• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ፓርላማ ፊት ቀርበው ከተናገሩት

November 30, 2020 01:18 am by Editor Leave a Comment

  • በለውጡ ዋዜማ የገጠመን መፈናቀል በሚሊዮን የሚቆጠር እንደነበርና በአንድ ጉድጓድ በርካቶችን የመቅበር ሂደት ይታይ ነበር፤
  • ከለውጡ በፊት የአገርን ደህንነት ለማስጠበቅ የተቋቋመ ተቋም የኦነግን ባንዲራ በገፍ በማሳተምና እሱን የያዙ ሰዎችን ኢሬቻ በዓል የሚከበርበት ቦታ ውስጥ በማስገባት ሰዎችን ለማፈን ይጠቀምበት ነበር፤ ሎጎ የሌላው ባንዲራም በተመለከተ ተመሳሳይ ነው፤
  • ይህም በስልጣን ላይ የነበረው ቡድን ዜጎችን ለማሳዘንና የተፈራው ለውጥ እንዳይመጣ ለማድረግ  ነው፤
  • ከለውጡ ጋር  በተያያዘ ለውጡን በቅርበት በሚመሩት አካላት ላይ የደህንነት አስጨናቂ ክትትልና ዛቻ እንዲሁም የእስር ማዘዣ እስከማውጣት ተደርሶ ነበር – በጁንታው ስብስብ፤
  • ከኢህአዴግ ሊቀመንበር ምርጫ ጋር በተያያዘ የፈለጉት ሰው ለማስመረጥ የጁንታው አባላት  ያልፈነቀሉት ድንጋይ አልነበረም – ግን አልተሳካላቸውም፤
  • ፍላጎቱ እኛን በማስወገድ መንግስት ያልሆኑ ግን መንግስት የሚመስሉ ሰዎችን ማስቀመጥ ነበር፤በመቃብራችን ላይ ነው እኛው የማንፈልገው ሰው አገርን የሚመራው ሲሉ ነበር፤
  • ከለውጡ በኋላም ቢሆን በአዲስ አስተሳሰብ ቂምና ጥላቻን ትተን በይቅርታ ላይ የተመሰረተ አካሄድ ተከትለን አቃፊ አገረ  መንግስት እንገንባ የሚል ሀሳብ ለማራመድ ተሞክሯል፣
  • ይሁን እንጂ በስብከት አገር መምርት አይቻልም፣ ደካማ መንግስት ነው ያለው በሚል እሳቤው  በተፈለገው መንገድ ለውጥ ሊያመጣ አልተቻለም፤
  • ከለውጡ በኋላ በደሎቻችን ረስተን በመደመር በይቅርታ በፍቅር እንለፍ፤ የመጠፋፋት ፖለቲካ አልጠቀመንም ነው ያልነው፤
  • ቀድሞ ለምን ወደ እርምጃ አልተገባም የሚለው የኃይል አሰላለፍ ትንተና ስለሚጠይቅ ነበር፤
  • አንድን ነገረ ከማድረግ በፊት በጥንቃቄ የኃይል አሰላለፍ ትንተና ማድረግ ስለሚፈልግ ነው፤
  • መንግሥት ለመሆን ጠላትን ማወቅ፣ የራስን አቅም  ማወቅ፣ የጠላትን የማድረግ አቅምና የራስን አቅም ማወቅ ያስፈልጋል፤ ፓርቲ ነን እና ለምን በሶስት ወር ውስጥ መንግሥት አንሆንም የሚባለው የኃይል አሰላለፍ ትንተና ካለመስራት የሚመነጭ ነው፣
  • በህወሃት ጁንታ ላይ ለምን እርምጃ ቀድሞ አልተወሰደም የሚለው ከዚህ አንፃር ተገቢ አይደለም፤
  • ጠቅላይ ሚኒስትር የሆንኩኝ ሰሞን ቢሮዬን ከፍተው የሚያስገቡኝ፣ ቆልፈው የሚያወጡኝ እነሱ ነበሩ፤
  • ጠቅላይ ሚኒስትር በሆንኩ እለት የግል ጠባቂዎችን እንኳን ይዤ መግባት እንደማልችል በደህንነት ሹሙ ተነግሮኛል፤ የግል ጠባቂዎቼን እንኳን ማዘዝ አልችልም ነበር፤ እንኳንስ አገር ልመራ፤
  • የቤቴ እና የቢሮዬ ቁልፍ እንኳን በደህንነት ሰዎች እጅ ነበር፤ እንኳንስ የአገርን ደህንነት ልጠብቅ ይቅርና የልጆቼን ደህንነት እንኳን ማረጋገጥ በማልችልበት ሁኔታ ውስጥ ነበርኩ፤
  • የቢሮዬን ግቢ እንኳን ለማየት ስጠይቅ አትችልም ተብዬ ተከልክዬ ነበር፤ በወቅቱ በአጭሩ ዘመናዊ እስር ቤት ውስጥ የነበረ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆኔን ተረዳሁ፤
  • የቤቴ ዋናው ቁልፍ እነዚህ ኃይሎች እጅ ነው የነበረው፣ ማታ አስገብተው የሚቆልፉብኝ እነሱ ነበሩ፣ ጠዋት ከፍተው የሚያስወጡኝ እነሱ ነበሩ፤
  • እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳይሆን በእስር ቤት ውስጥ እንዳለ ግን ሚዲያ ላይ መቅረብ  እንደሚችል ሰው ነው የነበርኩበት ሁኔታ፤
  • የቢሮዬን ግቢ እንኳን ለማየት ስጠይቅ አትችልም ተብዬ ተከልክዬ ነበር፤ በወቅቱ በአጭሩ ዘመናዊ እስር ቤት ውስጥ የነበረ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆኔን ተረዳሁ፤
  • ሱማሌ ክልል ለመሄድ ስነሳ አልሸባብ ሊገድልህ ስለሚችል መሄድ አትችልም አለኝ የደህንነት ሹሙ፤
  • ትግራይ ሲሄድ ወጣቱ ለውጥ ፈላጊ ስለነበረ ሁሉም ተባባሪ ነበር፤
  • አምቦ ለመሄድ ስሞክር አትሂድ ኦነግ ይገድለሃል ተብያለሁ፤
  • የሚገድልኝ ኦነግና አልሸባብ ሳይሆኑ ሊገድለኝ ያሰበው በጉያዬ ያለው ኃይል መሆኑ ስለገባኝ ተጨማሪ ጥበቃ አድርገን አምቦ ሄድን፤
  • የሃጫሉ ሙዚቃ እንዴት በቴሌቪዥን ተላለፈ ብለው በግምገማ ቁምስቅላችንን ያሳዩን ሰዎች  የኦሮሞ ታጋይ ሞተ ብለው በቴሌቪዥናቸው አስተላለፉ፤
  • በእያንዳንዱ ሳምንት የጦርነት ድግስ ነበር፣ መንግስት ስራ እንዳይሰራ በየቦታው ችግር ይፈጠር ነበር፣ 113 የሚሆኑ ግጭቶች ተፈጥረዋል፤
  • የብሔር፣ የሃይማኖት ግጭት እንዲነሳ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፤
  • አንድ ጎጃሜ ከጎጃም ወደ አምቦ ሲሄድ ወገኔ ነው ብሎ ነው የሚሄደው፣ ይህ ህዝብ በጥርጣሬ እንዲተያይ ነው ለማድረግ የሞከሩት፤
  • ባለፉት ሁለት ዓመት ተኩል በኦሮሚያ ውስጥ 37 ግጭቶች ነበሩ፤
  • ባለፉት ሁለት ዓመት ተኩል በአማራ ክልል 23 ግጭቶች ነበሩ፤
  • በቤንሻንጉል ጉሙዝ 15 ግጭቶች ተከስተዋል፤
  • አዲስ አበባ ላይ 14 ግጭቶች ተከስተው ነበር፤
  • የሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያን በተመለከተ ከሃጫሉ በተጨማሪ ሌሎች የኦሮሞና የአማራ አመራሮችን በመግደል ግጭቱን የኦሮሞና የአማራ ለማስመሰል ጥረት ተደርጓል፤
  • ከዚያ በኋላ ሃጫሉን አጥተናል እና ሌሎች ጉዳቶች እንዳይደርሱ ስራዎች ተሰርተዋል፤
  • በጋምቤላ 7 ግጭቶች ነበሩ፤
  • በሚዛን ቴፒ፣ ጉራፈርዳ ግጭቶች ተከስቷል፤
  • ጉጂና ጌዲዮ እንደ አንድ ቤተሰብ የሚኖር ህዝብ ሲሆን፣ እዚያ አካባቢ ሰዎች እንዲፈናቀሉ ተደርጓል፤
  • አማራ ክልል፣ ቤኒሻንጉል ያዋስነዋል ተጋጭቷል፣ ኦሮሚያ ያዋስነዋል ተጋጭቷል፣ አፋር ያዋስኗል ተጋጭቷል፣ ትግራይ ያዋስነዋል ነገር ግን አልተጋጨም፤
  • ሌሎች ክልሎችም ከጎረቤት ክልሎች ጋር እንዲጋጩ ተደርጓል፣ ትግራይ ክልል ጎረቤት ክልል ቢሆንም ከትግራይ ግን አለመጋጨታቸው ግጭቱ ታስቦበት የሚሰራ በመሆኑ ነው፤
  • አሁን ላይ በሰሜን እዝ ላይ የደረሰው ጥቃት እንዴት ተፈፀመ የሚለውን ጥያቄ በመመለስ ሂደት  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የመከላከያ  ሠራዊትን  አገነባብ በለውጡ ማግስት ምን ይመስል እንደነበር በዝርዝር ለፓርላማ ካቀረቡት ሀሳብ የሚከተሉትን አሃዛዊ መረጃዎችን አቅርበዋል፤
  • የመከላከያ ሠራዊት የተገነባበት ርዕዮት ከህገ መንግስቱ ጋር 100 ፐርሰንት የሚቃረን የአንድ ፓርቲን ርዕዮት ለማስጠብቅ ያለመ ነበር፤
  • ባለ አራት ኮኮብ ጀነራል 60 በመቶው ከአንድ ቡድን ነበር – (ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ከአንድ ቡድን” በማለት የጠቀሱት ከትግራይ መሆኑን ልብ ይሏል)፣
  • ከሌሎች የአገሪቱ  ህዘቦች ደግሞ የነበረው ስብጥር 40 በመቶ ብቻ፤
  • ሌተናንት ጀነራል 50 በመቶ ከአንድ ቡድን፤
  • ሜጀር ጀነራል 45 በመቶ ከአንድ አካባቢ፤
  • ብርጋዴር 40 በመቶ ጄነራል ከአንድ አካባቢ፤
  • ኮሌኔል 58 በመቶ ከአንድ አካባቢ፤
  • ሌተናል ኮሎኔል 66 በመቶው ከአንድ አካባቢ፤
  • ሻለቃ 53 በመቶ ከአንድ አካባቢ፤
  • ከጄነራል እስከ ሻለቃ ድረስ በአማካይ ሲታይ 55 በመቶው ከአንድ ክልል ብቻ ነበር ስብጥሩ
  • የመከላከያን ስብጥር ለማስጠበቅ በወቅቱ በነበረው ሁኔታ ማሰብ እንዳይቻል ተደርጎ የአንድ  ቡድንን የበላይነት ለማረጋገጥ ታልሞ የተሠራ ነው እንጂ ቢያንስ በታችኛው የወታደራዊ እርከኖች ከሌሎች አካባቢዎች የመጡ መኮንኖችን ማፍራት ይቻል ነበር፤
  • ኢትዮጵያ በነበሯት ሁሉም ዕዞች ይመሩ የነበሩት ዋና እና ምክትል ከአንድ ቡድን ወገን ነበሩ
  • ከዚህ በተለየ በሰሜን እዝ ላይ ዋና እና ምክትል አዛዥ፣ ሎጂስቲክ፣ አስተዳደርን የሚመሩት ሁሉም ከህወሓት ቡድን ነበር፤
  • ከእዝ በመለስ የመካናይዝድ ክፍለ ጦራችን በሙሉ 100 በመቶ እና የእግረኛ ክፍለ ጦሮችን 80 በመቶ የሚመሩት በዚሁ በአንድ ቡድን ነበር፤
  • ከወታደራዊ መለዮ ለባሾች ባሻገር የመከላከያ  ሚኒስቴር መስሪያ ቤት 80 በመቶው ተይዞ የነበረው በአንድ ቡድን ነበር፤
  • ሁሉም ክልል በሚገባው የህዝብ ቁጥር ልክ መወከል አለበት እንጂ ከሚገባው በላይ እንዲኖረው መደረጉ አሁን ላይ የደረስንበትን ችግር ፈጥሯል፤
  • የመከላከያ ከአንድ አከባቢ መሆን ለትግራይም ህዝብም ሆነ ለመላ የአገሪቱ ህዝቦች አይጠቅምም፣ የመከላከያ አመራሮች ከአንድ አከባቢ መሆን አሁን የተፈጠረው ዓይነት ችግርን ይፈጥራል፣
  • እነዚህን  ነባራዊ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት በትንሹም ቢሆን ለመቀየር እና ኢትዮጵያን የሚመስል መከላከያ ለማዋቀር ጅምር ስራዎች ተደርገዋል፤
  • በህወሃት ጁንታ ላይ የተደረገውን ዘመቻ በተመለከተ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳይ ሳይደርስ በሶስት ሳምንት ውስጥ ቁጥጥር ስር መዋል ተችሏል፤
  • ይህ የሆነው የመከላከያ ሰራዊቱ በጣም ዲሲፕሊን ያለው ጀግና ወታደር ስለሆነ ነው፤
  • መካናይዝድ ኦፕሬሽን ለመስራት ያልተቻለው ከገንዘብ ጋር የተያያዘ ነው፤
  • በርካታ ሮኬቶች አሉን፣ ነገር ግን በትግራይ አንድም ሮኬት አልተተኮሰም፤ በኃላፊነት ስሜት ነው ኦፕሬሽኑ የተሰራው፣
  • መቀሌን አፈረሱ ለሚሉ አካላት፣ እኛ የራሳችን የሆነን ነገር እንደ ጁንታው አናወድምም፤
  • የአገሪቱ አቅም ሰሜን እዝ ላይ እንዲሆን ሆን ተብሎ አስቀድሞ የህወሃት ቡድን ስራ ሰርቷል፤
  • ጥቅምት 24 ግልገል ጁንታ የሰሜን እዝ ማብራት በጣጥሶ፣ ወታደሩ እንዳይገናኝ ኮሚዩኒኬሽን አቋርጠው፣ ብዙዎችን ገድለው ብዙዎችን አፍነው፣ በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ አጉል ስራ ነው የሰሩት፤
  • ኢትዮጵያ ያደረገችውን ሕግ የማስከበር ስራ ድጋፍ ስላደረጉልን ለኤርትራ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ አገራት ምስጋና እና ክብር ይገባቸዋል፤
  • በሰሜን እዝ ላይ በደረሰው ጥቃት ራቁታቸውን ወደ ኤርትራ የሄዱ ሰዎች በኤርትራውያን የሚለበስ ልብስ አግኝተዋል፤
  • የክልሉ መሪዎች እየወጡ ሰሜን እዝ ከእኛ ጋር ሆኗል ሲሉ ነበር፣ ሰሜን እዝ ከእነሱ ጋር ከሆነ ምንም ንግግር አያስፈልግም ነበር፤ ምክንያቱም ከፍተኛ ወታደራዊ ቁሳቁስና የሰው     ኃይል ስለነበር፤
  • ሽረ አከባቢ በነበረው ካምፕም የሌሎች ብሔረሰብ አባላትን ወታደሮች አፍነው ወስደዋል፤
  • ከጥቃቱ  በፊት የሰሜን እዝ አዛዥ ጄኔራል ድሪባ ከእነሱ ጋር ምሳ ከበላ በኋላ ራሱን ይስታል፣ ጄኔራል ድሪባ እስከ ዛሬ ስራ መስራት የሚያስችል አቋም ላይ አይደለም፤
  • ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ የትግራይ ህዝብ ለመከላከያ ከፍተኛ ድጋፍ አድርገዋል፤
  • ባለፉት ሁለት ሶስት ሳምንታት ውስጥ ከሕጋዊ የትግራይ አስተዳደሮች ጋር ድርድር ሲደረግ ነበር፤
  • ከወንጀለኛ ጋር ግን ድርድር የሚባል ነገር የለም፤
  • ጁንታው ተሰባስቦ ከመቀሌ ወጥቶ ወደ ሀገረ ሰላም (ደጋ ተንቤን) ሸሽቷል፤
  • የአየር ኃይል ድሮኖች የ24 ሰዓት ክትትል እያደረጉ ነው፤
  • ትላንት ማታ በካምፑ የተፈጠረውን ውዝግብ ቁጭ ብለን ስንከታተል ነበር፤
  • እርምጃ መውሰድ ቢቻልም ሚስቶቻቸው እና ልጆቻቸው እና የታፈኑ የኛ ስራዊት አባላት ስለነበሩ ትተናቸዋል፤
  • ይሄ ምህረት ነገ አይደገመም።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Middle Column, News Tagged With: abiy ahmed, operation dismantle tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule