• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ለዶሮ በሽታ በሬ ማረድ ትክክል አይደለም” ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ

July 7, 2021 07:32 pm by Editor 1 Comment

አንዳንዶች ከሁለት አሥርት ዓመታት በላይ በቆዩበት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልነት የመጨረሻ ዘመንና የመጨረሻው ሳምንት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር ሰኔ 28 ቀን 2013. ዓ.ም. በነበራቸው ጥያቄና መልስ፣ በአገሪቱ ታሪክ ከፍተኛ የተባለውን 561 ቢሊዮን ብር የ2014 ዓመታዊ በጀት እንዲሆን የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ በሙሉ ድምፅ በማፅደቅ የመጨረሻ የውሳኔ አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡

በዕለቱ ከፍተኛ የአገሪቱ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች፣ የግሉ ዘርፍ ተወካዮችና ሌሎችም አካላት በተገኙበት በዚሁ የፓርላማው ስድስተኛ ዓመት አራተኛ ልዩ ስብሰባ በወቅታዊ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ያመዘኑ በርከት ያሉ ጥያቄዎች ከ15 የምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀርበውላቸው ነበር፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምክር ቤቱን በአገር ደረጃ የመንግሥት ለውጥ ተደርጎ ብዙ ፈተናና ችግር በተከሰተበት ጊዜ በታላቅ የኃላፊነት ስሜት ከፖለቲካ አባላት ከሚጠበቅና ከሚታመን በላይ ራሱን ማሳየት የቻለ፣ አገር ያሻገረ፣ የሕግ አወጣጥ ሥርዓቱን በብቃት የመራ ስለሆነ በዚህ የመጨረሻ መድረክ ላይ በአስፈጻሚውና በኢትዮጵያ ስም ከፍተኛ ምሥጋና አቀርባለሁ ብለዋል፡፡

የትግራይ ክልል አሁናዊ ሁኔታ ምን እንደሚመስልና ክልሉን መልሶ ወደ ተረጋጋ ሁኔታ ለመመለስ ምን እየተሠራ እንደሆነ አቶ ዘውዱ ከበደ ከተባሉ የምክር ቤት አባል ለጠቅላይ ማኒስትሩ ጥያቄ ቀርቦ ነበር፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለትግራይ ክልል ሲናገሩ የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ኃይሎች በክልሉ የሕግ ማስከበር ዘመቻ ከመጀመሩ በፊት፣ ቅጥረኞችን በማሰማራት በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ሕዝቡን እያመሱና እያገዳደሉ ግጭትን ሲያባዙ እንደነበር ገልጸዋል፡፡

በዚህም ‹እኛ ብንኖር አገሪቱ አትበጣበጥም እኛ እንምጣልህ በማለት፣ የስላቅ ክፋቱ እኛ ብቻ ነን ሰላማዊ ክልል ማለታቸው ነው› ብለዋል፡፡

“ይህ ሁሉ እንደተጠበቀ ሆኖ ያም አልበቃ ብሎ የትግራይ ሕዝብን ጋሻ መከታ ሆኖ ለበርካታ ዓመታት ሲጠብቅ የኖረ፣ እኔም ሦስትና አራት ዓመታት ልጅነቴንና ትምህርቴን ትቼ የኖርኩበት፣ በጣም ትንሹ የወንድሜ ልጅ የሞተበት፣ ብዙዎችን የገበርንበት ያ ሠራዊት ለሠራው ውለታ እንኳ ሲባል ቢያንስ ጡት እስከ መቁረጥ ድረስ መሄድ አልነበረባቸውም፤” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

በዚህ ግልጽ አደጋ የፌዴራል መንግሥት ሳይፈልግ በግድ አገሩን እንዲከላከል፣ እንዲሁም የተቀማውን የአገር ሀብት መሣሪያ ለማስመለስ ተገዶ ወደ ግጭት መግባቱን አስታውሰዋል፡፡

“በብዙ ሽምግልና ችግሩን ለመፍታት ቢከብድም ለሕወሓት እንደማይጠቅመው ተለምኖም የእብሪቱ ብዛት ልክ አልነበረውም፡፡ ነገር ግን ውጊያው ሲከፈት የፌዴራል መንግሥት በግጭቱ ወቅት ጥፋተኛው ላይ ብቻ አነጣጥሯል፤” ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም በሕግ ማስከበር ዘመቻው በከተሞች ላይ ጥቃት እንዳይደርስ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረጉንና ውጊያው ከተሞች ውስጥ እንዳይገባ የተደረገው ሙከራ፣ በታሪክ ውስጥ የኢትዮጵያን መከላከያ ሠራዊትና መንግሥት በጉልህ የሞራል ልዕልና የሚያስቀምጥ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት የፌዴራል መንግሥት ይህን ሁሉ ጣጣ ያመጣውን የሕውሓትን ኃይል ያሰረበትን እስር ቤት አስመልክቶ፣ “እጅግ ዘመናዊና ዴሞክራሲያዊ በሚባል አገር በሚደረግበት ልክ በነፃነት መቀለብ እንጂ አስረናልና እንግረፍ አላልንም፣ ገርፋችኋልና መገረፍን እዩት ሳይሆን በሕግ እንዲጠየቁ እየተደረገ ነው፤” በማለት ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ለትግራይ ሕዝብ የፌዴራል መንግሥት ያለ የሌለ ሀብቱን አፍስሶ ከማንም አገር በላይ ዕርዳታ ማቅረቡንና የመንግሥት አገልግሎትን ለማስጀመር በርካታ ሥራ መከናወኑን አስረድተዋል፡፡

በክልሉ መሠረተ ልማቶችንና አገልግሎቶችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ያፈሰሰውን 100 ቢሊዮን ብር ሌላ ነገር ላይ ቢያውል ብዙ ነገር መሸፈን እንደሚችል በመጥቀስ፣ ነገር ግን በክልሉ የነበረውን ቀውስ ማርገብ ይሻላል በሚል የተካሄደ ሙከራ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

የፌዴራል መንግሥት ይህን ሁሉ አድርጎ ምን ተገኘ ለሚለው መልስ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ “ለችግሩ ግንባር ቀደም የነበሩ ሐሳብ አመንጪዎች ዕርምጃ ተወስዶባቸዋል፣ የተቀሩትም ዳግም እንዲህ ዓይነት ተግባር ላይ እንዳይሰማሩ ሆነዋል፡፡ ሰሜን ዕዝ ነፃ ወጥቷል፣ ትጥቅ ተመልሷል፡፡ ጎንደር፣ ባህር ዳር ወይም አስመራ የሚተኮሰው ሚሳይል ተመልሷል፡፡ ከሁሉ በላይ መከላከያ ሠራዊት አገራዊና ጠንካራ ቁመና ይዞ እንዲገነባ በምንም መንገድ የማይገኝ መልካም ዕድልና ልምድ ተገኝቶበታል፤” ብለዋል፡፡

በአፍጋኒስታን፣ በየመን፣ በሶሪያ፣ በሊቢያና በመሳሰሉ አገሮች የገጠማቸውን መሰል ግጭቶች፣ እንዲሁም ጃፓንና ኮሪያ ገብተውበት የነበረውን ሁኔታ ለመፍታት የሄዱበትን ጥረትና ውሳኔ ለማየት ተሞክሮ መጨረሻ ላይ ‹ለዶሮ በሽታ በሬ ማረድ ትክክል አይደለም› የሚለው አባባል አስገዳጅ ሆኖ እንደመጣ ተናግረዋል፡፡

‹ዶሮ ታሞ በሬ የሚታረድበት ምክንያት ስለሌለና ተገደን በገባንበት ባሻን ሰዓት ማቆም ስለምንችል ማቆም ያስፈልጋል፣ ጥሞና ያስፈልጋል፣ ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡ በዚህም ከበሽታው ልክ በላይ መድከምና ጊዜ ማባከን ተገቢ ባለመሆኑ፣ እኛንም ሌላውንም ያስተምራል በሚልና በተለይም ‹ምስኪን› የአፍሪካ አገሮችም ከጉዳዩ መማር ከፈለጉ ሊማሩበት እንደሚችሉ የታሰበበት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የፌዴራል መንግሥት ከትግራይ ክልል ለመውጣት ውሳኔ ላይ የደረሰው ከአንድ ወር በፊት ከተለያዩ አካላት ጋር ተወያይቶ ቀድሞ በወሰነው ውሳኔ መሰረት ሆኖ ሳለ፣ አሁን በአንዳንዶች ፌዴራል መንግሥት ተሸንፎ ከትግራይ ክልል ወጥቷል እንደሚባለው አለመሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ጦርነት ይቀጥል ከተባለ አሥርና ሃያ ዓመታት ማስቀጠል ይቻላል ብለዋል፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ ውስጥ በአምስትና በአሥር ዓመት ዕድገት ማምጣት እንደማይቻል ግን አስረድተዋል፡፡

በመሆኑም መንግሥት ከትግራይ ክልል ሠራዊቱን ማስወጣት የጀመረው እንደሚባለው ከአንድ ሳምንት በፊት ሳይሆን፣ በአራት ዙር ካለፈው አንድ ወር ጀምሮ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አረጋግጠዋል፡፡

መንግሥት እዚህ ውሳኔ የደረሰበት ዋነኛ ምክንያት ፕሮጀክቶችን ለመጨረስ፣ ከስደት ተመላሽ ዜጎች መብዛት፣ የግብርና ሥራው እዚያም እዚህም መጀመር ስላለበት፣ የጥሞና ጊዜ ስለሚያስፈልግና ሕዝቡም ይየው በሚል መሆኑን አክለው ተናግረዋል፡፡

“መንግሥት መቀየር አለበት፣ አሁን ያለው መንግሥት አይመችም የሚሉ ሙከራ የሚያደርጉ አገሮች እንዳሉ እናውቃለን፡፡ ነገር ግን ለእነዚህ አገሮች ኢትዮጵያ እስከፀናችና እስከቆመች ድረስ እዚህ ያሉ ሰዎች ሥልጣን ላይ መቆየት ሁለተኛ ጉዳይ ነው፤” ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግጭቱ ወቅት የደረሰውን ኪሳራ እያንዳንዱ የትግራይ ሕዝብ ቆም ብሎ ሊያይ ይገባል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

የትግራይ እናቶች የደረሰባቸውን ነገር እንደሚያውቁት በመጥቀስ፣ ጉዳዬ ልክ የእስራኤል ሕዝብ የሚያልፍበትን መከራ ሁሉ አልፎ ከግብፅ በወጣበት ጊዜ እስከ ቀይ ባህር የተከተለውን የፈርኦንን መንግሥት የሚያስታውስ ነው በማለት ገልጸውታል፡፡

የትግራይ ክልል ሁኔታ የእስራኤልን ሕዝብ ከመከተል አርፎ በካይሮ ግብፅ መቀመጥ ሲገባው ቀይ ባህር ድረስ ተከትሎ እንደተዋጠው ፈርኦን ክስተት መሆኑን በመግለጽ፣ አሁንም ቆም ብሎ ማየት እንደሚያስፈልግና በዚህ ዓይነት እንቢተኝነት ኢትዮጵያን ማሸነፍ እንደማይቻል ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም፣ “ዝም ብሎ መከተል ጥሩ አይደለም፣ ፈረስ ጋሪን የሚያስከትለው ጋሪ ስለማያስብ ብቻ ሳይሆን ፈረስ ዙሪያውን እንዳያይ ዓይኑን ተሸፍኖ ስለሆነ ነው፤” ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአገሪቱን ውጭ ጉዳይ ፖሊስ አስመልክቶ በዓለም አሁን ባለው ተለዋዋጭ ሁኔታ፣ የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ መፈተሽ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል የውጭ ጉዳይ ተቋም መፈተሽና መታደስ እንደሚያስፈልገው በመግለጽ፣ አሁን “በተለያዩ አገሮች ያሉ 60 ያህል ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት ሁኔታ ያስፈልጋታል ብዬ አላስብም፣ በዚህም ቢያንስ ግማሹ መቀነስ አለበት፤” ብለዋል፡፡

“የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን በተመለከተ በጣም ብዙ ነገሮች ይነገራሉ፡፡ ነገር ግን ግድቡ የኢትዮጵያን የመብራት ጥያቄ በመመለስ፣ የሱዳንና የግብፅን ሥጋት እንዲቀንስ፣ በቀጣናው ሰላምና ብልፅግናን እንዲያመጣና ኢነርጂው ቢመረት በጋራ የምንጠቀምበት ውኃም ችግር ካለ እየተወያየን የምንፈታበት ሰላማዊ የልማት ጉዞ እንዲሆን እንፈልጋለን፤” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን አስመልክተው ማብራሪያ ሲሰጡ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ኮቪድ-19፣ የበረሃ አንበጣ፣ ግጭት፣ የፕሮጀክቶች መጓተት፣ የዋጋ ግሽበት፣ ከውጭ አገር ዜጎች በገፍ መመለስ ጋር ተደምሮ ኢኮኖሚው ላይ ጫና ቢፈጠርም የ2013 ኢኮኖሚ ዕድገት በ2011 ዓ.ም. ከነበረው የዘጠኝ በመቶ ኢኮኖሚ ዕድገት ጋር ተቀራራቢ መሆኑን፣ ከ2012 ዓ.ም. ከፍ ያለ ዕድገት ለማስመዝገብ አመላካች ሁኔታዎች አሉ ብለዋል፡፡

በ2013 ዓ.ም. ባልተለመደ ሁኔታ በተለይም በበጋ ስንዴ ምርት ከ15 ሚሊዮን በላይ ኩንታል መመረቱን፣ አንድ ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ቡና ለውጪ ገበያ መላኩን፣ አትክልትና ፍራፍሬ በተለይም አቮካዶና ፓፓያ በተሻለ መጠን ማምረት መጀመሩ፣ ከማዕድን ግማሽ ቢሊዮን ዶላር በላይ ለውጭ ገበያ ማቅረብ መቻሉና መሻሻል የታየበት እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

በፋይናንስ ዘርፉ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ባንኮች የሚዘዋወረው ገንዘብ ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ እንደ ደረሰ፣ የባንኮች አጠቃላይ ሀብት 1.9 ትሪሊዮን ብር መድረሱን ይበል የሚያሰኝ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሞካሽተዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ የብር ኖት መቀየርን ተከትሎ ባንኮች በ2011 ዓ.ም. ከነበረው 38.8 ሚሊዮን ደንበኞች፣ በ2013 ዓ.ም. ወደ 66.2 ሚሊዮን ደንበኞች መድረሱንና የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች ስድስት ቢሊዮን እንደ ደረሰ አስታውቀዋል፡፡

በወጪና በገቢ ንግድ መካከል በ2011 ዓ.ም. የነበረው ልዩነት 11.7 በመቶ መሆኑን፣ በ2013 ዓ.ም. 9.3 በመቶ እንደ ደረሰ አክለው ተናግረዋል፡፡

በኮንስትራክሽን ዘርፉ እየታየ የሲሚንቶ ምርት እጥረት መኖሩን፣ የፕሮጀክቶች የህዳሴ ግድብን ጨምሮ መብዛትና የማምረቻ ፋብሪካዎች በተለያዩ መንገዶች የማምረት አቅም መቀነሱን አመላክተዋል፡፡

በዚህም እጥረቱን ለመግታት የውጭ ባለሀብቶች አገር ውስጥ ገብተው ማምረት እንዲችሉ፣ አሁን ያሉትን ፋብሪካዎች አቅም በእጥፍ ሊያሳድግ የሚችሉ የውጭ ኩባንያዎች ወደ ሥራ ገብተው በአንድ ዓመት ውስጥ ችግሩን ለማቃለል እየተሠራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

እየተጠናቀቀ ባለው የበጀት ዓመት ኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ ለውጭ ከተላከ የአገር ውስጥ ምርት 3.5 ቢሊዮን ዶላር እንዳገኘች ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል፡፡

የአገሪቱ የውጭ ብድር ዕዳ ጫና ከነበረበት 37 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ በ2013 ዓ.ም. ወደ 27 ቢሊዮን ዶላር ዝቅ እንዳለ በመጥቀስ፣ ከአጠቃላይ ዕዳውና ዕዳው ከሚከፈልበት ጊዜ አንጻር ሲሰላ የመቀነስ አዝማሚያ እንዳለውና ይህም በዋነኝነት ዕዳ ለማቅለል ከወዳጅ አገሮች ጋር በተሠራው ሥራና ኮሜርሻል ብድር በመቆሙ ምክንያት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በ2013 ዓ.ም. ካለፈው ዓመት በ20 በመቶ በማደግ 2.7 ቢሊዮን ዶላር ወደ ብሔራዊ ባንክ መግባቱን ጠቁመዋል፡፡

 በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ባንኮች ከ2011 ዓ.ም. ከነበረው ብድር የ20 በመቶ ብልጫ ያለው ብድር ያቀረቡ መሆኑን፣ የብድሩ ምጣኔ 74 በመቶ ለግሉ ዘርፍና 25 በመቶ ለመንግሥት የተሰጠ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በግል ባንኮች ላይ ከተቀመጠው አጠቃላይ ገንዘብ 92 በመቶ የኢትዮጵያ ሕዝብ የቆጠበው መሆኑን፣ የባለአክሲዮኖች ገንዘብ ደግሞ 144 ቢሊዮን ብር ወይም ከአጠቃላይ ገንዘቡ ስምንት በመቶ ብቻ ሆኖ ሳለ ባንኮች ከሕዝቡ የሰበሰቡትን ገንዘብ ለቆጠበው የኢትዮጵያ አርሶ አደር መልሶ እንዲያለማበት ዕድል የማይመቻቹት ከሆነ፣ ይህ ገንዘብ ተሰብስቦ የት እንደሚገባ መልሶ መፈተሽ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡

ለኑሮ ውድነቱና ለዋጋ ግሽበቱ በዋነኝነት የዓለም የሸቀጦች ዋጋ መጨመር፣ በትግራይ ክልል የተከሰተው ቀውስ፣ ምርት እያለ በአቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ የተፈጠረ የንግድ ሳንካ መብዛትና የአምራቾች ምርትን መደበቅ እንደ ምክንያት ተጠቅሰዋል፡፡

 መንግሥት የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር የገበያ ማዕከላት ግንባታ፣ የግሉ ዘርፍ በፍራንኮ ቫሉታ ያለ ቀረጥ ምግብ ነክ ሸቀጦችን እንዲያስገቡ መደረጉን፣ መንግሥት ምግብ ነክ ሸቀጦችን በርካታ ቢሊዮን ብር መድቦ ማስገባቱን፣ ለኅብረት ሥራ ማኅበራት ተጨማሪ ግማሽ ቢሊዮን ብር በመመደብ ሸቀጦችን እንዲያከፋፍሉ በማድረግ መንግሥት ችግሩን ለማቃለል መሥራቱን ተናግረዋል፡፡

በ2014 በጀት ዓመት ገበያን ሆን ብለው በሚያውኩ አካላት ላይ ጠንካራ ዕርምጃ በመውሰድና የገንዘብ ፖሊሲን በማስተካከል፣ የዋጋ ግሽበቱን ለመቆጣጠር ጥረት ይደረጋል ብለዋል፡፡

በ2013 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ከተገነቡት የዳቦ ማምረቻ ፋብሪካዎች በተጨማሪ በ2014 በጀት ዓመት በአሥር ከተሞች ለአብነትም በጎንደር፣ በደሴ፣ በነቀምትና በሶዶ፣ ወዘተ ከተሞች ግንባታዎች ለማካሄድ ከሚድሮክ ኩባንያ ባለቤት ሼክ ሁሴን አል አሙዲ፣ እንዲሁም ማገዝ ከሚፈልጉ የውጭ አገሮች ጋር አብሮ ለመሥራት መንግሥት መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡ (ሲሳይ ሳህሉ-ሪፖርተር)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Middle Column, News, Politics Tagged With: abiy ahmed, ethiopian terrorists, operation dismantle tplf, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. ቆምጬ አምባው says

    July 13, 2021 02:34 pm at 2:34 pm

    Talk of phone analysis – here is one by his execellency

    “ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግጭቱ ወቅት የደረሰውን ኪሳራ እያንዳንዱ የትግራይ ሕዝብ ቆም ብሎ ሊያይ ይገባል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

    የትግራይ እናቶች የደረሰባቸውን ነገር እንደሚያውቁት በመጥቀስ፣ ጉዳዬ ልክ የእስራኤል ሕዝብ የሚያልፍበትን መከራ ሁሉ አልፎ ከግብፅ በወጣበት ጊዜ እስከ ቀይ ባህር የተከተለውን የፈርኦንን መንግሥት የሚያስታውስ ነው በማለት ገልጸውታል፡፡

    የትግራይ ክልል ሁኔታ የእስራኤልን ሕዝብ ከመከተል አርፎ በካይሮ ግብፅ መቀመጥ ሲገባው ቀይ ባህር ድረስ ተከትሎ እንደተዋጠው ፈርኦን ክስተት መሆኑን በመግለጽ፣ አሁንም ቆም ብሎ ማየት እንደሚያስፈልግና በዚህ ዓይነት እንቢተኝነት ኢትዮጵያን ማሸነፍ እንደማይቻል ተናግረዋል፡፡

    ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም፣ “ዝም ብሎ መከተል ጥሩ አይደለም፣ ፈረስ ጋሪን የሚያስከትለው ጋሪ ስለማያስብ ብቻ ሳይሆን ፈረስ ዙሪያውን እንዳያይ ዓይኑን ተሸፍኖ ስለሆነ ነው፤” ብለዋል፡፡”

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm
  • አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን March 15, 2023 08:52 am
  • ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ March 15, 2023 08:48 am
  • በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ March 15, 2023 01:43 am
  • ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ March 15, 2023 12:52 am
  • አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች  March 10, 2023 10:45 pm
  • ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ March 2, 2023 09:56 am
  • በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ? March 2, 2023 09:43 am
  • አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት February 24, 2023 10:44 am
  • በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል February 24, 2023 08:39 am
  • የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ! February 24, 2023 08:19 am
  • “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ February 21, 2023 10:09 am
  • አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ February 21, 2023 10:01 am
  • በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት February 17, 2023 06:39 pm
  • ኦነግ ሸኔ አሸባሪነቱ ሳይነሳለት በሽመልስ የሰላምና የእርቅ ጥሪ “በክብር” ቀረበለት February 17, 2023 12:35 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule