲናገሩ ተደምጧል። ለውጡን ተክትሎ ከህወሃት አሰልቺ የስብሰባና የግምገማ (ምይይጥ) ባህል በተቃራኒው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፍጥነት መጓዛቸውና ለህወሃቶች ከጅምሩ የማሰቢያ ጊዜ የከለከለ ነበር። የጎልጉል ታማኝ የመረጃ ምንጭ እንደሚሉት፤ የህወሃት ከፍተኛ አመራሮች ሲነጋ ልክ እንደማንኛውም ተራ ዜጋ ከፍተኛና አዳዲስ ውሳኔዎችን ይሰማሉ። በዚህም እነርሱ ለአንዱ ጉዳይ አንድ ወር ሲሰበሰቡና … [Read more...] about ህወሃት “የመጨረሻ” ያለው ሤራ መክሸፉን መቀበል አቅቶታል
“የህዳሴ ግድብ ስምምነት ፊርማ እንዲዘገይ አመራር ሰጥቻለሁ” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ
ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የተገዙ ሌት ከቀን እየደከሙ ነው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን ጨምሮ ከአደራዳሪዎቹ ጋር በስልክ ከተነጋገሩ በኋላ የህዳሴ ግድብ ስምምነት ፊርማ እንዲዘገይ አመራር መስጠታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተናገሩ። ዐቢይ ከትራምፕ ጋር በስልክ መነጋገራቸው ይፋ ከሆነ በኋላ ራሳቸውን ተንታኝ ያደረጉ ወገኖች የስምምነት ፊርማው እንዲፈረም በተደራዳሪዎች ላይ ጫና እንደፈጠሩ በመግለጽ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ሲያጠልሹዋቸው ከርመው ነበር። ዶ/ር ዐቢይ ሰኞ በተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ባደረጉት ጥያቄና መልስ እንደገለጹት የህዳሴውን ግድብ አስመልክቶ የኢትዮጵያን ጥቅም አሳልፎ መስጠትን በተመለከተ የሚደረግ አንድም ዓይነት ስምምነት እንደማይኖር አረጋግጠዋል። ከፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ከአሜሪካው የገንዘብ ሚኒስትር ስቴፈን ሙኑሺን እና ከዓለም ባንኩ ፕሬዚዳንት … [Read more...] about “የህዳሴ ግድብ ስምምነት ፊርማ እንዲዘገይ አመራር ሰጥቻለሁ” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ