• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“በኢትዮጵያ ክብርና ጥቅም ከመጣችሁ አንገቴ ይቀላል እንጂ አልደራደርም”

March 24, 2021 01:22 am by Editor 2 Comments

“ተላላኪ መንግስት አይኖርም” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ለበርካታ ዓመታት የነጮ ተላላኪ በመሆን ያገለገለው እና ሞት እንደ ቡሽ ክዳን ያስፈነጠረው መለስ ዜናዊ በግፍ ኢትዮጵያን በገዛበትና ከዚያ በኋላ ባሉት ዓመታት ፈጽሞ ባልተሰማ ሁኔታ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለአገራቸው ያላቸውን ስሜት በግልጽ ተናግረዋል። ኢትዮጵያን ተቀጥሮ እንደሚያስተዳድራት መሪ “አገሪቱ” እያለ ሲጠራት ከኖረው መለስ ዜናዊ በኋላ ፍጹም በተጻረረና ልብን በሚያሞቅ የአገር ስሜትና ወኔ ከእንግዲህ በኢትዮያ ተላላኪ መንግሥት እንደማይኖር ነው ለሕዝባቸው በፓርላማው ውይይት የተናገሩት።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ “በኢትዮጵያ ክብርና ጥቅም ከመጣችሁ አንገቴ ይቀላል እንጂ አይደረግም” ሲሉ ተጽዕኖ ለማሳደር ለሚሞክሩ አካላት ተናግረዋል። ዛሬ (ማክሰኞ) ለፓርላማ ባቀረቡት ንግግር ኢትዮጵያ ራስዋን ለማበልጸግ ከማናቸውም አካላት ጋር እንደምትሠራ ካስታወቁ በኋላ ነው “ከመበልጸግ የሚጠመዝዙን አንቀበልም” ሲሉ ነው ያስታወቁት።

በምንም ምክንያት በኢትዮጵያ ተላላኪ መንግሥት እንደማይፈጠር ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህዝብ እንዲተባበር ጥሪ አቅርበዋል። የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም ወጣቱ የኢትዮጵያን የህግ አስከባሪ ሃይል በመቀላቀል የዜግነት ድርሻውን እንዲወጣ አደራ ብለዋል። ከፌስቡክ ፉከራ የዘለለ ውሳኔ እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል።

ጠላት፣ ወዳጅና እጅ ጠምዛዥ አገራት እንዳሉ ያስታወቁት ዐቢይ አህመድ፣ ጥላ እንኳን በማታ ሲሸሽ፣ ጨለማ ባጋጠመን ወቅት የኤርትራ መንግሥትና ሕዝብ ያደረገልን ውለታ በታሪክ የማይዘነጋ መሆኑ አመልክተዋል። አያይዘውም ለዚህ ውለታ ልዩ ክብር እንደሚሰጥ ካስታወቁ በኋላ “እንዲህ ላደረገለን ህዝብና መንግሥት ስድብ እንድንመልስ የሚጠብቁ የዋሆች ናቸው” ሲል በግልጽ አመስግነዋል። ተፈጠሩ የተባሉ ችግሮችን ለመፍታት ውይይት እየተደረገ መሆኑንንም አመልክተዋል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Middle Column, News, Politics Tagged With: abiy ahmed

Reader Interactions

Comments

  1. ነፃ ሕዝብ says

    March 24, 2021 05:38 am at 5:38 am

    “ተላላኪ መንግስት አይኖርም” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ :- አንተ ምን የማትለው አለ ብለህ ነው ፥ Confused and convinced ያለንን የአንተን ተላላኪና ጉዳይ አስፈፃሚ ሽመልስ አብዲሳን መቼ እንረሳለን ፥ አብይ አህመድ አሊን የሚያምን ህይወት የሌለው በድን ብቻ ነው ፥ እንደ ንግግሩማ ቢሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ 100% አምነነው ተቀብለነው ነበር ፥ የአብይን ሃይማኖትም ሆነ ብ/ሰብ የተመለከተ ማንም ኢትዮጵያዊ አልነበረም ፥ እኛ የምናማርረው ወይም አጥብቀን የምንጠላው ከአብይ በተጨማሪ ጠ/ሚ/ር ተብሎ ሲሾም ያነበበልንን የፃፈለትን ሰው ነው ፥ የኢትዮጵያን ሕዝብ እንዲታለል አድርጎታል ፥ አብይን ማመን ቀብሮ እንጂ በህይወት እያለ ማመን በፍጹም አይቻልም ፥ የሚናገረውና በተግባር የሚያከናውናቸው ፍጹም የተለያዩ ናቸው ፥ በተለይ በአማራ ሕዝብና በኢትዮጵያ ኦርቶዶድክስ ተዋህዶ እምነት ላይ ያለው ጥላቻ ወሰን የለውም ፥ በዚህ አነጋግሩ ደግሞ የሚታለል ካለ በመርሳት በሽታ የተጠቃ ወይም ማሰብ የተሳነው ደካማ ፍጡር እንጂ ንፁህ አዕምሮ ያለው ሰው አብይን ማመን የሚያስችል ተግባር ፈጽሞ የለም ፥ የሰው ልጅ የሚታለለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው ፥ በተደጋጋሚ የሚታለል ግን ከላይ እንደጠቀስኩት ጤነኛ ያልሆነ ብቻ ነው ፥ አብይ አፈ ቅቤ ሲሆን ልበ ጩቤ ነው ፥ አብይ ኢትዮጵያን የመምራት ብቃት ፈፅሞ የለውም ፥ ዘረኛና ያልበሰለ አዕምሮ ያለው ሲሆን በሌላ በኩል ፈፅሞ ውሸታም ነው ፥ የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ውጊያ ላይ ፈፅሞ አልተሳተፉ እያለ ሲምል ሲገዘት የነበረ ሰው በትናትናው ዕለት በደረሰበት የምዕራባውያን ተፅኖ እውነታውን አፍርጦ ነገረን ፥ ለውሸቱ ማስፅናኛ ይሁን ወይም የገቡበትን ምክንያት ሲገልፅ ኤርትራ ባለውለታችንና ልናመሰግናቸው እንደሚገባም … ሌላም ሌላም ነገር ተናግሮዋል ፥ በእኔ በኩል ለምን የሚመራውን ሕዝብ በገሃድ ይዋሻል በሚል እንጂ ፋሽስቱ ወያኔን የኤርትራ ጦር በመዋጋቱ ቅሬታ የለኝም ፥ አብይ በዚህ ሶስት ዓመታት ውስጥ አያሌ ውሸቶችን ዋሽቷል ፥ አታልሎዋል ፥ በርካታ የአማራ ተወለጆችንና የኦርቶዶድክስ ሃይማኖት ተከታዮችን እንዲገደሉ አድርጎዋል ፥ አብይ ወንጀለኛ እንጂ ኢትዮጵያን የመምራት ብቃቱም ሆነ ስብዕናው አይፈቅድም ፥ እንዳውም እርሱ በሥልጣን ላይ ከቆየ ኢትዮጵያን ያፈርሳታል ፥ የአብይ አካሄድ ፈፅሞ ለሀገራችን እጅግ አስጊና ከተቻለ በፍጥነት ከሥልጣን መወገድ የሚገባው ፋሽስታዊና አፓርታይዳዊ አገዛዝ የሚያካሂድ ኦነግ ነው ፡፡

    Reply
    • tinbaso says

      March 31, 2021 04:48 am at 4:48 am

      አብዛኛው የ360 ሚዲያ አባላት በአብይ አህመድ ስር የሰደደ የጥላቻ በሽታ የተለከፋ ናቸው፡፡ በግለሰቦች ጥላቻ ላይ ያተኮረ ትንታኔ የሚያቀርብ እንደ 360 ያለ ሚዲያ ለህዝብ ከሚሰጠው ጥቅም ይልቅ ጉዳቱ እጅግ ይበልጣል፡፡ 360 ዶክተር አብይ እስከ አሁን ያከናወናቸውን መልካም ስራዎች የሚያይበት አይኖች የሌሉት እውር ሚዲያ ሲሆን አይናቸው የሚከፈተው የዶክተር አብይን ስህተቶች ለማየት ብቻ ነው፡፡ እንዲህ አይነት ሚዛናዊነት የጐደለው የየዕለት ዶክተር አብይ ጥላቻ ተኮር ወሬዎቻቸው በህዝብ ዘንድ ያስገኘላቸው እና የሚያስገኝላቸው ነገር ቢኖር ንቀት፡ ተአማኒነት ማጣት፡ ጥላቻን በስተመጨረሻም ውድቀትን ነው፡፡
      “”አሁንም በውድቀት መንገድ ላይ ያለ ሚዲያ ነው ነገር ግን ሙሉ ለሙሉ ከመውደቁ እና እንደ ህወሀት ታሪክ ሆኖ ከመቅረቱ በፊት በእጁ ባሉት ጊዜያቶች ተጠቅሞ እውነተኛ የኢትዮጵያ ሕዝብ አይን እና ጆሮ ለመሆን ከፈለገ እንደ ሀብታሙ እና ኤርምያስ አሰልቺ ጥላቻ ተኮር ወሬዎችን የሚያቀርቡ ግለሰቦችን ከስህተታቸው እንዲታረሙ ወይም ስራቸውን እንዲለቁ ካልተደረገ በስተቀር ውድቀቱ አይቀሬ ይሆናል፡፡

      ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የ360 ሚዲያ እንደሚያወራው በሆኑ ዘርና ሃይማኖት ጥላቻ ተለክፎ እነርሱን ለማጥፋት የሚሰራ ሳይሆን ለሁሉም የኢትዮጵያ ብሄሮች እና ሃይማኖቶች እኩልነት እንዲሁም ለኢትዮጵያ ህዝቦች ብልጽግና እውን መሆን ሌተ ተቀን የሚሰራ እና ህዝቡንም የሚያሰራ ብርቅና ድንቅ እንዲሁም ልዩ መሪያችን ነው ፡፡

      Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule