ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ በአዲስ መልክ የተገነባውን የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራ መርቀው ከፍተዋል።
በተለምዶ “15 ሜዳ” ተብሎ የሚጠራው የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፋራ ከዚህ ቀደም ለስፖርታዊ እንቅስቃሴ ምቹ እንዳልነበር ተጠቁሟል፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አነሳሽነት የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ በአዲስ መልኩ ተገንበቶ በመጠናቀቁ በዛሬው ዕለት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።
የስፖርት ማዘውተሪያው ግንባታ ለስፖርታዊ እንቅስቃሴ በሚያመች መልኩ የተገነባ በመሆኑ የቀደመ አግልግሎቶቹን እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡
የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራው ግንባታ የክረምት በጎ ፈቃድ ፕሮጀክት አካል መሆኑም ተገልጿል። (አዲስ ማለዳ)
በዘመነ ት ህነግ አዲስ አበባ ውስጥ ወጣቶች ምንም ዓይነት የመዝናኛ ቦታ እንዳይኖራቸው በዕቅድ ተደርጎ እንደነበር የሚታወስ ነው። በከተማዋ የሚገኙ ኪስ ቦታዎችን ሁሉ ት ህነግ ለካድሬዎቹና ለአሽከሮቹ እየሰጠ ፎቅ እየገነቡ ኪራይ እንዲሰበስቡ፤ ሕገወጥ ብራቸውን በኪራይ ሕጋዊ ሲያደርጉ ኖረዋል።
ወጣቱም የመዝናኛ ቦታ በማጣት የሱስ፣ የሺሻ፣ የጫት፣ ወዘተ ተጠቂ ሲሆን ኖሯል። ከዚያም ሲያልፍ የድንቁርና ሰለባ እንዲሆንና አሁን ያለውን ዓይነት ካልኮረጅሁ አልፈተንም የሚል ወራዳ ትውልድ ተፈጥሯል። ወላጆችም ልጆቻችንን የት እንውሰዳቸው ሲሉ የኖሩ ሲሆን ወጣቶችም የት ሄደን እንዝናና በማለት የማያቋርጥ ጥያቄ ሲጠይቁ ኖረዋል።
ከዚህ ሁሉ አንጻር ዛሬ ተመርቆ የተከፈተው የስፖርት ሜዳ ትውልድ ከመቅረጽ አኳያ እና ት ህነግ ያፈረሰውን እሴት በመገንባት ደረጃ የሚኖረው አስተዋጽዖ እጅግ ከፍተኛ ነው። በሌሎችም ክፍለ ከተሞች ተመሳሳይ ትውልድን የሚቀርጽና ወጣቶችን ከአጉል ሱስ የሚያላቅቅ ሥራ ሊሠራ ይገባል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply